መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
29. የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች


“29. የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“29. የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
እናት እና ልጇ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ

29.

የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች

29.0

መግቢያ

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ለአምልኮ፣ እርስ በርስ ለመተናነፅ እንዲሁም ወንጌልን ለማስተማር እና ለመማር ይሰሰባሉ (አልማ 6፥6ሞሮኒ 6፥5–6 ይመልከቱ)። አዳኙ ቃል እንደገባው፣ “ሁለት ወይም ሶስት በስሜ በሚሰበሰቡበት እኔ በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ” (ማቴዎስ18፥20)። በህብረት መሰብሰብ ልቦቻችን “በአንድ ላይ በአንድነት እና አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር [የሚጣበቁበት]” አንዱ መንገድ ነው (ሞዛያ 18፥21)።

ሆኖም ስብሰባ ማድረግ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማገልገልን መተካት የለበትም።

29.1

ስብሰባዎችን ማቀድ እና ማካሄድ

መሪዎች “እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝ እና ራዕይ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት” ስብሰባዎችን ማቀድ እና ማከናወን አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥45ን፤ በተጨማሪምሞሮኒ 6፥9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥2ን ይመልከቱ)። በስብሰባዎቻቸው ላይ የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ለመጋበዝ መንገዶችን ይፈልጋሉ።

መሪዎች የስብሰባዎች ብዛት እና ርዝመት በቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ ጫና አለመፍጠሩን ያረጋግጣሉ።

29.2

የአጥቢያ ስብሰባዎች

29.2.1

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

29.2.1.1

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን ማቀድ

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን ያቅዳል እንዲሁም ይመራል። ስብሰባው በቅዱስ ቁርባኑ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን በመገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑን ያረጋግጣሉ።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ አንድ ሰዓት ይፈጃል። የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  1. የመግቢያ ሙዚቃ (ለመመሪያው 19.3.2 ንይመልከቱ)።

  2. ሰላምታ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት።

  3. ለስብሰባው የበላይ መሪ ባለሥልጣናት ወይም ለሌሎች ጎብኚ መሪዎች እውቅና መስጠት።

  4. ማስታወቂያዎች። እነዚህ የተቻለውን ያህል አጭር መሆን አለባቸው።

  5. የመክፈቻ መዝሙር እና ጸሎት 19.3.2 እና 29.6 ይመልከቱ።

  6. እንደሚከተሉት ያሉ የአጥቢያ እና የካስማ ሥራዎች

    • ለመሪዎች እና ለአስተማሪዎች ድጋፍ መስጠት እንዲሁም ማሰናበት (30.3 እና 30.6 ይመልከቱ)።

    • በአሮናዊ ክህነት ክፍሎች የሚሾሙ ወንድሞችን ሥሞች ማቅረብ (18.10.3 ይመልከቱ)።

    • በቅርብ ጊዜ የተለወጡትን ጨምሮ ለአዲስ የአጥቢያ አባላት እውቅና መስጠት።

  7. ልጆችን መሰየም እና በረከት መስጠት (18.6 ይመልከቱ)። ይህ በአብዛኛው የሚከናወነው በጾም እና በምስክርነት ስብሰባ ላይ ነው (29.2.2 ይመልከቱ)።

  8. ለአዳዲስ አባላት ማረጋገጫ መስጠት (18.8 ይመልከቱ)።

  9. የቅዱስ ቁርባን መዝሙር እና ቅዱስ ቁርባንን ማከናወን ቅዱስ ቁርባን የስብሰባው ዋነኛ ትኩረት ነው። ይህ ሥርዓት አባላት ሃሳባቸውን ወደ አዳኙ እና ለእነርሱ ወደከፈለው መስዋዕት የሚመራ አጋጣሚ ነው።

    ቅዱስ ቁርባንን ስለማዘጋጀት፣ ስለመባረክ እና ስለማሳለፍ የበለጠ ለማግኘት 18.9 ይመልከቱ።

  10. የወንጌል መልዕክት እና የምዕመናን ዝማሬ ወይም ሌላ ሙዚቃ።

  11. የመዝጊያ መዝሙር እና ጸሎት።

  12. የመዝጊያ ሙዚቃ

29.2.1.4

ተናጋሪዎችን መምረጥ

የኤጲስ ቆጶሱአመራሩ ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ተናጋሪዎችን ይመርጣሉ። አብዛኛውን ጊዜ፣ ወጣቶችን ጨምሮ የአጥቢያ አባላትን ይጋብዛሉ።

ተናጋሪዎቹ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ይሰጣሉ እንዲሁም ቅዱሳት መጻህፍትን በመጠቀም ወንጌሉን ያስተምራሉ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥1252፥9ይመልከቱ)።

29.2.2

የጾም እና የምስክርነት ስብሰባ

በጾም እና ምሥክርነት ስብሰባ ላይ ተናጋሪዎች አይመደቡም ወይም ልዩ የመዝሙርሙዚቃ ምርጫዎች አይኖሩም። ከዚያ ይልቅ ስብሰባውን የሚመራው ግለሰብ አጭር ምስክርነቱን ይሰጣል። ከዚያም የስብሰባው ተሳታፊዎች ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ይጋብዛል። ምስክርነት መስጠት ማለት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የወንጌልን እውነታዎች መናገር ማለት ነው።

29.2.3

የአጥቢያ ጉባኤ

29.2.4

የኤጲስ ቆጶስ አመራር ስብሰባ

ግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • በካስማው ውስጥ የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ማስተባበር።

  • በአጥቢያው ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ማጠናከር—በተለይ ወጣቶችን እና ልጆችን።

  • የክህነት ሥርዓቶችን ጨምሮ ሥርዓቶችን ለመቀበል ሊዘጋጁ የሚችሉ አባላትን መለየት።

  • በአጥቢያ መደቦች ሊጠሩ የሚችሉ አባላትን መለየት።

29.2.5

የአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባ

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባዎችን ያቅዳል፣ ይመራል፣ እንዲሁም ያካሂዳል። ምክር ቤቱ ኤጲስ ቆጶሱ ሳይኖር ዋና ውሳኔዎችን አያደርግም።

የአጥቢያ ድርጅት መሪዎች በአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ በሁለት በኩል ይሳተፋሉ።

  1. ሁሉንም የአጥቢያ አባላት በመባረክ እንደሚረዱ እንደ አጥቢያ ምክር ቤት አባላት።

  2. እንደ ድርጅቶቻቸው ተወካዮች።

በጋራ ሲሰበሰቡ፣ የአጥቢያ ምክር ቤት አባላት ከመላው ምክር ቤት የተቀናጀ ጥረት ሊጠቀሙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ። እያንዳንዱ የምክር ቤት አባል በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሀሳቡን/ቧን እና በመንፈስ የተነሳሳ ግንዛቤውን/ዋን እንዲያካፍል/ድታካፍል ይበረታታል/ትበረታታለች።

ብዙውን ጊዜ የአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባ ከአንድ ሰዓት በላይ አይቆዩም። በጸሎት እና ባለፉት ስብሰባዎች በተሰጡ ስራዎች አጭር የክንውን ሪፖርቶች ይጀምራሉ። ኤጲስ ቆጶሱ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ለመባረክ ይበልጥ ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ቅድሚያ ይሰጣል።

  • በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር። ሁሉም አባላት እምነትን እንዲገነቡ፣ የመዳን ሥርዓቶችን እንዲቀበሉ እና ቃል ኪዳኖቻቸውን እንዲጠብቁ መርዳት።

  • እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት፡፡ ግለሰቦችን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቡን ለመባረክ ሃብቶችን እና ክህሎቶችን ማጋራት። የአጥቢያው አባላት ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ መርዳት። (ምዕራፍ 22 ይመልከቱ።)

  • ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ። ስለወንጌል የሚማሩትን እንዲሁም አዲስ እና እንደገና ወደቤተክርስቲያኗ የተመለሱ አባላትን እድገት መገምገም። አባላት ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል የሚችሉባቸውን መንገዶች መወያየት። (ምዕራፍ 23 ይመልከቱ።)

  • ቤተስቦችን ለዘለአለም ማጣመር። የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ያሉ አባላትን እድገት መገምገም። ብዙ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለማግኘት ብቁ እንዲሆኑ ለመርዳት መንገዶችን ማቀድ። አባላት በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ላይ ሊሳተፉ ስለሚችሉባቸው መንገዶች መወያየት። (ምዕራፍ 25 ይመልከቱ።)

የምክር ቤቱ አባላት ማንኛውንም የግል ወይም ጥንቃቄ የሚያሻው መረጃ ሚስጥራዊ አድርገው መያዝ አለባቸው ( 4.4.6ን ይመልከቱ)።

29.2.6

የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ

ከእያንዳንዱ ስብሰባ በፊት ኤጲስ ቆጶሱና ግምገማውን የሚመራው ሰው ለውይይት የሚቀርቡትን ነገሮች ይከልሳሉ።

  • የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ

  • በአጥቢያው ውስጥ ያሉ ወጣቶች ፍላጎቶች እና እነሱን ለማሟላት የሚቻልባቸው መንገዶች።

  • ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን ወይም አዲስ አባላትን ለመርዳት የሚደረግ ጥረት።

  • አክቲቪቲዎች—እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የማገልገል እድሎችን ጨምሮ። አብዛኛው እቅድ የሚታቀደው በቡድን ወይም በክፍል የአመራር ስብሰባዎች ነው (ምዕራፍ 20 ይመልከቱ)።

  • ማገልገል (ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ።)

  • አዲስ ለተጠሩ የቡድን እና የትምህርትክፍል አመራሮችን መግለጫ መስጠት።

29.2.8

የእሁድ ስብሰባዎች መርሃ ግብር

አጥቢያዎች ከሚከተሉት የሁለት ሰዓት መርሃ ግብሮች አንዱን ለእሁድ ስብሰባዎች ይጠቀማሉ።

ዕቅድ 1

60 ደቂቃዎች

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

10 ደቂቃ

ወደ ክፍሎች እና ወደስብሰባዎች መሸጋገሪያ

50 ደቂቃዎች

በሁሉም እሁዶች፦ የመጀመሪያ ክፍል፣ የህጻናትን ክፍል ጨምሮ

በየወሩ በመጀመሪያው እና በሶስተኛው እሁዶች፦ የሰንበት ትምህርት

በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁዶች፦ የክህነት ቡድን ስብሰባዎች፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባዎች እና የወጣት ሴቶች ስብሰባዎች

በአምስተኛው እሁዶች፦ የወጣቶች እና የጎልማሶች ስብሰባዎች። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ርዕሱን ይወስናል እንዲሁም አስተማሪዎችን ይመድባል።

ዕቅድ 2

50 ደቂቃዎች

በሁሉም እሁዶች፦ የመጀመሪያ ክፍል፣ የህጻናትን ክፍልን ጨምሮ

በየወሩ በመጀመሪያው እና በሶስተኛው እሁዶች፦ የሰንበት ትምህርት

በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁዶች፦ የክህነት ቡድን ስብሰባዎች፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባዎች እና የወጣት ሴቶች ስብሰባዎች።

በአምስተኛው እሁዶች፦ የወጣቶች እና የጎልማሶች ስብሰባዎች። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ርዕሱን ይወስናል እንዲሁም አስተማሪዎችን ይመድባል።

10 ደቂቃዎች

ወደ ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ መሸጋገር

60 ደቂቃዎች

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

29.3

የካስማ ስብሰባዎች

29.3.1

የካስማ ጉባኤ

29.3.2

የካስማ አጠቃላይ የክህነት ስብሰባ

29.3.3

የካስማ የክህነት መሪዎች ስብሰባ

29.3.4

የካስማ መሪዎች ስብሰባዎች

29.3.5

የካስማ ሊቀ ካህናት ቡድን ስብሰባ

29.3.6

የካስማ አመራር ስብሰባ

29.3.7

የከፍተኛ ምክር ቤት ስብሰባ

29.3.8

የካስማ ምክር ቤት ስብሰባ

29.3.9

የካስማ የጎልማሶች መሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ

29.3.10

የካስማ የወጣቶች መሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ

29.3.11

የካስማ የኤጲስ ቆጶሳት ምክር ቤት ስብሰባ

29.5

የሞቱ ሰዎች የቀብር እና የሌሎች ነገሮች ሥርዓቶች

29.5.1

አጠቃላይ መርሆዎች

ለሞቱ የሚደረጉ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች አስፈላጊ ዓላማ ስለደህንነት ዕቅድ በተለይም ስለአዳኙ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ መመስከር ነው። እነዚህ አገልግሎቶች የተከበሩ መንፈሳዊ ተሞክሮዎች መሆን አለባቸው።

የቤተክርስቲያን መሪዎች የሌሎች ሃይማኖቶችን ወይም ቡድኖችን የአምልኮ ሥርዓቶች ለሞቱ በሚደረጉ የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች ውስጥ ማካተት የለባቸውም።

29.5.2

ለቤተሰቡ እርዳታ ማድረግ

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላት “ከሚያዝኑት ጋር [ያዝናሉ] … መፅናናትን ለሚፈልጉ [ያፅናናሉ]” (ሞዛያ 18፥9)። አንድ አባል በሚሞትበት ጊዜ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ቤተሰቡን ለማፅናናት ይጎበኛል።

ኤጲስ ቆጶሱ ከሽማግሌዎች ቡድን እና ከሴቶች መረዳጃ ማህበር ጨምሮ ከአጥቢያ አባላት የሚገኝን እርዳታ ይሰጣል።

29.5.4

የቀብር ሥርዓቶች (በባህላዊ በሚከናወኑበት ቦታ)

በቤተክርስቲያኗ ህንፃ ውስጥም ሆነ በሌላ ቦታ በኤጲስ ቆጶሱ አማካኝነት የሚደረግ የቀብር ሥነ ሥርዓት የቤተክርስቲያን ስብሰባ እና የሃይማኖት ሥርዓት ነው። መንፈሳዊ ጊዜ መሆን አለበት።

የቀብር ሥነ ሥርዓቶች በሰዓታቸው መጀመር አለባቸው። በአጠቃላይ ለተገኙት ክብር ሲባል ከ1.5 ሰዓታት በላይ መቆየት የለባቸውም።

በተለምዶ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች በእሁድ ቀን አይካሄዱም።

29.6

በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ የሚደረጉ ጸሎቶች

በቤተርስቲያኗ ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ ጸሎቶች አጭር፣ ቀላል እና በመንፈስ የሚመሩ መሆን ይገባቸዋል። ማንኛውም የተጠመቀ የቤተክርስቲያኗ አባል የመክፈቻ እና የመዝጊያ ጸሎት ማቅረብ ይችላል። ያልተጠመቁ ልጆች በመጀመሪያ ክፍል መጸለይ ይችላሉ።

29.7

በቀጥታ የሚተላለፉ ስብሰባዎች እና በኮምፒተር የታገዙ የገፅ ለገፅ ስብሰባዎች

ኤጲስ ቆጶሱ በልዩ ሁኔታ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎችን እና በመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚደረጉ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን እንዲሁም የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶችን በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፉ ሊፈቅድ ይችላል።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ የቀጥታ ስርጭት የቅዱስ ቁርባን ሥርዓቱን አይጨምርም።

ለአንዳንድ ስብሰባዎች፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአካል መገኘት የማይችሉ አባላትን በኮምፒተር በታገዘ የገፅ ለገፅ ዘዴ እንዲሳተፉ ሊፈቅድላቸው ይችላል። እነዚህ ስብሰባዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • የአመራር ወይም የምክር ቤት ስብሰባዎችን የመሳሰሉ የአመራር ስብሰባዎች።

  • የቡድን፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የወጣት ሴቶች ስብሰባዎች።

  • የሰንበት ትምህርት ክፍሎች

  • የመጀመሪያ ክፍል የትምህርት ክፍሎች እና የመዝሙር ጊዜ