መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም


“35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“35. የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ሰዎች መስታወት እየወለወሉ እና በቫኪዩም እያጸዱ

35.

የስብሰባ አዳራሾች አያያዝ እና አጠቃቀም

35.1

ዓላማ

የቤተክርስቲያኗ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን የምታቀርበው የሚገቡበት ሁሉ፦

35.2

ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

35.2.2

የቤተክርስቲያኗ ፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ

በቤተክርስቲያኗ የተቀጠረ/ረች የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ እያንዳንዱ ካስማ የስብሰባ አዳራሾችን መጠቀም እንዲችል ይረዳል። እርሱ ወይም እርሷ ዋና ጥገናዎችን፣ ሙሉ ፅዳትን እና መደበኛ የህንፃ ጥገና እንዲደረግ ያመቻቻል/ታመቻቻለች።

እንደ አስፈላጊነቱ፣ የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪው፣ የካስማ እና የአጥቢያ የሕንፃ ተወካዮች ሕንፃውን እንዴት እንደሚያፀዱ እና ሌሎች የአካባቢ ሥራዎችን እንዴት እንደሚሠሩ በማስተማር ያግዛል/ታግዛለች። እርሱ ወይም እርሷ መመሪያዎችን፣ ቁሳቁሶችን እና መሳሪያዎችን ያቀርባል/ታቀርባለች።

እርሱ ወይም እርሷ የግንባታ ወጪዎችን ከኤጲስ ቆጶሳት ጋር መገምገምም ይችላል/ትችላለች።

35.2.7

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ኤጲስ ቆጶስ አመራሩ (ወይም የአጥቢያው የሕንፃ ተወካይ) አባላት ሕንፃውን እንዴት እንደሚጠቀሙ፣ እንደሚንከባከቡ እና ደህንነቱን እንደሚጠብቁ ያስተምራቸዋል። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የህንጻ ቁልፎችን ለአጥቢያ መሪዎች ይሰጣል።

በህንፃው እንዲሁም በግቢው ውስጥ የሚደረጉ አክቲቪቲዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ መደረጋቸውን ያረጋግጣሉ (20.7ን ይመልከቱ)።

ስለጥገና እና የአጠቃቀም ፍላጎቶች ከቤተክርስቲያኗ የፋሲቲዎች አስተዳዳሪ ጋር ይነጋገራሉ። እንዲሁም ተዛማጅ ወጪዎችን ከፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ ጋር መገምገም ይችላሉ።

35.2.9

የአጥቢያ የህንጻ ተወካይ

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ የህንጻ ተወካይን ስለመጥራት ይወስናል። ይህንን ጥሪ ለመስጠት ከወሰኑ ኤጲስ ቆጶሱ አንድን ጎልማሳ ወንድ ወይም ሴት አባል ሊጠራ ይችላል። የአጥቢያው የሕንፃ ተወካይ ካልተጠራ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ይህንን ኃላፊነት ከአማካሪዎቹ ለአንዱ፣ ለአጥቢያ ጸሐፊው ወይም ለረዳት የአጥቢያ ጸሐፊው ወይም ለዋና ጸሐፊው ሊሰጥ ይችላል።

የአጥቢያ የሕንፃ ተወካዩ አባላት እና በጎ ፈቃደኞች ሕንፃውን እንዲያጸዱ እና እንዲጠግኑ ያደራጃቸዋል። እርሱ ወይም እርሷ ባሉት አቅርቦቶች እና መሳሪያዎች እያንዳንዱን ሥራ እንዴት እንደሚሠሩ ያስተምሯቸዋል።

35.3

የስብሰባ አዳራሾችን ማቅረብ

የመሰብሰቢያ አዳራሾች እንደየአካባቢው ፍላጎቶች እና ሁኔታዎች በመጠን እና በዓይነት ይለያያሉ። የመሰብሰቢያ አዳራሸ በቤተክርስቲያን የተገነባ ወይም የተገዛ ቦታ፣ የአንድ አባል ቤት፣ የአካባቢ ትምህርት ቤት ወይም የማህበረሰብ ማዕከል፣ በኪራይ የተገኘ ቦታ ወይም ሌላ የተፈቀደ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

የዋና አካባቢ እና የቅርብ አካባቢ መሪዎች አሁን ያሉትን የመሰብሰቢያ አዳራሾች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ይጥራሉ እንዲሁም ተጨማሪ ቦታን በጥቆማ ለማቅረብ ጥበበኞች ይሆናሉ።

35.4

የስብሰባ አዳራሾችን መጠገን

35.4.1

የስብሰባ አዳራሾችን ማፅዳት እና መጠገን

የአካባቢ መሪዎች እና አባላት ወጣቶችን ጨምሮ፣ እያንዳንዱን ሕንፃ ፅዱ የማድረግ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲሆን የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው።

የፅዳት መርሃ ግብሩ በአባላት ላይ ጫና መፍጠር የለበትም። ለምሳሌ ወደ ሕንፃው የሚደረግ ጉዞ አስቸጋሪ ከሆነ፣ አባላት በህንፃው ባሉበት በዚያው ጊዜ የሳምንታዊ ዝግጅቶች ክፍል አድርገው ማፅዳት ይችላሉ።

35.4.2

ጥገና መጠየቅ

የአጥቢያ እና የካስማ ምክር ቤት አባላት የሕንፃ ጥገና ፍላጎቶችን ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ይህም Facility Issue Reporting (FIR) [የፋሲሊቲ ጉዳዮች ሪፖርት ማቅረቢያ] መሳሪያን በመጠቀም ሊደረግ ይችላል።

35.4.5

ደህንነት እና ጥበቃ

መሪዎች እና አባላት የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፦

  • ደህንነቱ የተጠበቀ መግቢያ እና መውጫ እንዲኖር መተላለፊያ መንገዶችን፣ ደረጃዎችን፣ መውጫ በሮችን እና እቃ ማስቀመጫ ክፍሎች ግልፅ ማድረግ።

  • በህንፃዎች ውስጥ አደገኛ ወይም ተቀጣጣይ ነገሮችን አለመጠቀም ወይም አለማስቀመጥ።

  • ህንጻዎችን የመቆለፍ ሂደቶችን ማዘጋጀት እና መከተል።

  • የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ መሳሪያዎችን ከስርቆት መጠበቅ።

  • እንደ ውሃ፣ መብራት እና ጋዝ ወይም ነዳጅ ያሉ መገልገያዎችን እንዴት መዝጋት እንደሚቻል ማወቅ

እንዳስፈላጊነቱ የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪው/ዋ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሳቁሶች ያሉበትን እንዲሁም መገልገያዎች የሚዘጉበትን ቦታ የሚያሳይ ካርታ ማቅረብ ይችላል/ትችላለች። ስለደህንነት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ“Security and Lockup Procedures [ጥበቃ እና ቦታዎችን የመቆለፍ ሂደት” “የመሰብሰቢያ አዳራሾችን መጠገን” (Meetinghouse Facilities Guide [የመሰብሰቢያ አዳራሽ መመሪያ መፅሐፍ]) ውስጥ ይገኛል። በተጨማሪም 20.7 ይመልከቱ።

35.5

የቤተክርስቲያኗ የንብረት አጠቃቀም ፖሊሲዎች

35.5.1

የጥበብ ስራ

ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ አክብሮትን የማሳየት ዝንባሌ ያላቸው እና አባላት በእርሱላይ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ ሊሆን ይገባል። ይህንን ማዕከላዊ እምነት ለማሳየት የኢየሱስ ክርስቶስ ምስል ያለበትን ሥዕል በስብሰባ አዳራሽ መግቢያው ላይ መሰቀል አለበት።

35.5.2

የማይፈቀዱ የህንጻ አጠቃቀሞች

35.5.2.1

የንግድ አጠቃቀሞች

የቤተክርስቲያን ንብረት ለንግድ ዓላማ ጥቅም ላይ አይውልም። ለምሳሌ፣ ማንኛውንም ዓይነት ንግድ ለመደገፍ ጥቅም ላይ አይውልም። እንዲህ ያለው አጠቃቀም ከቤተክርስቲያኗ ንብረቶች ዓላማዎች ጋር አብሮ አይሄድም። በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗን ንብረት ከቀረጥ ነፃ ማድረግን ሊፈቅዱ ከሚችሉ የአካባቢ ወይም አገራዊ ህጎች ጋር ሊጋጭ ይችላል።

ተሳታፊዎችን ለሚመለምሉ ተናጋሪዎች ወይም አስተማሪዎች፣ ደንበኞችን ለሚለምኑ፣ ወይም ትምህርቶች፣ሴሚናሮችን በሚሰጡበት ጊዜ ክፍያ ለሚከፈላቸው፣ (ለግል ፒያኖ ወይም ኦርጋን ትምህርት ካልሆነ በስተቀር 19.7.2ን ይመልከቱ)፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትምህርቶች እና ሌሎች ተግባራትን ለሚያከናውኑ አይፈቀዱም

35.5.2.2

ለፖለቲካ ዓላማዎች

የቤተክርስቲያኗ ንብረት ለፖለቲካ ዓላማዎች ጥቅም ላይ አይውልም። እነዚህም የፖለቲካ ስብሰባዎችን ወይም ዘመቻዎችን ያካትታሉ። ቤተክርስቲያኗ ከፖለቲካ ገለልተኛ ናት (38.8.30ን ይመልከቱ)።

35.5.2.3

ሌሎች አጠቃቀሞች

ያልተፈቀዱ ሌሎች የቤተክርስቲያኗ ንብረቶች አጠቃቀም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የተደራጁ የአትሌቲክስ ተግባራትን ወይም ሌሎች በቤተክርስቲያኗ ስፖንሰር ያልተደረጉ ዝግጅቶችን ማካሄድ። የማህበረሰብ መዘምራን እና የመዘጋጃ ቤት ጋብቻዎች በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ (ስለማዘጋጃ ቤት ጋብቻዎች 38.3.4ን ይመልከቱ)።

  • ለአዳር መጠለያነት መፍቀድ (ድንገተኛ ሁኔታዎች ካልሆነ በቀር፤ 35.5.4 ይመልከቱ)።

  • ካምፕ ወይም እዚያው ማደርን የሚያካትቱ ሌሎች አክቲቪቲዎች።

የሚከተሉት አጠቃቀሞች በአጠቃላይ አይፈቀዱም። የቅርብ የአካባቢ መሪዎች በተለየ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ነገር እንዳለ ከተሰማቸው የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪን ያነጋግራሉ።

  • የቤተክርስቲያኗ ሕንፃዎችን እና ንብረቶችን ማከራየት ወይም በሊዝ እንዲያዙ ማድረግ።

  • ንብረቶችን ለፖለቲካ ድምፅ ሰጪዎቸ መመዝገቢያ ወይንም እንደ ምርጫ ጣቢያ መጠቀም፤ ምክንያታዊ አማራጭ ከሌለ እና ዝግጅቱ የቤተክርስቲያኗን ገፅታ ወይም ያላትን ገለልተኛ አቋም የማይጎዳ ከሆነ በመንግስት ባለስልጣናት ጥያቄ ሲቀርብ በልዩ ሁኔታ ሊታይ ይችላል (38.8.30ን ይመልከቱ)።

35.5.4

ድንገተኛ ሁኔታዎች

ድንገተኛ ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአጥቢያ ወይም የካስማ ሥብሰባዎችን ማድረግ ያስፈልግ እንደሆነ ይወስናል። በተጨማሪም ሕንፃዎች እና የቤተክርስቲያኗ ንብረቶች በድንገተኛ አደጋ ድርጅቶች እና ተዛማጅ በሆኑ ጥረቶች ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሊፈቅድ ይችላል።

35.5.10

በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ወቅት ፎቶግራፍ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረፅ

ቅዱስ ቁርባን ሥብሰባዎች የተቀደሱ ናቸው። በዚህ ምክንያት ቅዱስ ቁርባን ስብሰዎችን ፎቶግራፍ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረፅ አይፈቀድም።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰዎችን እና ሌሎች ስብሰዎችን ስለማሰራጨት ወይም በቀጥታ ስለማስተላለፍ መረጃ ለማግኘት 29.7ን ይመልከቱ።