ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 23–29 (እ.አ.አ)፦“ተነሱ እናም ወደ እኔ ኑ።” 3 ኔፊ 8–11


“መስከረም 23–29፦‘ተነሱ እናም ወደ እኔ ኑ።’ 3 ኔፊ 8-11፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“መስከረም 23–29 (እ.አ.አ)፣ 3 ኔፊ 8–11፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ክርስቶስ ለኔፋውያን ታየ

እኔ የአለም ብርሃን ነኝ፣ በጀምስ ፉልመር

መስከረም 23–29 (እ.አ.አ)፦“ተነሱ እናም ወደ እኔ ኑ።”

3 ኔፊ 8–11

“እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፣ ነቢያት ወደ ዓለም ይመጣል ብለው የመሰከሩልኝም” (3 ኔፊ 11:10)። ከ600 ዓመታት በላይ የሆናቸውን የመፅሐፈ ሞርሞን ትንቢቶች እንዲፈፀሙ በማድረግ ከሞት የተነሳው አዳኝ እራሱን ያስተዋወቀው በእነዚህ ቃላት ነበር። ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ “ያ መከሰት እና ያ ንግግር በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ ውስጥ የትኩረት ማዕከልና እጅግ ታላቁ ጊዜ ነበር” ሲሉ ፅፈዋል። እያንዳንዱን ኔፊያዊ ነቢይ አሳውቆ እና አነሳስቶ የነበረ መገለጥ እና ንግግር ነበር። ሁሉም ሰለእርሱ አውርቶ፣ ዘምሮ፣ አልሞ እና እንዲመጣ ፀልዮ ነበር—ሆኖም በርግጥ በእዚህ ተከስቶ ነበር። የቀናቶች ሁሉ ቀን! እያንዳንዱን ድቅድቅ ጨለማ ወደ ቀን ብርሃን የሚለውጠው እግዚአብሔር መጥቷል (ክርስቶስ እና አዲሱ ቃልኪዳን [1997 (እ.አ.አ)]፣ 250–51)።

በተጨማሪም “Jesus Christ Appears in the Ancient Americas” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

3 ኔፊ 8–11

ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነው።

ከጨለማ እና ከብርሃን ጋር የተያያዙ ጭብጦች በመላው 3 ኔፊ 8–11 ውስጥ ተደጋግመው እንደሚገኙ ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ከእነዚህ ምዕራፎች ስለመንፈሳዊ ጨለማ እና ብርሃን ምን ትማራላችሁ? (ለምሳሌ እነዚህን ተመልከቱ 3 ኔፊ 8:19–239:1810:9–13)። ጨለማን ወደ ህይወታችሁ የሚያመጣው ምንደን ነው? ብርሃንን የሚያመጣውስ? አዳኙ እራሱን እንደ “የዓለም ብርሃንና ህይወት” ያስተዋወቀው ለምን ይመስላችኋል? (3 ኔፊ 9:1811:11)።

3 ኔፊ 9–11 ውስጥ የተገለጹት ክስተቶች በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ እጀግ ቅዱስ ከሆኑት መካከል ናቸው። በዝግታ አንብቧቸው እንዲሁም በጥንቃቄ አሰላስሏቸው። እናንተን ለመርዳት የቀረቡ ጥያቂዎች እነሆ። ወደ እናንተ የሚመጡትን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች መመዝገብን ታሳቢ አድርጉ።

  • ከነዚህ ሰዎች መካከል ብሆን ኖሮ እንዴት ተሰምቶኝ ይሆን ነበር?

  • በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ስለ አዳኙ ምሳሌ ምን ያስደንቀኛል?

  • ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ እንደሆነ እንዴት አውቃለሁ?

  • በህይወቴ ውስጥ ብርሃን የሆነው እንዴት ነው?

በተጨማሪም የሼረን ዩባንክን፣ “Christ: The Light That Shines in Darkness [ክርስቶስ፦በጨለማ የሚያበራው ብርሀን]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 73–45ን ይመልከቱ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። የምትቀበሏቸውን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ስትመዘግቡ የበለጠ የመቀበል ችሎታችሁ የሰፋ ነው።

3 ኔፊ 9–10

ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይጓጓል።

ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን “አዳኙ ሃጢያታችንን ይቅር ለማለት እንደሚችል እና ይቅር ለማለት እንደሚጓጓ እመሰክራለሁ” ሲሉ ተናግረዋል (“Repent … That I May Heal You,” ሊያሆና፤ ሕዳር 2009(እ.አ.አ)፣ 40)። ክርስቶስ ይቅር ለማለት እንደሚጓጓ የሚያሳይ ማስረጃን በ3 ኔፊ 9–10 ውስጥ ፈልጉ። በ3 ኔፊ 9:13–2210:1–6 ውስጥ ፍቅሩ እና ምህረቱ እንዲሰማችሁ የሚረዳቸሁን ታገኛላችሁ? እርሱ “እንደሚሰበስባችሁ” እና “እንደሚመግባችሁ” የተሰማችሁ መቼ ነው? (3 ኔፊ 10፥4 ይመልከቱ)።

3 ኔፊ 9፥19-22

ጌታ “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ” ይፈልጋል።

አዳኙ ከመምጣቱ በፊት የእንስሳት መስዋዕቶች የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት ምልክት ነበሩ። ( ሙሴ 5:5–8 ይመልከቱ)። አዳኙ በ3 ኔፊ 9:20–22 ውስጥ ምን አዲስ ትዕዛዝ ሰጥቷል? ወደ እርሱ እና ወደመስዋዕቱ የሚመራን እንዴት ነው?

የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ ማቅረብ ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? አዳኙ ይህንን መስዋዕት ከእናንተ እንደሚፈልግ የሚሰማችሁ ለምንድን ነው?

3 ኔፊ 11፥1–8

ምስል
seminary icon
የእግዚአብሄርን ድምፅ ለመስማት እና ለመረዳት መማር እችላለሁ።

እግዚአብሄር እያናገራችሁ እንደሆነ የምታውቁት እንዴት ነው? ምናልባት በ3 ኔፊ 11፥1–8 ውስጥ ያሉት ህዝቦች ተሞክሮዎች የእግዚአብሔርን ድምፅ የመስማት እና የመረዳት አንዳንድ መርሆዎችን እንድትገነዘቡ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ሕዝቡ የሰሙትን የእግዚአብሔርን ድምጽ ባህሪያት እና እርሱን የበለጠ ለመረዳት ያደረጉትን ነገር ልታስተውሉ ትችላላችሁ።

ስለእግዚአብሔር ድምጽ ወይም ስለመንፈሱ ተጽዕኖ የሚገልጹ ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትን ለመመርመር ሊረዳም ይችላል። የተወሰኑት ቀርበውላችሁሃል። ምናልባት እነዚህን ካነበባችሁ በኋላ መገለጥን ለማወቅ የሚረዱ አንዳንድ መመሪያዎችን ልትፅፉ ትችላላችሁ፦1 ነገሥት 19:11–12ገላትያ 5:22–23አልማ 32:27–28, 35ሔለማን 10:2–4ኤተር 4:11–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9:7–911:11–14

የእግዚአብሄርን ድምፅ የመስማት እና የመከተል ልምድ ካላቸው ከዘመኑ ነቢያት፣ ሐዋርያት እና ከሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ከመስማትም ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ብዙዎቹ ልምዳቸውን በ“እርሱን ስሙት!” የወንጌል ላይብረሪ የቪዲዮ ሥብሥቦች ውስጥ ልምዳቸውን ያካፍላሉ። አንድ ወይም ከአንድ በላይ መመልከትን አስቡ።

የእግዚአብሔርን ድምጽ ይበልጥ በጥራት ስለመስማት እና ስለመለየት የተማራችሁትን እንዴት ተግባራዊ ታደርጋላችሁ?

እንዲሁም ራስክ ኤም ኔልሰን፣ እርሱን ስሙት!ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 88–92፤ ይመልከቱ። የምወደው ልጄ ይህ ነውየልጆች መዝሙር መፅሀፍ  76 የወንጌል አርዕስቶች የግል መገለጥ

ምስል
ኢየሱስ የችንካሩን ምልክት ለኔፋውያን እያሳየ

One by One [አንድ በአንድ]፣ በዋልተር ሬን

3 ኔፊ 11፥8–17

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእርሱ የግል ምስክርነት እንዳገኝ ይጋብዘኛል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጠ ጊዜ ወደ 2,500 የሚጠጉ ሰዎች በለጋስ ምድር በሚገኘው ቤተመቅደስ ተሰብስበው ነበር (3 ኔፊ 17:25 ይመልከቱ)። ይህ ብዙ ቁጥር ቢሆንም አዳኙ በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ ያሉትን የችንካሩን ምልክት እንዲዳስሡ እያንዳንዳቸውን “አንድ በአንድ” ጋበዛቸው (3 ኔፊ11:14–15)። በምታነቡበት ጊዜ እዚያ መገኘት ምን አይነት ስሜት ይኖረው እንደሆነ አስቡ። አዳኙ “[እንድትነሱ] እና [ወደ እርሱ እንድትመጡ] እየጋበዛችሁ ያለው በምን መንገዶች ነው? (3 ኔፊ 11:14).

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

3 ኔፊ 8–9

በጨለማ ውስጥ ስሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ሊሆነኝ ይችላል።

  • ልጆቻችሁ በ3 ኔፊ 8-9 ውስጥ የተገለጹትን ልምዶች እንዲያገነዘቡ ለመርዳት የእነዚህን ምዕራፎች የተወሰኑ ክፍሎች በጨለማ ክፍል ውስጥ እንደገና ለመተረክ ወይም ለማዳመጥ ትችላላችሁ። ለሶስት ቀናት በጨለማ ውስጥ መሆን ምን ሊመስል ይችል እንደነበር ተወያዩ። ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ለምን የዓለም ብርሃን ብሎ እንደጠራ ተነጋገሩ (3 ኔፊ 9:18 ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ ብርሃናችን ይሆን ዘንድ ሕዝቡን እና እኛን ምን እንድናደርግ ጋብዟል? (3 ኔፊ 9:20–22)።

3 ኔፊ 10፥4–6

ዶሮ የጫጩቶቿን ደህንነት እንደምትጠብቅ ኢየሱስም ህዝቡን ይጠብቃል።

  • ዶሮ ጫጩቶቿን የምትሰበስብበት ዓይነ ህሊናዊ ምስል ልጆች የአዳኙን ባህርይ እና ተልዕኮ እንዲገነዘቡ ለመርዳት የሚችል ኃይለኛ የማስተማሪያ መሳሪያ ሊሆን ይችላል። ቤተሰባችሁ የዶሮ እና የጫጩቶችን ሥዕል እየተመለከተ እያለ እናንተ 3 ኔፊ 10:4–6 ልታነቡ ትችላላችሁ። ዶሮ ጫጩቶቿን መሰብሰብ የሚያስፈልጋት ለምንድን ነው? አዳኙ ወደ እርሱ ሊሰበስበን የሚፈልገው ለምንድን ነው? ጥበቃ ለማግኘት ወደ እርሱ መምጣት የምንችለው እንዴት ነው?

3 ኔፊ 11፥1–15

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንድመጣ ይጋብዘኛል።

  • 3 ኔፊ11:1–15ን በጋራ ስታነቡ ልጆቻችሁ መንፈሱ እንዲሰማቸው የምትረዷቸው እንዴት ነው? ምናልባት የእግዚአብሄር ፍቅር እንዲሰማቸው የረዳቸውን አንድ ነገር በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ሲያገኙ እንዲነግሯችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በዚህ መዘርዝር ውስጥ ባሉት ሥዕሎች ወይም “Jesus Christ Appears at the Temple” (የወንጌል ላይብረሪ).በሚለው ቪዲዮም እንዲሁ ልታደርጉ ትችላላችሁ። ስለነዚህ ክስተቶች ስታነቡ እና ስታሰላስሉ እንዴት እንደሚሰማችሁ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው። እነርሱም ሥሜቶቻቸውን እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው።

3 ኔፊ 11፥1–8

እግዚአብሔር በለስላሳ አነስተኛ ድምፅ ያናግረኛል።

  • ምናልባት ከእነዚህ ጥቅሶች የተወሰኑትን በለስላሳ “በአነስተኛ ድምፅ” ልታነቡ ትችላላችሁ፡፡(3 ኔፊ 11:3). ወይም እንደ“ This Is My Beloved Son፣” ያለ መዝሙር ቅጂን ለመስማት በሚያስቸግር አነስተኛ ድምፅ ልታጫውቱ ትችላላችሁ (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣76)። ከሰማይ የሚመጣውን ድምጽ ለመረዳት ህዝቡ ምን ማድረግ ነበረባቸው? ቁጥር 5-7 ይመልከቱ)። ከእነርሱ ተሞክሮ ምን እንማራለን?

3 ኔፊ 11፥21–26

ኢየሱስ ክርስቶስ እንድጠመቅ ይፈልጋል።

  • እናንተ 3 ኔፊ 11:21–26ን ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ ጥምቀት የሚለውን ቃል በሰሙ ቁጥር እንዲቆሙ መጋበዝ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ስለጥምቀት ምን አስተምሯል? ልጆቻችሁ ከዚህ በፊት የጥምቀት ሥርዓት አይተው የሚያውቁ ከሆነ ያዩትን እንዲገልፁ ጠይቋቸው። ኢየሱስ እንድንጠመቅ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ክርስቶስ ለኔፋውያን ታየ

One Shepherd [አንድ እረኛ]፣ በሓዋርድ ሊዮን