መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
5. አጠቃላይ እና የዋና አካባቢ አመራር


“5. አጠቃላይ እና የዋና አካባቢ አመራር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]

“5. አጠቃላይ እና የዋና አካባቢ አመራር፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ቀዳሚ አመራር

5.

አጠቃላይ እና የዋና አካባቢ አመራር

5.0

መግቢያ

ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኗ ”የማዕዘን ራስ ድንጋይ” ነው (ኤፌሶን 2፥20)። እርሱ ሁሉንም የክህነት ቁልፎች ይዟል። በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ እንዲረዱት ሃዋርያትን እና ነቢያትን ጠርቷል። በምድር ላይ ያለችውን የእግዚአብሔር መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የሚመለከቱ ሁሉንም ቁልፎች ለእነዚህ ለተመረጡ አገልጋዮቹ ሰጥቷል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥12–13፤ እንዲሁም በዚህ መመሪያ መፅሐፍ 3.4.1 ይመልከቱ)።

በነቢያት እና በሐዋርያት አማካኝነት፣ ጌታ በአለም ሁሉ ያለውን ስራውን ይረዱ ዘንድ ሰዎችን በሰባዎች ክፍል ይጠራል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥38 ን ይመልከቱ)። በተጨማሪም የኤጲስ ቆጶስ አመራር፣ አጠቃላይ መሪዎች፣ እና ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች መሪዎች በስራው እንዲረዱ አስፈላጊ ኃላፊነቶች ተሰጥቷቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች ምዕራፍ 5አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ( )።