ምዕራፍ ፲፩
ኔፊ የጌታን መንፈስ አየ እና የህይወት ዛፍ በራዕይ ታየው—እርሱም የእግዚአብሔርን ልጅ እናት አየ እናም ስለእግዚአብሔር ትህትና ተማረ—እርሱም የእግዚአብሔርን በግ ጥምቀት አገልግሎትና ስቅለት አየ—እናም ደግሞ የአስራ ሁለቱን የበጉን ሐዋርያት ጥሪና አገልግሎት አየ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ ያየውን ነገሮች ለማወቅ ከፈለግሁ በኋላ፣ እናም ጌታ ሊያሳውቀኝ እንደሚችል በማመን በልቤ ሀእያሰላሰልኩ ተቀምጬ ሳለሁ በጌታ መንፈስ፣ አዎን፣ በፊት አይቼው ወደማላውቀውና ከዚህ በፊት በእግሮቼ ቆሜበት ወደማላውቀው እጅግ ከፍ ያለ ለተራራ ሐተወሰድኩ።
፪ እነሆ መንፈስ፣ ምን ትፈልጋለህ? አለኝ።
፫ እና እኔም አልሁ፥ አባቴ ሀያያቸውን ነገሮች ማየት እፈልጋለሁ።
፬ እና መንፈስም አለኝ—አባትህ የተናገረውን ሀዛፍ እንዳየ ታምናለህን?
፭ እናም እኔ አልኩ—አዎን፣ የአባቴን ቃላት በሙሉ ሀእንደማምን አንተ ታውቃለህ።
፮ እናም እነዚህን ቃላት ስናገር መንፈስ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፥ ሆሳዕና ለጌታ ለልዑል እግዚአብሔር፤ እርሱ ሀበምድር ሁሉ ላይ፣ አዎን፣ ከሁሉም በላይ አምላክ ነው። እናም አንተ፣ ኔፊ፣ የተባረክህ ነህ፣ ምክንያቱም አንተ በልዑል እግዚአብሔር ልጅ ለአምነሀልና፣ ስለዚህ የተመኘሀቸውን ነገሮች ታያለህ።
፯ እና እነሆ እነዚህ ነገሮች ለአንተ ሀለምልክት ይሰጡሀል፣ አባትህ የቀመሰውን ፍሬ የሚሰጠውን ዛፍ ካየህ በኋላ ደግሞም አንድ ሰው ከሰማይ ሲወርድ ታያለህ፣ እናም አንተ እርሱን ታያለህ፤ እናም ካየኸውም በኋላ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለትመሰክራለህ።
፰ እናም እንዲህ ሆነ መንፈስ እንዲህ አለኝ—ተመልከት! ተመለከትኩና ሀዛፍን አየሁ፤ አባቴም እንዳየው አይነት ዛፍ ነበር፤ ውበቱም አዎን ከሁሉም ውብ ነገር የላቀ ነበር፤ ንጣቱም ከሚገፋው በረዶ ለንጣት የላቀ ነበር።
፱ እናም እንዲህ ሆነ ዛፉን ካየሁ በኋላ፣ ለመንፈሱ፥ ከሁሉ በላይ ሀየከበረውን ዛፍ እንዳሳየኸኝ ተመለከትኩ አልኩት።
፲ እናም እርሱ፥ አንተ ምን ትፈልጋለህ? አለኝ።
፲፩ እናም እኔ ለእርሱ፥ ሀትርጓሜውን ለማወቅ ነው አልኩት—እኔም ሰው እንደሚናገረው ለእርሱ ተናገርኩት፤ ምክንያቱም እርሱ በሰው ለአምሳል እንደነበር ስለተመለከትኩ ነው፤ ይሁን እንጂ፣ የጌታ መንፈስ መሆኑን አውቅ ነበር፣ እናም ሰው ከሌላ እንደሚነጋገር እርሱ እኔን ተናገረኝ።
፲፪ እናም እንዲህ ሆነ እርሱ እኔን፥ ተመልከት! አለኝ፣ እኔም እርሱን ለመመልከት ዞርኩ እናም አላየሁትም ከእኔ ዘንድ ሄዶ ነበርና።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ እኔ ተመለከትኩ፣ እናም ታላቂቷን የኢየሩሳሌም ከተማ፣ ደግሞም ሌሎች ከተሞችን አየሁ። የናዝሬትንም ከተማ ተመለከትኩ፣ ሀበናዝሬትም ከተማ አንዲት ለድንግል ተመለከትኩ፣ እርሷም እጅግ ውብና ያማረች ነበረች።
፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ሀሰማያት ሲከፈቱ አየሁ፤ እናም አንድ መልአክ ወረደና በፊቴ ቆመ፤ እንዲህም አለኝ፥ ኔፊ፣ ምን ትመለከታለህ?
፲፭ እናም አንዲት ከድንግሎች ሁሉ በላይ መልካም፣ በጣም ቆንጆ ድንግል፣ በማለት ተናገርኩት።
፲፮ እናም የእግዚአብሔርን ትህትና ታውቃለህ? አለኝ።
፲፯ እናም እርሱ ልጆቹን እንደሚወድ አውቃለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ የሁሉን ነገሮች ትርጉም አላውቅም አልኩት።
፲፰ እነሆ የተመለከትካት ሀድንግል በስጋ የእግዚአብሔር ልጅ ለእናት ናት አለኝ።
፲፱ እናም እንዲህ ሆነ፣ እርሷ በመንፈስ እንደተወሰደች ተመለከትኩ፤ እና ለጥቂት ጊዜ ሀበመንፈስ ከተወሰደች በኋላ መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ተመልከት!
፳ እናም በድጋሚ ድንግሊቷ፣ በክንዷ ሀልጅ ይዛ አየሁ፣ እንዲሁም ተመለከትኩ።
፳፩ እናም መልአኩ እንዲህ አለኝ፥ እነሆ ሀየእግዚአብሔር በግ፣ አዎን እንዲያውም የዘላለማዊው ለአባት ሐልጅ! አባትህ ያየውን መዛፍ ትርጉም ታውቃለህ?
፳፪ እናም እንዲህ ስል መለስኩለት፤ አዎን፣ ይህ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ሁሉ ራሱን በስፋት የሚያፈስ የእግዚአብሔር ሀፍቅር ነው፤ ስለዚህ ከሁሉ ነገሮች በላይ መልካም ነው።
፳፫ እርሱም፣ አዎን፣ ለነፍስም በጣም ሀደስ የሚያሰኝ ነው አለኝ።
፳፬ እነዚህንም ነገሮች ካለ በኋላ፣ እንዲህ አለኝ—ተመልከት! እናም የእግዚአብሔር ልጅ በሰው ልጆች መካከል ሀሲሄድ ተመለከትኩ፤ ብዙዎችም በእግሩ ስር ሲወድቁና ሲሰግዱለት ተመለከትኩ።
፳፭ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ ያየው ሀየብረት በትር፣ ወደ ለህይወት ውሃዎች ምንጭ፣ ወይንም ወደ ሐህይወት ዛፍ፣ የሚመራው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ተመለከትኩ፤ ውሃዎቹም የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት ናቸው፤ ደግሞም የህይወት ዛፉም የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት መሆኑን አየሁ።
፳፮ እናም መልአኩ እንደገና እንዲህ አለኝ—የእግዚአብሔርን ሀትህትና እይ እንዲሁም ተመልከት አለኝ።
፳፯ እናም እኔ ሀተመለከትኩና አባቴ የተናገረለትንም የዓለም መድኃኒት ተመለከትኩ፣ ደግሞም ከእርሱ በፊት መንገዱን የሚያዘጋጀውን ለነቢይ ተመለከትኩ። የእግዚአብሔርም በግ ሄዶ በእርሱ ሐተጠመቀ፣ ከተጠመቀም በኋላ፣ ሰማያት ሲከፈቱና መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ ሲወርድና መበእርግብ አምሳል በእርሱ ላይ ሲያርፍ ተመለከትኩ።
፳፰ እናም እርሱ ህዝቡን ሀበኃይልና በታላቅ ክብር እያገለገለ ሲሄድ ተመለከትኩ፤ ብዙ ህዝብም ሊያዳምጡት ተሰበሰቡ፤ ከመካከላቸው ሲያስወጡትም ተመለከትኩ።
፳፱ እናም ደግሞ ሌሎች ሀአስራ ሁለት ሲከተሉት ተመለከትኩ። እናም እንዲህ ሆነ ከፊቴ በመንፈስ ተወሰዱም ተሰወሩብኝም።
፴ እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፣ ተመልከት! እናም ተመለከትኩና፣ ሰማያት እንደገና ሲከፈቱ ተመለከትኩ፣ ሀመላዕክትም በሰው ልጆች ላይ ሲወርዱ አየሁ፤ እነርሱንም አገለገሏቸው።
፴፩ እንደገናም እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ተመልከት! እኔም ተመለከትኩ፣ እናም የእግዚአብሔር በግ በሰው ልጆች መካከል ሲሄድ ተመለከትኩ። ብዛት ያላቸው የታመሙ እና በብዙ በሽታዎች፣ ሀበአጋንንትና ለበርኩሳን መናፍስት የሚሰቃዩ ሰዎችንም ተመለከትኩ፣ መልአኩም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለእኔ ተናገረም አሳየኝም። እነርሱም በእግዚአብሔር በግ ኃይል ሐተፈወሱ፣ እናም አጋንንትና ርኩሳን መናፍስትም ወጥተዋል።
፴፪ እናም እንዲህ ሆነ መልአኩ በድጋሚ እንዲህ ሲል ተናገረ—ተመልከት! እኔም የእግዚአብሔር በግ በሰዎች ሲወሰድ ተመለከትኩ፣ አዎን፣ የዘለዓለማዊው እግዚአብሔር ልጅ በዓለም ሀተፈረደበት፤ እኔም አየሁ፣ ምስክርም ሰጠሁ።
፴፫ እናም እኔ ኔፊ፣ ለዓለም ኃጢያት ሀበመስቀል ላይ ሲሰቀልና ለሲገደል ተመለከትኩ።
፴፬ እናም እርሱ ከተገደለ በኋላ የምድሪቱ ሰዎች የበጉን ሐዋርያት ለመዋጋት ሲሰበሰቡ ተመለከትኩ፣ ምክንያቱም እንደዚህ ነበር አስራ ሁለቱ በጌታ መልአክ የተጠሩት።
፴፭ እናም ብዙ የምድሪቱ ሰዎች በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አባቴም እንዳየው ህንፃ አይነት ትልቅና ሰፊ ሀህንፃ ውስጥ እንደነበሩ ተመለከትኩ። እናም የጌታ መልአክ እንዲህ ሲል እንደገና ተናገረኝ፥ እነሆ ዓለምና በውስጧ ያለው ጥበብ፣ አዎን፣ እነሆ የእስራኤል ቤት የበጉን አስራ ሁለት ሐዋርያት ለመዋጋት በአንድነት ተሰበሰቡ።
፴፮ እናም እንዲህ ሆነ ትልቁና ሰፊው ህንፃ የዓለም ሀኩራት መሆኑን አየሁ፣ መሰከርኩም፤ ይህም ወደቀ፣ ውድቀቱም እጅግ ታላቅ ነበር። በድጋሚም የጌታ መልአክ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ አስራ ሁለቱን የበጉን ሐዋርያት የሚዋጉ ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝቦች ሁሉ ውድቀት እንዲህ ይሆናል።