መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
38. የቤተክርስቲያን ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች


“38. የቤተክርስቲያን ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“38. የቤተክርስቲያን ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

38.

የቤተክርስቲያን ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች

38.1

የቤተክርስቲያን ተሳትፎ

የሰማይ አባታችን ልጆቹን ይወዳል። “ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው“ እንዲሁም “ከቸርነቱ ይካፈሉ ዘንድ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል“ (2 ኔፊ 26፥33)።

38.1.1

የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ተሳትፎ

ሁሉም በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ፣ በሌሎች የእሁድ ስብሰባዎች እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምታዘጋጃቸው ማህበራዊ ዝግጅቶች ላይ እንዲገኙ ይጋበዛሉ። የበላይ መሪው የሚሳተፉ ሁሉ ለቅዱስ ቦታው አክብሮት እንደሚያሳዩ የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።

ተሳታፊዎቹ ከአምልኮ ወይም ከሌሎች የስብሰባው ዓላማዎች ተቃራኒ የሆኑ መስተጓጎሎችን ወይም ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ማስወገድ አለባቸው። ለተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች የተቀመጡ ሁሉም የእድሜ እና የባህሪ መስፈርቶች መከበር አለባቸው። ይህም ከተጋነነ የፍቅር ስሜት መግለጫ ባህርይ እንዲሁም ትኩረትን ከሚከፋፍል አለባበስ ወይም አጋጌጥ መራቅን ይጠይቃል። እንዲሁም በአዳኙ ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎችን ሃሳብ በሚከፋፍል መልኩ ፖለቲካዊ መግለጫዎችን መስጠትን ወይም ስለጾታዊ ጉዳዮች ወይም ስለሌሎች የግል ባህሪያት መናገርን ይከለክላል።

ተገቢ ያልሆነ ባህሪ በሚፈጠር ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በፍቅር መንፈስ የግል ምክር ይሰጣሉ። ለዝግጅቱ ተገቢ ያልሆነ ባህርይ ያላቸው ሁሉ የሰማይ አባትን እና አዳኙን ለማምለክ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለተገኙት ሁሉ የተቀደሰ ቦታ እንዲኖር በመርዳት ላይ እንዲያተኩሩ ያበረታታል።

የቤተክርስቲያኗ መሰብሰቢያ አዳራሾች በቤተክርስቲያኗ ፖሊሲዎች የሚተዳደሩ የግል ንብረት ናቸው። እነዚህን መመሪያዎች ለመከተል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች የቤተክርስቲያን ስብሰባዎችን እና ዝግጅቶችን እንዳይሳተፉ በአክብሮት ይጠየቃሉ።

38.2

የሥርዓቶች እና የበረከቶች ፖሊሲዎች

ስለሥርዓቶች እና በረከቶች የሚገልፅ አጠቃላይ መረጃ በምዕራፍ 18 ውስጥ ቀርቧል። ስለቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚገልፅ መረጃ በምዕራፍ 27 እና28 ውስጥ ቀርቧል። ኤጲስ ቆጶሳት ጥያቄዎች ካሏቸው የካስማ ፕሬዘደንቱን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። የካስማ ፕሬዚዳንቶች ጥያቄዎች ካሏቸው የዋና አካባቢ አመራርን ሊያነጋግሩ ይችላሉ።

38.3

በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻ

የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ አባላት ለቤተመቅደስ ጋብቻ ብቁ እንዲሆኑ እንዲሁም እንዲጋቡ እና እንዲታተሙ ያበረታታሉ። ሆኖም በአካባቢው ህግ የሚፈቀድ ከሆነ በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ።

በመዘጋጃ ቤት የሚፈጸሙ ጋብቻዎች በሚፈጸሙባቸው ቦታዎች ባሉት ሕጎች መሠረት መከናወን አለባቸው።

38.3.1

በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻን ማን ሊፈፅም ይችላል

በአካባቢው ህግ ሲፈቀድ፣ በወቅቱ በማገልገል ላይ ያሉ የሚከተሉት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶችን ለማከናወን በጥሪያቸው ሊጠቀሙ ይችላሉ፦

  • የሚስዮን ፕሬዚዳንት

  • የካስማ ፕሬዚዳንት

  • የአውራጃ ፕሬዚዳንት

  • ኤጲስ ቆጶስ

  • የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት

እነዚህ ሃላፊዎች በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻን ሊፈፅሙ የሚችሉት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ ነው። የሚከተሉት ሁኔታዎች በሙሉ መሟላትም አለባቸው፦

  • ሙሽሪቷ ወይም ሙሽራው የቤተክርስቲያኗ አባል ከሆኑ ወይም ለመጠመቅ ቀን የቆረጡ ከሆኑ።

  • የሙሽራዋ ወይም የሙሽራው የአባልነት መዝገብ አሁን ወይም ከጥምቀቱ በኋላ የበላይ መሪው በሚመራበት የቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ የሚሆን ከሆነ።

  • የቤተክርስቲያኗ መሪ ጋብቻው በሚፈጸምበት ቦታ ህግ በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻን ለመፈፀም ህጋዊ ፈቃድ ያለው ከሆነ።

38.3.4

በቤተክርስቲያን ህንጻዎች ውስጥ በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻ

የቤተክርስቲያኗን መደበኛ ተግባራት ካላስተጓጎለ የሠርግ ሥነ ሥርዓት በቤተክርስቲያኗ ሕንፃ ውስጥ ሊደረግ ይችላል። የሠርግ ሥነ ሥርዓት በሰንበት ቀን ወይም ሰኞ ምሽት መካሄድ የለበትም። በቤተክርስቲያኗ ሕንፃ ውስጥ የሚደረግ የሠርግ ሥነ ሥርዓት መጠነኛ እና ክብሩን የጠበቀ መሆን አለበት። ሙዚቃው ቅዱስ፣ ጥልቅ አክብሮት የተመላበት እና አስደሳች መሆን አለበት።

የጋብቻ ሥነ ሥርዓቶች በጸሎት ቤት፣ በባህል አዳራሽ ወይም በሌላ ተስማሚ ክፍል ሊከናወኑ ይችላሉ። ሠርጎች የመሰብሰቢያ አዳራሹን በአግባቡ ለመጠቀም የወጡትን መመሪያዎች መከተል አለባቸው።

38.3.6

በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻ ሥነ ስርዓት

በማዘጋጃ ቤት ሹም አማካኝነት የሚፈጸም ጋብቻ ሲካሄድ፣ የቤተክርስቲያኗ መሪ ባልና ሚስቱን በስም ይጠራቸውና “እባካችሁ በቀኝ እጃችሁ ተያያዙ“ ይላል። ከዚያም እንዲህ ይላል፣ “[የሙሽራው ሙሉ ስም] እና [የሙሽራዋ ሙሉ ስም]፣ እርስ በርሳችሁ በቀኝ እጃችሁ የተያያዛችሁት በእግዚአብሔር እና በእነዚህ ምስክሮች ፊት አሁን ስለምትገቡት መሃላ ምልክት እንዲሆን ነው።“ (ጥንዶቹ እነዚህን ምስክሮች አስቀድመው ሊመርጡ ወይም ሊሾሙ ይችላሉ።)

መሪው ሙሽራውን በስም ይጠራውና እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፣ “[የሙሽራው ሙሉ ስም]፣ [የሙሽራዋ ሙሉ ስም] በገዛ ፈቃድህ እና ምርጫህ እንደጓደኛዋ እና ህጋዊ ባሏ ከእርሷ ጋር እንጂ ከሌላ ከማንም ጋር የማትቆራኝ፤ ቅዱስ ጋብቻን የተመለከቱ ሁሉንም ህጎች፣ ኃላፊነቶች እና ግዴታዎች የምትጠብቅ እና ሁለታችሁም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ የምትወዳት፣ የምታከብራት እና የምትንከባከባት ህጋዊ ሚስትህ አድርገህ ትቀበላታለህ?”

ሙሽራው “አዎ” ወይም “አዎ እቀበላታለሁ” በማለት ይመልሳል።

መሪው ሙሽራዋን በስም ይጠራትና እንዲህ ሲል ይጠይቃታል፣“[የሙሽራዋ ሙሉ ስም]፣ [የሙሽራው ሙሉ ስም] በገዛ ፈቃድሽ እና ምርጫሽ እንደጓደኛ እና ህጋዊ ሚስቱ ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ከማንም ጋር የማትቆራኚ፤ ቅዱስ ጋብቻን የተመለከቱ ሁሉንም ህጎች፣ ኃላፊነቶች እና ግዴታዎች የምትጠብቂ እና ሁለታችሁም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ የምትወጂው፣ የምታከብሪው እና የምትንከባከቢው ህጋዊ ባልሽ አድርገሽ ትቀበይዋለሽ?”

ሙሽራዋ “አዎ” ወይም “አዎ እቀበለዋለሁ” በማለት ትመልሳለች።

መሪው ጥንዶቹን በስም ይጠራና እንዲህ ይላል፣ [የሙሽራው ሙሉ ስም] እና [የሙሽራዋ ሙሉ ስም] የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሽማግሌ በመሆኔ በተሰጠኝ ህጋዊ ስልጣን መሰረት፣ በምድር ህይወታችሁ ሁሉ በህግ የተጋባችሁ ህጋዊ ባል እና ሚስት ናችሁ እላችኋለሁ።”

(በቤተክርስቲያኗ የበላይ መሪ ሆኖ ለማያገለግል ካህን አማራጭ አባባል፦ [የሙሽራው ሙሉ ስም] እና [የሙሽራዋ ሙሉ ስም] [የወታደራዊ ቅርንጫፍ ወይም የግል ድርጅት] ካህን በመሆኔ በተሰጠኝ ህጋዊ ስልጣን መሰረት፣ በምድር ህይወታችሁ ሁሉ በህግ የተጋባችሁ ህጋዊ ባል እና ሚስት ናችሁ እላችኋለሁ።”)

“እግዚአብሔር ጥምረታችሁ በዘራችሁ ውስጥ የደስታ እንዲሆን እና አንድ ላይ ረጅም የደስታ ዘመን እንዲኖራችሁ ይባርካችሁ እንዲሁም ቃል የገባችሁትን ቅዱስ መሃላ እንድትጠብቁ ይባርካችሁ። እነዚህን በረከቶች ለእናንተ የምለምነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

እንደ ባልና ሚስት እንዲሳሳሙ የሚደረገው ግብዣ በባህላዊ ደንቦች ላይ የተመሰረተ የምርጫ ጉዳይ ነው።

38.4

የእትመት ፖሊሲ

አባላት ሥርዓቶችን በተቀበሉ ጊዜ የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ ሲጥሩ የቤተመቅደስ እትመት ቤተሰቦችን ለዘለዓለም ያጣምራል። የእትመት ሥርዓቶች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • የባል እና የሚስት እትመት

  • ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር ማተም

ቃል ኪዳኖቻቸውን የሚጠብቁ ሲታተሙ የተሰጧቸውን የግለሰብ በረከቶች ይቀበላሉ። የትዳር ጓደኛ ቃል ኪዳንን ወይም ትዳርን ቢያፈርስም ይህ እውነት ነው።

ከወላጆቻቸው ጋር የታተሙ ወይም በቃል ኪዳኑ ውስጥ የተወለዱ ታማኝ ልጆች ዘለዓለማዊ የወላጅነት በረከት ይኖራቸዋል። ወላጆቻቸው የጋብቻ እትመታቸውን ቢሰርዙም፣ ከቤተክርስቲያኗ አባልነታቸው ቢወገዱም ወይም ከአባልነታቸው በፈቃዳቸው ቢለቁም ይህ እውነት ነው።

አባላት ስለእትመት ፖሊሲዎች ጥያቄዎች ካሏቸው ከኤጲስ ቆጶሳቸው ጋር መማከር ይኖርባቸዋል። ኤጲስ ቆጶሱ ጥያቄዎች ካሉት የካስማ ፕሬዘደንቱን ሊያነጋግር ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቶች ጥያቄዎች ካሏቸው በቤተመቅደስ አውራጃቸው ያለውን የቤተመቅደስ አመራር፣ የዋና አካባቢ አመራር ወይም የቀዳሚ አመራር ቢሮ ማነጋገር ይችላሉ።

38.5

በቤተመቅደስ ከላይ የሚለበሱ ልብሶች እና የቤተመቅደስ ልብሶች

38.5.1

በቤተመቅደስ ከላይ የሚለበሱ ልብሶች

የቤተክርስቲያን አባላት የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ እና የእትመት ሥርዓቶችን በሚከናወኑበት ጊዜ ነጭ ልብስ ይለብሳሉ። ሴቶች የሚከተሉትን ነጭ ልብሶች ይለብሳሉ፦ ረጅም እጅጌ ያለው ወይም እጅጌው ሶስት አራተኛ ርዝመት ያለው ቀሚስ (ወይም ረዥም ጉርድ ቀሚስና ረጅም እጅጌ ያለው ወይም እጅጌው ሶስት አራተኛ ርዝመት ያለው ሸሚዝ)፣ ካልሲ ወይም ስቶኪንግ እና ሽፍን ወይም ክፍት ጫማ።

ወንዶች የሚከተሉትን ነጭ ልብሶች ይለብሳሉ፦ ረጅም እጅጌ ያለው ሸሚዝ፣ ከረባት፣ ቢራቢሮ ከረባት፣ ሱሪ፣ ካልሲ እና ሽፍን ወይም ክፍት ጫማ።

የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ እና የእትመት ሥርዓቶችን በሚከናወኑበት ጊዜ አባላት በነጭ ልብሶቻቸው ላይ ተጨማሪ የሥነ ሥርዓት ልብሶችን ይለብሳሉ።

38.5.2

በቤተመቅደስ ከላይ የሚለበሱ ልብሶችን እና የቤተመቅደስ ልብሶችን ማግኘት

የአጥቢያ እና የካስማ መሪዎች አባላት የራሳቸውን የቤተመቅደስ ልብስ እንዲያገኙ ያበረታታሉ። በቤተመቅደስ ከላይ የሚለበሱ ልብሶችን እና የቤተመቅደስ ልብሶችን ከቤተክርስቲያኗ ማሰራጫ መጋዘን ወይም store.ChurchofJesusChrist.orgከ መግዛት ትችላላችሁ። የካስማ እና የአጥቢያ ጸኃፊዎች አልባሳትን በማዘዝ አባላትን ሊረዱ ይችላሉ።

38.5.5

የቤተመቅደስ ልብሶቹን መልበስ እና እንክብካቤ ማድረግ

የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ የተቀበሉ አባላት የቤተመቅደስ ልብሱን በህይወታቸው ሙሉ ለመልበስ ቃል ኪዳን ይገባሉ።

የቤተመቅደስ ልብስን መልበስ የተቀደሰ ዕድል ነው። ይህንን ማድረግ አዳኙን ኢየሱስ ክርስቶስን የመከተል ውስጣዊ ቆራጥነት ውጫዊ መገለጫ ነው።

የቤተመቅደስ ልብሶች በቤተመቅደስ የተገቡትን ቃል ኪደኖች አስታዋሾች ናቸው። በህይወት ሙሉ በጥንቃቄ ሲለበስ እንደ ጥበቃ ያገለግላል።

የቤተመቅደስ ልብሱ ከሌሎች ልብሶች ስር መለበስ አለበት። ሌሎች የውስጥ ልብሶችን በቤተመቅደስ ልብሱ ሥር ወይም ላይ መልበስ የግል ምርጫ ጉዳይ ነው።

የቤተመቅደስ ልብሱን በመልበስ ሊደረጉ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ልብሱ መውለቅ የለበትም። የተለያዩ የአለባበስ መንገዶችን ለመከተል ሲባል ልብሱ መስተካከል የለበትም።

የቤተመቅደስ ልብሱ የተቀደሰ ነው ስለዚህ በክብር መያዝ አለበት። የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ የተቀበሉ አባላት በቤተመቅደስ ልብስ አለባበስ ላይ ስላላቸው የግል ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የመንፈስ ቅዱስን ምሪት መሻት ይኖርባቸዋል።

38.5.7

የቤተመቅደስ ልብሶችን እና የቤተመቅደስ የሥነ ሥርዓት ልብሶችን ማሰወገድ

ያረጁ የቤተመቅደስ ልብሶችን ለማስወገድ አባላት ምልክቶቹን ቆርጠው ማውጣት እና ማጥፋት አለባቸው። ከዚያም አባላቱ የቀረውን ጨርቅ የቤተመቅደስ ልብስ መሆኑን መለየት እንዳይቻል አድርገው ይቀዳድዱታል። ቀሪው ጨርቅ ሊጣል ይችላል።

አባላት በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ የቤተመቅደስ ልብሶችን ለሌሎች የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለተቀበሉ አባላት ሊሰጡ ይችላሉ።

38.5.8

የቤተመቅደስ የቀብር ልብስ

ከተቻለ፣ የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበሉ አባላት ሲሞቱ የቤተመቅደስ ልብስ ለብሰው መቀበር ወይም መቃጠል አለባቸው። ባህላዊ ሥርዓቶች ወይም የቀብር ልማዶች ይህንን ተገቢ ያልሆነ ወይም አስቸጋሪ የሚያደርጉት ከሆነ ልብሱ ተጣጥፎ ከአስከሬኑ አጠገብ ሊቀመጥ ይችላል።

የወንዶች አሰከሬን የቤተመቅደስ ልብስ እና የሚከተሉትን ነጭ ልብሶች ይለብሳል፦ረጅም እጅጌ ያለው ሸሚዝ፣ ከረባት፣ ቢራቢሮ ከረባት፣ ሱሪ፣ ካልሲ እና ሽፍን ወይም ክፍት ጫማ። የሴቶች አሰከሬን የቤተመቅደስ ልብስ እና የሚከተሉትን ነጭ ልብሶች ይለብሳል፦ ረጅም እጅጌ ያለው ወይም እጅጌው ሶስት አራተኛ ርዝመት ያለው ቀሚስ (ወይም ረዥም ጉርድ ቀሚስና ረጅም እጅጌ ያለው ወይም እጅጌው ሶስት አራተኛ ርዝመት ያለው ሸሚዝ)፣ ካልሲ ወይም ስቶኪንግ እና ሽፍን ወይም ክፍት ጫማ።

በቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ ላይ እንደታዘዘው የቤተመቅደስ ሥነ ሥርዓት ልብስ በአስከሬኑ ላይ ይቀመጣል። መጎናጸፊያው በቀኝ ትከሻ ላይ ይቀመጣል እንዲሁም በግራ ወገብ ላይ ሸምቀቆ ይታሰራል። ሽርጡ ወገብ ላይ ይደረጋል። ማሰሪያው በወገብ ዙሪያ ይደረግና ግራ ዳሌ ላይ በሸምቀቆ ይታሰራል።። የሬሳ ሣጥኑ ወይም መያዣው እስኪዘጋ ድረስ የወንድ ኮፍያ ብዙውን ጊዜ በአስከሬኑ አጠገብ ይቀመጣል። ከዚያም ኮፍያው ከሸምቀቆው ጋር በግራ ጆሮ ላይ ይቀመጣል። የሴት ጭምብል ከጭንቅላቷ ጀርባ ትራስ ላይ ሊለብስ ይችላል። ከቀብር ወይም ከማቃጠል በፊት የሴትን ፊት በጭምብል መሸፈን በቤተሰቡ የሚወሰን የምርጫ ጉዳይ ነው።

38.6

የስነ ምግባር ጉዳዮችን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች

38.6.1

ፅንስ ማስወረድ

ጌታ ”አትግደል፣ ወይም እንዲህ ዓይነት ነገሮችን አታድርግ” ሲል አዟል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥6 ይመልከቱ)። ቤተክርስቲያኗ የግል ወይም ማህበራዊ ምቾትን ለመጠበቅ ሲባል የሚደረግ የተመረጠ ፅንስ ማስወረድን ትቃወማለች። አባላት ፅንስ ማስወረድ፣ ማከናወን፣ ማመቻቸት፣ መክፈል፣ እንዲደረግ መስማማት ወይም ማበረታታት የለባቸውም። ብቻኛ የተለዩ ሁኔታዎች የሚሆኑት፦

  • አስገድዶ በመደፈር ወይም የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚከሰት እርግዝና።

  • ብቃት ያለው ሐኪም የእናትየው ህይወት ወይም ጤና ከባድ አደጋ ላይ መሆኑን አስመልክቶ ሲወስን።

  • ብቃት ያለው ሐኪም ፅንሱ ከውልደት በኋላ በህይወት እንዳይቆይ የሚያደርጉ ከባድ ጉድለቶች እንዳሉበት ሲወስን።

እነዚህ የተለዩ ሁኔታዎች እንኳን ፅንስ ማስወረድን ወዲያውኑ ተገቢ አያደርጉትም። ፅንስ ማስወረድ በጣም አሳሳቢ ነገር ነው። ይህ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች በጸሎት ማረጋገጫ ካገኙ በኋላ ብቻ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ፣ አባላት ከኤጲስ ቆጶሳቸው ጋር ሊማከሩ ይችላሉ።

38.6.2

ጥቃት

ጥቃት ማለት አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ስሜታዊ ወይም የገንዘብ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል መንገድ ሌሎችን መያዝ ወይም ችላ ማለት ነው። ቤተክርስቲያኗ ማንኛውም ዓይነት መልክ ያለው ጥቃትን መታገስ አይቻልም የሚል አቋም አላት። በትዳር ጓደኞቻቸው፣ በልጆቻቸው፣ በሌሎች የቤተሰብ አባሎቻቸው ወይንም በማንኛውንም ሌላ ሰው ላይ ጥቃት የሚያደርሱ የእግዚአብሔርን እና የሰውን ህግ ይጥሳሉ።

ሁሉም አባላት፣ በተለይም ወላጆች እና መሪዎች፣ ልጆችን እና ሌሎችን በንቃት እና በትጋት ከጥቃት ለመጠበቅ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። አባላት አንድ ሰው ጥቃት እንደደረሰበት ካወቁ፣ ጥቃቱን ለአካባቢው የህግ አካላት ያሳውቃሉ እንዲሁም ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ይማከራሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች የጥቃት ሪፖርቶችን በቁም ነገር መውሰድ አለባቸው እንዲሁም ፈፅሞ ችላ ሊሏቸው አይገባም።

ከልጆች ወይም ከወጣቶች ጋር የሚሰሩ ጎልማሶች ሁሉ ድጋፍ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ አለባቸው ( ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ)። ሥልጠናውን በየሶስት ዓመቱ መድገም ይኖርባቸዋል።

ጥቃት ሲከሰት፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የመጀመሪያ እና አፋጣኝ ሀላፊነት ጥቃት የደረሰባቸውን መርዳት እንዲሁም ተጋላጭ ሰዎችን ወደፊት ሊደርስ ከሚችል ጥቃት መጠበቅ ነው። መሪዎች አንድን ሰው ጥቃት ባለበት ወይም ደህንነት ላይ ችግር ሊያስከትል በሚችል ቤት ውስጥ እንዲቆይ ማበረታታት የለባቸውም።

38.6.2.1

የጥቃት እርዳታ የስልክ መስመር

በአንዳንድ አገሮች፣ ቤተክርስቲያኗ የካስማ ፕሬዘደንቶችን እና ኤጲስ ቆጶሳትን ለመርዳት ሚስጥራዊ የጥቃት እርዳታ የስልክ መስመር አዘጋጅታለች። እነዚህ መሪዎች አንድ ሰው ጥቃት ደርሶበት ከሆነ ወይም ጥቃት ሊደርስበት የሚችልበት ሥጋት እንዳለ ሲያውቁ ወዲያውኑ ወደ እርዳታ የስልክ መስመሩ መደወል አለባቸው። እንዲሁም አንድ አባል የልጆች የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም እንደሚመለከት፣ እንደሚገዛ ወይም እንደሚያሰራጭ ካወቁ ወደዚህ ቁጥር መደወል አለባቸው።

የእርዳታ የስልክ መስመር በሌለባቸው አገሮች፣ጥቃት እየተፈጸመ እንደሆነ ያወቀ ኤጲስ ቆጶስ የካስማ ፕሬዘደንቱን ማነጋገር አለበት። የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዋና አካባቢ ቢሮው ካለው የአካባቢ የሕግ አማካሪ መመሪያ መጠየቅ ይገባዋል።

38.6.2.2

ጥቃት በሚፈጸም ጊዜ የሚሰጥ ምክር

የጥቃት ሰለባዎች ብዙውን ጊዜ ከባድ የሥሜት ቀውስ ይደርስባቸዋል። የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት ልባዊ በሆነ ርህራሄ ምላሽ ይሰጣሉ። ጥቃቱ ያስከትለውን አፍራሽ ውጤት እንዲቋቋሙ ለመርዳት መንፈሳዊ ምክር እና ድጋፍ ይሰጣሉ።

አንዳንድ ጊዜ ተጠቂዎች የሃፍረት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። ተጠቂዎች የኃጢአት ጥፋተኝነት የለባቸውም። መሪዎች፣ እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት የሚመጣውን ፈውስ እንዲገነዘቡ ይረዷቸዋል (አልማ 15፥83 ኔፊ 17፥9 ይመልከቱ)።

የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት ጥቃት የፈጸሙ ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ እና ጥቃት የመፈጸም ባህርያቸውን እንዲያቆሙ መርዳት አለባቸው። አንድ ጎልማሳ በአንድ ልጅ ላይ ወሲባዊ ኃጢያት ከሠራ ይህንን ባህርይ መለወጥ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል። የንስሐ ሂደቱ በጣም ረጅም ሊሆን ይችላል። 38.6.2.3 ይመልከቱ።

የቤተክርስቲያኗ መሪዎች፣ የጥቃት ሰለባዎች፣ ወንጀለኞች እና ቤተሰቦቻቸው በመንፈስ አነሳሽነት ከሚገኝ እርዳታ በተጨማሪ ሙያዊ ምክር ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ለመረጃ 31.3.6 ይመልከቱ።

38.6.2.3

የልጆች ወይም የወጣቶች ጥቃት

የልጆች ወይም የወጣቶች ጥቃት በተለይ ከባድ ሃጢያት ነው (Luke 17፥2 ይመልከቱ)። በዚህ አጠቃቀም መሰረት፣ የልጆች ወይም የወጣቶች ጥቃት የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • አካላዊ ጥቃት፦ በሃይል ጥቃት ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ። አንዳንድ ጉዳቶች ላይታዩ ይችላሉ።

  • ጾታዊ ጥቅት ወይም ብዝበዛ፦ ከአንድ ልጅ ወይም ወጣት ጋር ማንኛውንም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ወይም ሆን ብሎ ሌሎች በእንደዚህ ዓይነት ተግባር እንዲሳተፉ መፍቀድ ወይም መርዳት። በዚህ አጠቃቀም መሰረት፣ ፆታዊ ጥቃት በእድሜ ተቀራራቢ በሆኑ ሁለት ታዳጊዎች መካከል በስምምነት የሚደረግን የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አያካትትም።

  • ሥሜታዊ ጥቃት ልጆች ወይም ወጣቶች ለራሳቸው የሚሰጡትን ክብር ወይም ዋጋ በእጅጉ የሚጎዱ ድርጊቶችን እና ቃላትን መጠቀም። ይህ ዘወትር ተደጋጋሚ የሆኑ እና ቀጣይነት ያላቸው ስድቦችን፣ በዘዴ ጎጂ ተፅዕኖዎችን ማድረግን እንዲሁም የሚያዋርዱ እና ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉ ትችቶችን ይጨምራል። እንክብካቤ ማጓደልን ሊጨምርም ይችላል።

  • የልጆች የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም፦ 38.6.6 ይመልከቱ።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ እንደሆነ ካወቀ ወይም ከጠረጠረ በአፋጣኝ በ 38.6.2.1 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል። እንዲሁም ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል የሚረዳ እርምጃ ይወስዳል።

አንድ ጎልማሳ አባል በአንድ ልጅ ወይም ወጣት ላይ ጥቃት ያደረሰ ከሆነ፣ የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ እና በመዝገብ ላይ ማብራሪያ ማስፈር ያስፈልጋል። በተጨማሪም 38.6.2.5 ይመልከቱ።

አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ በአንድ ልጅ ላይ ጥቃት ካደረሰ የካስማ ፕሬዘደንቱ መመሪያ ለማግኘት የቀዳሚ አመራርን ያነጋግራል።

38.6.2.4

በትዳር ጓደኛ ወይም በሌላ ጎልማሳ ላይ ጥቃት ማድረስ።

ብዙውን ጊዜ ለሁሉም ሁኔታዎች ሊሰራ የሚችል አንድ ዓይነት የጥቃት ትርጓሜ የለም። ከዚያ ይልቅ የማጥቃት ባህሪ የክብደት ደረጃ አለው። ይህ የጥቃት ባህርይ ደረጃ አልፎ አልፎ ጎጂ ቃላትን ከመጠቀም አንስቶ ከባድ ጉዳት እስከማድረስ ሊሄድ ይችላል።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት በአንድ የትዳር ጓደኛ ወይም በሌላ ጎልማሳ ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ ካወቀ ወይም ከጠረጠረ በአፋጣኝ በ38.6.2.1 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል። እንዲሁም ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል የሚረዳ እርምጃ ይወስዳል።

መሪዎች ጥቃትን ለመፍታት ከግል ምክር እና የአባልነት ምክር ቤትን ከማካሄድ የትኛው በጣም ትክክለኛው ሁኔታ እንደሆነ ለመወሰን የመንፈስን ምሪት ይሻሉ። ስለሁኔታው ከቅርብ የክህነት መሪያቸው ጋር ሊመክሩም ይችላሉ። ሆኖም ከዚህ በታች በተገለጹት ደረጃዎች በትዳር ጓደኛ ላይ ወይም በሌላ ጎልማሳ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ዓይነት ጥቃት የአባልነት ምክር ቤት ማድረግን ይጠይቃል።

  • አካላዊ ጥቃት፦ በሃይል ጥቃት ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ። አንዳንድ ጉዳቶች ላይታዩ ይችላሉ።

  • ጾታዊ ጥቃት38.6.18.3 ውስጥ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ይመልከቱ

  • ሥሜታዊ ጥቃት ልጆች ወይም ወጣቶች ለራሳቸው የሚሰጡትን ክብር ወይም ዋጋ በእጅጉ የሚጎዱ ድርጊቶችን እና ቃላትን መጠቀም። ይህ ዘወትር ተደጋጋሚ የሆኑ እና ቀጣይነት ያላቸው ስድቦችን፣ በዘዴ ጎጂ ተፅዕኖዎችን ማድረግን እንዲሁም የሚያዋርዱ እና ዝቅ ዝቅ የሚያደርጉ ትችቶችን ይጨምራል።

  • ገንዘብ ነክ ጥቃት አንድን ሰው በገንዘብ መጠቀሚያ ማድረግ። ይህ የአንድን ሰው ንብረት፣ ገንዘብ ወይም ሌሎች ውድ ንብረቶች ህገወጥ በሆነ መንገድ ወይም ያለፈቃድ መጠቀምን ሊያካትት ይችላል። እንዲሁም፣ በማጭበርበር በአንድ ሰው ላይ የገንዘብ ኃይል ማግኘትን ሊያካትትም ይችላል። ባህርይን በድግ ለማስቀየር የገንዘብን ሃይል መጠቀምን ሊያካትት ይችላል።

38.6.2.5

የቤተክርስቲያን ጥሪዎች፣ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እና የአባልነት መዝገብ ማብራሪያዎች

በሌሎች ላይ ጥቃት ያደረሱ አባላት ንስሃ እስኪገቡ እና የቤተክርስቲያኗ የአባልነት እገዳዎች እስኪነሱላቸው ድረስ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች ሊሰጧቸው አይገባም እንዲሁም የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ አይኖራቸውም።

አንድ ግለሰብ በአንድ ልጅ ወይም ወጣት ላይ ፆታዊ ጥቃት ከፈጸመ ወይም በአንድ ልጅ ወይም ወጣት ላይ ከባድ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት ካደረሰ በአባልነት መዝገቡ ላይ ማብራሪያ ይጻፋል። እሱ ወይም እሷ ልጆችን እና ወጣቶችን የሚያካትት ጥሪም ሆነ የስራ ምደባ ሊሰጣቸው አይገባም። ይህ በቤት ውስጥ ወጣቶች ወይም ልጆች ላለው ቤተሰብ የአገልግሎት የስራ ምደባ አለመሰጠትን ይጨምራል። ይህ ከአንድ ከወጣት ጋር የአገልግሎት ጓደኛ አለመደረግንም ይጨምራል። ቀዳሚ አመራር ማብራሪያው እንዲወገድ ካልፈቀደ በስተቀር እነዚህ ገደቦች አይነሱም።

38.6.2.6

የካስማ እና የአጥቢያ ምክር ቤቶች

የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት ጥቃትን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት በካስማ እና በአጥቢያ የምክር ቤት ሥብሰባዎች ላይ የቤተክርስቲያኗን ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች በየጊዜው ይገመግማሉ። መሪዎች እና የምክር ቤት አባላት ስለዚህ ጥንቃቄ የሚያሻው ጉዳይ ሲያስተምሩ እና ሲወያዩ የመንፈስን መመሪያ ይሻሉ።

የምክር ቤት አባላትም የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ሥልጠናን ማጠናቀቅ አለባቸው (38.6.2 ይመልከቱ)።

38.6.2.7

ከጥቃት ጋር የተያያዙ የህግ ጉዳዮች

አንድ አባል ያደረሳቸው የጥቃት ድርጊቶች ያለውን ህግ የሚጥሱ ከሆኑ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እነዚህን እንቅስቃሴዎች ለህግ አካላት ወይም አግባብነት ላላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እንዲያሳውቅ አባሉን ማሳሰብ አለበት።

የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላት ጥቃትን ለመንግሥት ባለስልጣናት ሪፖርት ለማድረግ ሁሉንም ህጋዊ ግዴታዎች መወጣት አለባቸው።

38.6.4

የወሊድ መቆጣጠሪያ

ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ ልጆች ሥጋዊ አካልን የመስጠት መብት ልጆች መውለድ የሚችሉ ጥንዶች ያላቸው ዕድል ነው፤ ከዚያም እነሱን የመንከባከብ እና የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው (2.1.3 ይመልከቱ)። ምን ያህል ልጆች እንደሚወልዱ እና መቼ እንደሚወልዱ የሚያደርጉት ውሳኔ ለግለሰቦች የተተው እና የግል ጉዳዮች ናቸው። ለጥንዶቹ እና ለጌታ የሚተው መሆን አለበት።

38.6.5

ንፅህና እና ታማኝነት

የጌታ የንፅህና ህግ እንዲህ ነው፦

  • በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ካለው ሕጋዊ ጋብቻ ውጭ ከሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መታቀብ።

  • በትዳር ውስጥ ታማኝነት።

በባልና በሚስት መካከል ያለው አካላዊ መቀራረብ ያማረ እና የተቀደሰ እንዲሆን የታሰበ ነው። ይህም ልጆችን ለመፍጠር እንዲሁም በባልና በሚስት መካከል ያለን ፍቅር ለመግለፅ በእግዚአብሔር የታዘዘ ነው።

38.6.6

የልጆች የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም

ቤተክርስቲያኗ በማንኛውም መልኩ የልጆች የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስልን ወይም ፊልምን ታወግዛለች። አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት፣ አንድ አባል የልጆች የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስልን ወይም ፊልምን በመመልከት እንደተሳተፈ ካወቀ በአፋጣኝ በ 38.6.2.1 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

38.6.8

የሴት ልጅ ግርዛት

ቤተክርስቲያኗ የሴት ልጅ ግርዛትን ታወግዛለች።

38.6.10

የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት

ቤተክርስቲያኗ ማንኛውንም የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ታወግዛለች። በዚህ አጠቃቀም መሰረት፣ የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማለት በሚከተሉት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማለት ነው፦

  • በወላጅ እና ልጅ።

  • በአያት እና በልጅ ልጅ።

  • በወንድም እና በእህት።

  • በአጎት ወይም በአክስት እና በእህት ወንድ/ሴት ልጅ ወይም በወንድም ወንድ/ሴት ልጅ።

በዚህ አጠቃቀም መሰረት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ ወንድምና እህት፣ የእህት ሴት ልጅ ወይም የወንድም ሴት ልጅ፣ እንዲሁም የእህት ወንድ ልጅ ወይም የወንድም ወንድ ልጅ ስጋዊ፣ የጉዲፈቻ፣ የእንጀራ ወይም የማደጎ ግንኙነቶችን ይጨምራል።

ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጥቃት ሲደርስበት ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የቤተክርስቲያኗን የጥቃት የእርዳታ መስመር(ካለ) ይደውላል (38.6.2.1ን ይመልከቱ)። በሌሎች አገራት የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዋና አካባቢ ቢሮ ካለው የአካባቢ የሕግ አማካሪ መመሪያ መጠየቅ አለበት። እንዲሁም በዋና አካባቢ ቢሮ ካለው የቤተሰብ አገልግሎቶች ሠራተኛ ወይም የበጎ አድራጎት እና ራስን መቻል ሥራ አስኪያጅ ጋር እንዲማከር ይበረታታል።

አንድ አባል የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመ ከሆነ የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ እና በመዝገብ ላይ ማብራሪያ ማስፈር ያስፈልጋል። የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን መፈጸም ሁልጊዜ ቤተክርስቲያኗ ግለሰብን ከአባልነት እንድታስወግድ ያደርጋታል።

ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈጸመ ከሆነ የካስማ ፕሬዚዳንቱ መመሪያ ለማግኘት የቀዳሚ አመራርን ያነጋግራል።

የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ተጠቂዎችብዙውን ጊዜ ከባድ የሥሜት ቀውስ ይደርስባቸዋል። መሪዎች ልባዊ በሆነ ርህራሄ ምላሽ ይሰጣሉ። የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነትጥቃት ያስከተለውን አፍራሽ ውጤት እንዲቋቋሙ ለመርዳት መንፈሳዊ ምክር እና ድጋፍ ይሰጣሉ።

አንዳንድ ጊዜ ተጠቂዎች የሃፍረት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። ተጠቂዎች የኃጢአት ጥፋተኝነት የለባቸውም። መሪዎች፣ እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት የሚመጣውን ፈውስ እንዲገነዘቡ ይረዷቸዋል(አልማ 15፥83 ኔፊ 17፥9ን ይመልከቱ)።

የጥቃት ሰለባዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች በመንፈስ አነሳሽነት ከሚቀበሉት እርዳታ በተጨማሪ ሙያዊ ምክር ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ለመረጃ 38.6.18.2. ይመልከቱ።

38.6.12

መናፍስታዊ የአምልኮ ሥርዓቶች

መናፍስታዊ የአምልኮ ሥርዓት በጨለማ ላይ ያተኩራል እንዲሁም ወደ መታለል ይመራል። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት ያጠፋል።

መናፍስታዊ የአምልኮ ሥርዓት የሰይጣን አምልኮን ያካትታል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ጋር የማይስማሙ ሚሥጥራዊ ተግባራትንም ያካትታል። እንደነዚህ አይነት ተግባራት ከእግዚአብሔር የክህነት ስልጣን ሃይል የተኮረጁትን ሟርተኝነትን፣ እርግማንን እና የፈውስ ድርጊቶችን (ነገር ግን በዚህ ብቻ አይገደቡም) ያካትታሉ (ሞሮኒ 7፥11–17 ይመልከቱ)።

የቤተክርስቲያን አባላት በማንኛውም መልኩ በሰይጣን አምልኮ ውስጥ መሳተፍ ወይም በምንም መንገድ በመናፍስታዊ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ መሳተፍ የለባቸውም። ንግግሮች ወይም የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች እንደዚህ ባለው ጨለማ ላይ ማተኮር የለባቸውም።

38.6.13

የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም

ቤተክርስቲያኗ በማንኛውም መልክ ያለውን የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም ታወግዛለች። ማንኛውንም ዓይነት የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም መጠቀም የግለሰብን ሕይወት፣ ቤተሰብን እና ማህበረሰብን ይጎዳል። የጌታን መንፈስንም ያርቃል። የቤተክርስቲያን አባላት ማንኛውንም ዓይነት የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም ማስወገድ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ዝግጅቱን፣ ስርጭቱን እና ጥቅም ላይ መዋሉን መቃወም አለባቸው።

አንድ ሰው የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም በመጠቀሙ ምክንያት ንስሃ እንዲገባ እርዳታ በሚሰጠው ጊዜ የግል ምክር መስጠት እና መደበኛ ያልሆነ የአባልነት እገዳ መጣል በቂ ነው። በተለምዶ የአባልነት ምክር ቤት አይካሄዱም። ሆኖም በአባሉ ትዳር ወይም ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም በከፍተኛ ደረጃ ወይም በአስገዳጅ ሁኔታ ለሚጠቀም ምክር ቤት ማካሄድ ሊያስፈልግ ይችላል (38.6.5 ን ይመልከቱ)። አንድ አባል የልጆችን የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ምስል ወይም ፊልም የሚያዘጋጅ፣ የሚያከፋፍል፣ የሚይዝ ወይም ደጋግሞ የሚመለከት ከሆነ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል (38.6.6 ን ይመልከቱ)።

38.6.14

ጭፍን ጥላቻ

ሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ሁሉም የእርሱ መለኮታዊ ቤተሰብ የሆኑ ወንድሞች እና እህቶች ናቸው(“ቤተሰብ፦ ለዓለም የተላለፈ ዓዋጅ” ይመልከቱ)። እግዚአብሔር “የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ” (የሐዋሪያት ሥራ 17፥26)። “ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው“ (2 ኔፊ 26፥33)። “አንዱ ፍጡር እንደሌላው በፊቱ የከበረ ነው” (ያዕቆብ 2፥21)።

ጭፍን ጥላቻ ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ጋር አብሮ አይሄድም። በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ሞገስ ወይም አለመወደድ ለእርሱ እና ለትዕዛዛቱ ባለ ቁርጠኝነት ላይ እንጂ በቆዳ ቀለም ላይ የተመካ አይደለም።

ቤተክርስቲያኗ ሁሉም ሰዎች በማንኛውም ቡድን ወይም ግለሰብ ላይ ያላቸውን የጭፍን ጥላቻ አመለካከት እና ድርጊት እንዲተዉ አጥብቃ ትጠይቃለች። የቤተክርስቲያኗ አባላት ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ክብርን በማሳየት ረገድ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው። አባላት ሌሎችን እንዲወዱ አዳኙ የሰጠውን ትእዛዝ ይከተላሉ (ማቴዎስ 22፥37-39 ን ይመልከቱ)። ማንኛውንም ዓይነት ጭፍን ጥላቻ በማስወገድ ለሁሉም የወዳጅነት ስሜት ያላቸው ለመሆን ይጥራሉ። ይህ በዘር፣ በብሄር፣ በዜግነት፣ በጎሳ፣ በፆታ፣ በእድሜ፣ በአካል ጉዳተኝነት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ፣ በሃይማኖታዊ እምነት ወይም አለማመን እንዲሁም በወሲብ መስህብ ላይ የተመሰረተ ጭፍን ጥላቻን ይጨምራል።

38.6.15

የተመሳሳይ ፆታ መስህብ እና የተመሳሳይ ጾታ ባህሪ

ቤተሰቦች እና አባላት ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሰዎች የሚሳቡ ሰዎችን በጥንቃቄ፣ በፍቅር እና በአክብሮት እንዲረዱ ቤተክርስቲያኗ ታበረታታለች። ቤተክርስቲያኗ በአጠቃላይ ህብረተሰብ ውስጥ ስለደግነት፣ ስለማካተት፣ ለሌሎች ፍቅር እና ለሰው ልጆች ሁሉ አክብሮት ስለመስጠት ያሏትን ትምህርቶች የሚያንፀባርቅ ግንዛቤን በማስፋፋት ትጠቀማለች። ቤተክርስቲያኗ በተመሳሳይ ጾታ መስህብ ምክንያቶች ላይ አቋም አትወስድም።

የእግዚአብሔር ትዕዛዛት በተቃራኒ ጾታ መካከልም ሆነ በተመሳሳይ ጾታ መካከል ያለ ማንኛውንም ንፅህና የጎደለው ባህርይ ይከለክላሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች የንፅህናን ህግ ላፈረሱ አባላት ምክር ይለግሳሉ። መሪዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ላይ ስለማመን፣ ስለንስሃ ሂደት እና በምድር ላይ ስላለው የህይወት አላማ ግልፅ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዷቸዋል።

አባላት የተመሳሳይ ፆታ መስህብ ከተሰማቸው እና የንፅህና ህግን ለመኖር እየጣሩ ከሆነ መሪዎች ውሳኔያቸውን ይደግፋሉ እንዲሁም ያበረታቷቸዋል። እነዚህ አባላት የቤተክርስቲያን ጥሪዎችን ሊቀበሉ፣ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ሊያገኙ እና ብቁ ከሆኑ የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ሊቀበሉ ይችላሉ። ወንድ የቤተክርስቲያን አባላት ክህነትን ሊቀበሉ እና ሊጠቀሙ ይችላሉ።

ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ አባላት ሁሉ በዚህ ህይወት ውስጥ የዘለዓለማዊ ጋብቻ እና የወላጅነት በረከቶችን ለመቀበል ሁኔታቸው ቢፈቅድላቸውም ባይፈቅድላቸውም ሁሉንም ቃል የተገባላቸውን በረከቶች በዘለዓለማዊ ህይወት ያገኛሉ (ሞዛያ 2፥41ን ይመልከቱ)።

38.6.16

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ

በቅዱሳት መጻህፍት ላይ እንደተመሰረተ የትምህርት መርህ፣ ቤተክርስቲያኗ በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ ፈጣሪ ለልጆቹ ላለው የዘለዓለማዊ እጣ ፈንታ ዕቅድ አስፈላጊ መሆኑን ታረጋግጣለች። በተጨማሪም፣ ጋብቻ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረግ ህጋዊ እና በህጋዊ መንገድ የተደረገ ጥምረት እንደሆነ የእግዚአብሔር ህግ እንደሚተረጉም ቤተክርስቲያኗ ታረጋግጣለች።

38.6.17

የሥነ-ተዋልዶ ትምህርት

ወላጆች በቀደምትነት ልጆቻቸውን የሥነ-ተዋልዶ ትምህርት የማስተማር ሀላፊነት አለባቸው። ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ስለጤናማና በፅድቅ ስለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት ታማኝ፣ ግልፅ እና ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ አለባቸው።

38.6.18

ጾታዊ ጥቃት፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች የወሲብ ትንኮሳ መልኮች

ቤተክርስቲያኗ ጾታዊ ጥቃትን ታወግዛለች። በዚህ አጠቃቀም መሰረት፣ ጾታዊ ጥቃት ማለት ማንኛውንም ያልተፈለገ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሌላ ሰው ላይ መጫን ማለት ነው። ህጋዊ ፈቃድ ካልሰጠ ወይም መስጠት ከማይችል ግለሰብ ጋር የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ፆታዊ ጥቃት ተደርጎ ይወሰዳል። ፆታዊ ጥቃት በትዳር ጓደኛ ወይም በመጠናናት ግንኙነት ውስጥም ሊከሰት ይችላል። ስለልጆች እና ወጣቶች ጾታዊ ጥቃት መረጃ ለማግኘት 38.6.2.3 ን ይመልከቱ።

ጾታዊ ጥቃት ከትንኮሳ እስከ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች የወሲብ ትንኮሳ መልኮችን የሚያካትቱ ሰፊ ድርጊቶችን ይሸፍናል። በአካል፣ በቃላት እና በሌሎች መንገዶች ሊከሰት ይችላል። ፆታዊ ጥቃት፣ አስገድዶ መደፈር ወይም ሌሎች የወሲብ ትንኮሳ መልኮች ለደረሰባቸው አባላት ምክር ስለመስጠት መመሪያ ለማግኘት 38.6.18.2ን ይመልከቱ።

አባላት ፆታዊ ጥቃት እንደተፈጸመ ከጠረጠሩ ወይም መፈፀሙን ካወቁ፣ ተጠቂዎችን እና ሌሎችን ለመጠበቅ በተቻለ ፍጥነት እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ለመንግሥት ባለሥልጣናት ማሳወቅን እንዲሁም ኤጲስ ቆጶሱን ወይም የካስማ ፕሬዘደንቱን ማስጠንቀቅን ይጠይቃል። በአንድ ልጅ ላይ ጥቃት የተፈፀመ እንደሆነ አባላት በ38.6.2.1 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች መከተል አለባቸው።

38.6.18.2

ለፆታዊ ጥቃት፣ አስገድዶ መደፈር ወይም ለሌሎች የወሲብ ትንኮሳ መልኮችተጠቂዎች ምክር መስጠት

የፆታዊ ጥቃት፣ አስገድዶ መደፈር ወይም የሌሎች የወሲብ ትንኮሳ መልኮች ተጠቂዎችብዙውን ጊዜ ከባድ የሥሜት ቀውስ ይደርስባቸዋል። በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ ላይ እምነት ሲጥሉ፣ እርሱ ልባዊ በሆነ ርህራሄ ምላሽ ይሰጣል። ጥቃቱ ያስከተለውን አፍራሽ ውጤት እንዲቋቋሙ ለመርዳት መንፈሳዊ ምክር እና ድጋፍ ይሰጣል። የቤተክርስቲያኗን የጥቃት እርዳታ የስልክ መስመር (ካለ) ይደውላል።

አንዳንድ ጊዜ ተጠቂዎች የሃፍረት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። ተጠቂዎች የኃጢአት ጥፋተኝነት የለባቸውም። መሪዎች ተጠቂውን ጥፋተኛ ማድረግ የለባቸውም። እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት የሚመጣውን ፈውስ እንዲገነዘቡ ይረዷቸዋል (አልማ 15፥8ን፤ 3 ኔፊ 17፥9ን ይመልከቱ)።

አባላት ስለጥቃቱ ወይም ስለትንኮሳው መረጃን ለመጋራት ሊመርጡ ቢችሉም፣ መሪዎች በዝርዝሮቹ ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር የለባቸውም። ይህ ለተጠቂዎች ጎጂ ሊሆን ይችላል።

የጥቃት ሰለባዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች በመንፈስ አነሳሽነት ከሚቀበሉት እርዳታ በተጨማሪ ሙያዊ ምክር ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ለመረጃ 31.3.6ን ይመልከቱ።

38.6.18.3

የአባልነት ምክር ቤት

በአንድ ሰው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ወይም ጾታዊ ጥቃት ለፈጸመ ሰው የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። አንድ አባል አስገድዶ መድፈር ከፈጸመ ወይም በሌላ ዓይነት ወሲባዊ ትንኮሳ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

38.6.20

ራስን ማጥፋት

ሥጋዊ ህይወት የእግዚአብሔር ውድ ስጦታ ነው—ዋጋ ሊሰጠው እና ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ስጦታ ነው። ቤተክርስቲያኗ ራስን ማጥፋትን መከላከልን አጥብቃ ትደግፋለች።

ራስን ስለማጥፋት የሚያስቡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከአካላዊ፣ ከአእምሯዊ፣ ከስሜታዊ ወይም ከመንፈሳዊ ህመም እፎይታን ማግኘት ይፈልጋሉ። እንደነዚህ አይነት ግለሰቦች ከቤተሰብ፣ ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች እና ብቃት ካላቸው ባለሙያዎች ፍቅር፣ እርዳታ እና ድጋፍ ይፈልጋሉ።

አንድ አባል ራሱን ለማጥፋት እያሰበ ከሆነ ወይም ሞክሮ የሚያውቅ ከሆነ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተክርስቲያን ድጋፍ ይሰጣል። እንዲሁም አባሉ ወዲያውኑ የባለሙያ እርዳታ እንዲያገኝ ይረዳዋል።

የምንወዳቸው ሰዎች፣ መሪዎች እና ባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረቶችን ቢያደርጉም ራስን ማጥፋት ሁልጊዜ መከላከል የሚቻል ነገር አይደለም። ለሚወዷቸው እና ለሌሎች ጥልቅ የሆነ የልብ ስብራትን፣ ትልቅ አሉታዊ የስሜት ለውጥን እና ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ትቶ ያልፋል። መሪዎች ቤተሰቡን መምከር እና ማፅናናት ይኖርባቸዋል። እንክብካቤን እና ድጋፍን ይሰጣሉ።

አንድ ግለስብ የራሱን ወይም የራሷን ሕይወት ማጥፋቱ/ቷ ትክክል አይደለም። ሆኖም በግለሰቡ ሃሳቦች፣ ድርጊቶች እና በተጠያቂነት ደረጃ ሊፈርድ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው (1 ሳሙኤል 16፥7ን፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥9ን ይመልከቱ)።

የሚወዱትን ሰው ራስን በማጥፋት ያጡ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ተስፋን እና ፈውስን ሊያገኙ ይችላሉ።

38.6.23

በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች

በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች ውስብስብ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል። ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገልጹ አባላት እና አባላት ያልሆኑ ግለሰቦች—እንዲሁም ቤተሰባቸው እና ጓደኞቻቸው—በጥንቃቄ፣ በደግነት፣ በርህራሄ እና በተትረፈረፈ የክርስቶስ መሰል ፍቅር መያዝ አለባቸው። ሁሉም በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ፣ በሌሎች የእሁድ ስብሰባዎች እና ቤተክርስቲያኗ በምታዘጋጃቸው ማህበራዊ ዝግጅቶች ላይ እንዲገኙ ይጋበዛሉ (38.1.1ን ይመልከቱ)።

ጾታ የሰማይ አባት የደስታ እቅድ አስፈላጊ ባህሪ ነው። ጾታ በቤተሰብ ለአለም የተላለፈ አዋጅ ውስጥ እንዲኖረው የታሰበው ትርጉም በውልደት ጊዜ የተገኘ ባዮሎጂያዊ ጾታ ነው። አንዳንድ ሰዎች በባዮሎጂያዊ ጾታቸው እና በጾታ ማንነታቸው መካከል አለመጣጣም ይሰማቸዋል። በዚያ ምክንያት፣ ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገልጹ ሊሆኑ ይችላሉ። ቤተክርስቲያኗ በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ በሚገልጹ ግለሰቦች ምክንያቶች ላይ አቋም አትወስድም።

አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን ተሳትፎዎች እና አንዳንድ የክህነት ሥርዓቶች የየትኛውም ፆታ አባል መሆንን የሚጠይቁ አይደሉም። ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገልጹ ግለሰቦች በ38.2.8.10 ውስጥ በተዘረዘረው መሰረት ሊጠመቁ እና ማረጋገጫ ሊያገኙ ይችላሉ። ቅዱስ ቁርባንን ሊወስዱ እና የክህነት በረከቶችን ሊቀበሉም ይችላሉ። ነገር ግን የክህነት ሹመት እና የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን መቀበል የሚቻለው በውልደት ጊዜ በተገኘ ባዮሎጂያዊ ጾታ መሰረት ነው።

የቤተክርስቲያን መሪዎች አንድ ግለሰብ በውልደት ጊዜ ካገኘው ባዮሎጂያዊ ጾታው ወደ ተቃራኒው ጾታ ለመቀየር ዓላማ የሚያደርገውን የተመረጠ የሕክምና ወይም የቀዶ ጥገና ጣልቃ ገብነት (“ፆታን እንደገና መመደብ”) የሚነቅፍ ምክርን ይለግሳሉ። እነዚህን ድርጊቶች መፈጸም ቤተክርስቲያኗ የአባልነት እገዳዎችን ለመጣል ምክንያት ሊሆናት እንደሚችል መሪዎች ይመክራሉ።

በተጨማሪም መሪዎች ማህበራዊ ሽግግርን /ሶሻል ተራንዚሽኒንግ/ የሚነቅፍ ምክር ይለግሳሉ። ማህበራዊ ሽግግርን /ሶሻል ተራንዚሽኒንግ/ አንድ ግለሰብ ከእርሱ ወይም ከእርሷ በውልደት ጊዜ የተገኘ ባዮሎጂያዊ ጾታ ተቃራኒ ሆኖ/ና ለመቅረብ ሲል/ስትል አለባበስን ወይም አጋጌጥን ወይም ስምን ወይም ተውላጠ ስምን መቀየርን ያካትታል መሪዎች ማህበራዊ ሽግግር/ሶሻል ተራንዚሽኒንግ/ የሚያደርጉ ሰዎች በዚህ ሽግግር ጊዜ ውስጥ አንዳንድ የቤተክርስቲያን የአባልነት እገዳዎች እንደሚጣልባቸው ይመክራሉ።

የሚጣሉት እገዳዎች ክህነትን መቀበልን እና መጠቀምን፣ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ማግኘትን እና መጠቀምን እንዲሁም የተወሰኑ የቤተክርስቲያን ጥሪዎችን መቀበልን ያካትታሉ። ምንም እንኳን በአንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶች ላይ እገዳ የተጣለ ቢሆንም፣ ሌላ የቤተክርስቲያን ተሳትፎ በበጎ ይታያል።

አንድ አባል የመረጠውን ስም ወይም የመጠሪያ ተውላጠ ስም ለመቀየር ከወሰነ፣ የስም ምርጫው በአባልነት መዝገቡ ላይ ባለው የተመራጭ ስም ቦታ ላይ ምልክት ሊደረግበት ይችላል። ግለሰቡ በአጥቢያው ውስጥ በመረጠው ስም ሊጠራ ይችላል።

ሁኔታዎች ከክፍል ክፍል እንዲሁም ከሰው ሰው በጣም ይለያያሉ። አባላት እና መሪዎች በጋራ እንዲሁም ከጌታ ጋር ይመክራሉ፡፡ የዋና አካባቢ አመራሮች ግለሰባዊ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ የቅርብ የአካባቢ መሪዎችን ይረዷቸዋል። ኤጲስ ቆጶሳት ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ሊመክሩ ይችላሉ። የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና የሚስዮን ፕሬዚዳንቶች ከዋና አካባቢ አመራር ምክር መሻት ይኖርባቸዋል (32.6.3ን ይመልከቱ)።

38.7

የህክምና እና የጤና ፖሊሲዎች

38.7.2

ቀብር እና አስከሬን ማቃጠል

የሟቹ/ቿ ቤተሰብ አስከሬኑ ይቀበር ወይስ ይቃጠል የሚለውን ይወስናሉ። እነርሱም የግለሰቡን/ቧን ፍላጎት ያከብራሉ።

የአንዳንድ አገሮች ሕግ አስከሬን ማቃጠልን አስገዳጅ ያደርጋል። በሌሎች ሁኔታዎች ቀብር ማስፈጸም አይቻልም ወይም የቤተሰቡ አቅም አይፈቅድም። በሁሉም ሁኔታዎች አስክሬኑ በክብር እና በጥልቅ አክብሮት መያዝ አለበት። አባላት የትንሳኤ ሃይል ሁልጊዜ እንደሚሰራ ማጋገጫ ሊያገኙ ይገባል (አልማ 11፥42–45 ይመልከቱ)።

በተቻለ መጠን የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ ሟች አስከሬን በሚቀበርበት ወይም በሚቃጠልበት ጊዜ የቤተመቅደስ የሥነ ሥርዓት ልብስ መልበስ አለበት (38.5.8 ን ይመልከቱ)።

38.7.3

ከውልደት በፊት የሞቱ ልጆች (ሞተው የተወለዱ እና የጨነገፉ ልጆች)

ወላጆች የመታሰቢያ ወይም የቀብር ቦታ ፕሮግራሞችን ስለማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ።

ከውልደት በፊት ለሞቱ ልጆች የቤተመቅደስ ሥርዓቶች አያስፈልጉም ወይም አይደረጉም። ይህ እነዚህ ልጆች በዘለዓለማዊ ህይወት የቤተሰቡ አካል የመሆን እድላቸውን አያበላሽም። ወላጆች በጌታ እንዲታመኑ እና ማፅናኛውን እንዲሹ ይበረታታሉ።

38.7.4

በፅኑ የተታመመ የማይድንን ሰው ህይወቱ እንዲያልፍ መርዳት

ሥጋዊ ህይወት የተቀደሰ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። “Euthanasia [ዩትኔዚያ] ማለት በማይድን በሽታ ወይም በሌላ ሁኔታ የሚሠቃይን ሰው ሕይወት ሆን ብሎ እንዲያልፍ መርዳት ማለት ነው። አንድን ሰው ራስን በማጥፋት እንዲሞት መርዳትን ጨምሮ በፅኑ የተታመመ የማይድንን ሰው ህይወቱ እንዲያልፍ በመርዳት /ዩትኔዚያ/ ውስጥ የሚሳተፍ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ይጥሳል እንዲሁም የአካባቢ ህጎችን ሊጥስም ይችላል።

በህይወት መጨረሻ ላይ ለአንድ ሰው የሚደረግን ውስብስብ የህይወት ድጋፍ ድርጊቶችን ማቋረጥ ወይም ማቆም በፅኑ የተታመመ የማይድንን ሰው ህይወት እንዲያልፍ እንደመርዳት /ዩትኔዚያ/አይቆጠርም (38.7.11ን ይመልከቱ)።

38.7.5

የኤችአይቪ ኢንፌክሽን እና ኤድስ

በኤች አይ ቪ(ሂዩማን ኢሚዩነውዲፊሸንሲ ቫይረስ) የተያዙ አባላት ወይም ኤድስ (አኳየርድ ኢሚዩኖዲፊሸንሲ ሲንድረም)ብሽታያለባቸው አባላት በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች እና አክቲቪቲዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል። ተሳትፏቸው በሌሎች ላይ የጤና ስጋት የሚፈጥር አይደለም።

38.7.8

ህክምና እና ጤና ጥበቃ

ብቁ የሕክምና እርዳታ መፈለግ፣ እምነት ማድረግ እና የክህነት በረከቶችን መቀበል በጌታ ፈቃድ መሰረት ፈውስን ለማግኘት አብረው ይሰራሉ።

አባላት በሥነ ምግባር፣ በመንፈሳዊ ወይም በሕግ አጠያያቂ የሆኑ የሕክምና ወይም የጤና ልምምዶችን መጠቀም ወይም ማስተዋወቅ የለባቸውም። የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በሚሰሩበት አካባቢ የሥራ ፈቃድ ካላቸው ባለሙያዎች ጋር መማከር አለባቸው።

38.7.9

ለህክምና የተፈቀደ ማሪዋና

ቤተክርስቲያኗ ለህክምና ዓላማዎች ካልሆነ በስተቀር ማሪዋና መጠቀምን ትቃወማለች። 38.7፥14ን ይመልከቱ።

38.7.11

(የህይወት ድጋፍን ጨምሮ) ህይወትን ማራዘም

አባላት ውስብስብ በሆኑ መንገዶች ምድራዊ ህይወትን የማራዘም ግዴታ እንዳለባቸው ሊሰማቸው አይገባም። እነዚህ ውሳኔዎች በተሻለ ሁኔታ ሊደረጉ የሚችሉት ከተቻለ በግለሰቡ ወይም በቤተሰብ አባላት ነው። በጸሎት አማካኝነት ብቁ የሕክምና ምክር እና መለኮታዊ መመሪያ ማግኘት አለባቸው።

38.7.13

ክትባቶች

ብቃት ባላቸው የሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ ክትባቶች ጤናን ይጠብቃሉ እንዲሁም ህይወትን ጠብቀው ያቆያሉ። የቤተክርስቲያኗ አባላት ራሳቸውን፣ ልጆቻቸውን እና ማህበረሰባቸውን በክትባት እንዲከላከሉ ይበረታታሉ።

በመጨረሻም ግለሰቦች ክትባትን በተመለከተ የራሳቸውን ውሳኔ የመስጠት ሃላፊነት አለባቸው። አባላት ሥጋት ካላቸው ከህክምና ባለሙያዎች ጋር መማከር እና የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ መሻት አለባቸው።

38.7.14

የጥበብ ቃል እና ጤናማ የሆኑ ልምዶች

የጥበብ ቃል የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89 ውስጥ ያሉት ትምህርቶች ሲጋራን፣ ጠንካራ መጠጦችን (አልኮል) እና ትኩስ መጠጦችን (ቡና እና ሻይ) እንደሚያካትቱ ነቢያት አብራርተዋል።

በጥበብ ቃል ወይም በቤተክርስቲያን መሪዎች ተለይተው ያልተገለጹ ሌሎች ጎጂ ነገሮች እና ልማዶች አሉ። አባላት አካላዊ፣ መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ጤንነታቸውን የማሳደግ ምርጫዎችን በማድረግ ረገድ ጥበብን እና በጸሎት መንፈስ የተመራ ውሳኔን ማድረግ አለባቸው።

38.8

አስተዳደራዊ ፖሊሲዎች

38.8.1

ጉዲፈቻ እና የማደጎ እንክብካቤ

ልጆችን በጉዲፈቻ ማሳደግ እና የማደጎ እንክብካቤ መስጠት ልጆችን እና ቤተሰቦችን ይባርካል። አፍቃሪ ዘለዓለማዊ ቤተሰቦች በጉዲፈቻ ሊፈጠሩ ይችላሉ። ልጆች ቤተሰብን የሚቀላቀሉት በጉዲፈቻም ሆነ በመወለድ እኩል ውድ በረከት ናቸው።

ልጆችን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ወይም የማደጎ እንክብካቤ ለመስጠት የሚፈልጉ አባላት የሚመለከታቸውን አገሮች እና መንግስታት ጉዳዩን የተመለከቱ ህጎች ሁሉ ማክበር አለባቸው።

38.8.4

የአጠቃላይ ባለሥልጣናት፣ የአጠቃላይ ኃላፊዎች እና የአካባቢ ሰባዎች ፊርማዎች እና ፎቶግራፎች

የቤተክርስቲያን አባላት የአጠቃላይ ባለሥልጣናትን፣ የአጠቃላይ ኃላፊዎችን እና የአካባቢ ሰባዎችን ፊርማዎች እና ፎቶግራፎች መፈለግ የለባቸውም። ይህንን ማድረግ የተቀደሱ ጥሪዎቻቸውን እና የስብሰባዎቹን መንፈስ ትኩረት ይበትናል። ለሌሎች አባላት ሰላምታ እንዳይሰጡ ሊያደርጋቸውም ይችላል።

አባላት አጠቃላይ ባለሥልጣናትን፣ አጠቃላይ ኃላፊዎችን እና የአካባቢ ሰባዎችን በጸሎት ቤት ውስጥ ፎቶ ማንሳት አይገባቸውም።

38.8.7

የቤተክርስቲያን መፅሔቶች

የቤተክርስቲያን መፅሔቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

ቀዳሚ አመራሮች እያንዳንዱ አባል የቤተክርስቲያን መፅሄቶችን እንዲያነብ ያበረታታሉ። መፅሔቶቹ፣ አባላት የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲማሩ፣ በህይወት ያሉ ነቢያትን ትምህርቶች እንዲያጠኑ፣ ከዓለም አቀፉ የቤተክርስቲያኗ ቤተሰብ ጋር አንድነት እንዲሰማቸው፣ ፈተናዎችን በእምነት እንዲጋፈጡ እና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ መርዳት ይችላሉ።

38.8.8

የቤተክርስቲያኗ ስም፣ የፅሁፍ ሎጎ እና ምልክት

ምስል
የቤተክርስቲያን የፅሁፍ ሎጎ እና ምልክት

የቤተክርስቲያኗ ስም፣ የፅሁፍ ሎጎ እና ምልክት የቤተክርስቲያኗ ቁልፍ መለያዎች ናቸው።

የፅሁፍ ሎጎ እና ምልክት የቤተክርስቲያኗ የፅሁፍ ሎጎ እና ምልክት(ምስሉን ከላይ ይመልከቱ)በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት በሚፈቀድበት ጊዜ ብቻ ስራ ላይ ይውላሉ። እነዚህ እንደማጋጌጫ ነገሮች ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም። እንዲሁም በማንኛውም የግል፣ የንግድ ወይም የማስታወቂያ መንገድ መጠቀም አይቻልም።

38.8.10

ኮምፒተሮች

በቤተክርስቲያኗ መሰብሰቢያ አዳራሾች ውስጥ የሚያገለግሉ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች የሚቀርቡት እና የሚተዳደሩት በቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም በዋና አካባቢው ቢሮ ነው። መሪዎች እና አባላት እነዚህን ሀብቶች የሚጠቀሙት የቤተሰብ ታሪክ ስራን ጨምሮ የቤተክርስቲያን ዓላማዎችን ለመደገፍ ነው።

በእነዚህ ኮምፒውተሮች ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች በሙሉ በትክክል ቤተክርስቲያኗ እንድትጠቀምባቸው ፈቃድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

38.8.12

የሥርዓተ ትምህርት መርጃዎች

አባላት የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲማሩ እና እንዲኖሩ ለመርዳት ቤተክርስቲያኗ መርጃዎችን ታቀርባለች። እነዚህም ቅዱሳት መጻህፍትን፣ አጠቃላይ የጉባኤ መልእክቶችን፣ መፅሔቶችን፣ ማኑዋሎችን፣ መጻሕፍትን እና ሌሎች መገልገያዎችን ያካትታሉ። አባላት ወንጌልን በቤት ለማጥናት ቅዱሳት መጻህፍትን እና እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ መሪዎች ያበረታታሉ።

38.8.14

ልብስ እና ገፅታ

የቤተክርስቲያኗ አባላት የተገቢ አለባበስ እና ገፅታ ምርጫቸው ለአካላቸው ያላቸውን ክብር የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ይበረታታሉ። ተገቢ አለባበስ እንደባህሉ እንዲሁም ለተለያዩ ሁኔታዎች የተለያየ ነው።

38.8.16

የጾም ቀን

አባላት በማንኛውም ጊዜ ሊፆሙ ይችላሉ። ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ የወሩን የመጀመሪያ ሰንበት የጾም ቀን አድርገው ያከብራሉ።

የፆም ቀን መጸለይን፣ ለ24 ሰአታት ያህል ያለምግብ እና ያለመጠጥ መቆየትን (በአካል ብቁ ከሆነ) እና በቸርነት የጾም በኩራት መስጠትን ያካትታል። የጾም መስዋዕት እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት የሚደረግ ስጦታ ነው (22.2.2ን ይመልከቱ)።

አንዳንድ ጊዜ በወሩ የመጀመሪያ ሰንበት ቤተክርስቲያን አቀፍ ወይም የአካባቢ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የካስማ አመራሩ አንድ ተለዋጭ ሰንበትን የጾም ቀን እንዲሆን ይወስናል።

38.8.17

ቁማር እና ሎተሪዎች

ቤተክርስቲያኗ ማንኛውንም ዓይነት ቁማር ታወግዛለች እንዲሁም ከእርሱ መራቅ እንደሚገባ ትመክራለች። የስፖርት ውርርድን እና በመንግስት የሚደረጉ የሎተሪ ዕጣዎችን ይጨምራል።

38.8.19

ስደት

በትውልድ አገራቸው የሚቆዩ አባላት አብዛኛውን ጊዜ በዚያ ቤተክርስቲያንን የመገንባት እና የማጠናከር ዕድሎች አሏቸው። ሆኖም ወደ ሌላ አገር መሰደድ የግል ምርጫ ነው።

ወደ ሌላ ሀገር የሚሄዱ አባላት የሚመለከቷቸውን ህጎች ሁሉ ማክበር አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥21ን ይመልከቱ)።

ሚስዮናውያን ሌሎች እንዲሰደዱ ስፖንሰር አይሆኑም።

38.8.22

የአገሩ ህግ

አባላት የሚኖሩባቸውን ወይም የሚሄዱባቸውን የማናቸውንም ሀገር ህጎች መጠበቅ፣ ማክበር እና መደገፍ አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥21ን፤ የእምነት አንቀጾች 1፥2 ይመልከቱ)። ይህ፣ በሙሉ ጊዜ ስለወንጌል ማስተማርን የሚከለክሉ ህጎችን ይጨምራል።

38.8.25

አባላት ከቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት

የቤተክርስቲያኗ አባላት ትምህርትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን፣ የግል ችግሮችን ወይም ጥያቄዎችን ለአጠቃላይ ባለስልጣናት ለማቅረብ ስልክ እንዳይደውሉ፣ ኢሜል እንዳይልኩ ወይም ደብዳቤ እንዳይፅፉ ይበረታታሉ። አባላት መንፈሳዊ መመሪያ በሚፈልጉበት ጊዜ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ወይም የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ የቅርብ የአካባቢ መሪዎቻቸውን እንዲገናኙ ይበረታታሉ (31.3ን ይመልከቱ)።

38.8.27

የአካል ጉዳት ያለባቸው አባላት

መሪዎች እና አባላት በሚኖሩበት አካባቢ ባለው ክፍላቸው ውስጥ የሚኖሩትን ሁሉ ፍላጎቶች እንዲያሟሉ ይበረታታሉ። አካል ጉዳት ያለባቸው አባላት ዋጋ አላቸው እንዲሁም ትርጉም ባለው መንገድ አስተዋፅዖ ማድረግ ይችላሉ። የአካል ጉዳቶች አእምሯዊ፣ ማህበራዊ፣ ስሜታዊ ወይም አካላዊ ሊሆኑ ይችላሉ።

38.8.29

ሌሎች እምነቶች

ብዙ የሚያነሳሳ፣ መልካም እና እጅግ ትልቅ ክብር የሚገባው ነገር በብዙ ሌሎች እምነቶች ውስጥ ይገኛል። ሚስዮናውያን እና ሌሎች አባላት የሌሎችን እምነቶች እና ልማዶች በተመለከተ ጥንቃቄ የሚያደርጉ እና ክብር የሚሰጡ መሆን አለባቸው።

38.8.30

የፖለቲካ እና የሲቪክ እንቅስቃሴ

የቤተክርስቲያን አባላት በፖለቲካ እና በመንግስት ጉዳዮች እንዲሳተፉ ይበረታታሉ። በብዙ አገራት፣ ይህ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  • ድምፅ መስጠትን።

  • የፖለቲካ ፓርቲዎችን መቀላቀልን ወይም በፖለቲካዊ ፓርቲዎች ውስጥ ማገልገልን።

  • የገንዘብ ድጋፍ መስጠትን።

  • ከፓርቲ መሪዎች እና ከዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር መገናኘትን።

  • በተመረጡበት ወይም በተሾሙበት ክልላዊ እና ብሄራዊ መንግስት ማገልገልን።

በተጨማሪም አባላት ማህበረሰባቸውን ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ እና ቤተሰብን ለማሳደግ መልካም ምግባር በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ።

የቅርብ አካባቢ የቤተክርስቲያን መሪዎች አባላት በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ ማደራጀት አይገባቸውም። እንዲሁም መሪዎች አባላት በሚሳተፉበት መንገድ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ መሞከር አይገባቸውም።

መሪዎች እና አባላት ቤተክርስቲያኗን እንደ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ መድረክ፣ ፖሊሲ ወይም እጩ ደጋፍ ሊያስወስዷት የሚችሉ ንግግሮችን ወይም ባህርያትን ማስወገድ አለባቸው።

38.8.31

የአባላት የመረጃ ጥበቃ

የቤተክርስቲያን መሪዎች የአባላትን የመረጃ ጥበቃን የማስከበር ግዴታ አለባቸው። የቤተክርስቲያን መዛግብት፣ ማውጫዎች እና ተመሳሳይ የመረጃ ምንጮች ለግል፣ ለንግድ ወይም ለፖለቲካ ጉዳዮች ጥቅም ላይ አይውሉም።

38.8.35

ስደተኞች

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመንከባከብ (ሞዛያ 4፥26ን ይመልከቱ) በተጣለባቸው ሃላፊነት መሰረት፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች ስደተኞችን እንደማህበረሰባቸው አባላት አድርገው ለመቀበል ጊዜያቸውን፣ ተሰጥኦዋቸውን ይሰጣሉ እንዲሁም ወዳጅነታቸውን ያሳያሉ።

38.8.36

ቤተክርስቲያኗን የገንዘብ እርዳታ መጠየቅ

እርዳታ የሚያስፈልጋቸው አባላት የቤተክርስቲያኗን ዋና መስሪያ ቤት ከማነጋገር ወይም ከሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ወይም አባላት ገንዘብ ከመጠየቅ ይልቅ ኤጲስ ቆጶሳቸውን እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ።