የጥናት እርዳታዎች
መላእክት


መላእክት

በሰማይ ውስጥ መላእክት ተብለው የተጠሩ ሁለት አይነት ህያው ፍጡር አሉ፥ መንፈሳት የሆኑ እና የስጋ እና አጥንት ሰውነቶች ያላቸው። መንፈስ የሆን መላእክት የስጋ እና አጥንት ሰውነትን አላገኙም፣ ወይም ስጋዊ ሰውነት የነበራቸው እና ትንሣኤን የሚጠብቁ መንፈሶች ናቸው። የስጋ እና አጥንት ሰውነቶች ያሏቸው መላእክት ከሞት የተነሱ ወይም በእምነት የተወሰዱ ናቸው።

በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ ስለመላእክት ስራ የሚጠቅሱ ብዙዎች አሉ። አንዳንዴ መላዕክት የእግዚአብሔር መልእክቶችን ሲያቀርቡ በመብረቅ ድምጾች ይናገራሉ (ሞዛያ ፳፯፥፲፩–፲፮)። ጻድቅም ስጋዊ ሰዎች መላዕክት ተብለው ለመጠራት ይችላሉ (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፲፱፥፲፭ [ተጨማሪ])። አንዳንድ መላእክት በሰማይ ውስጥ በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ ያገለግላሉ (አልማ ፴፮፥፳፪)።

ቅዱሣት መጻህፍት ስለዲያብሎስ መላእክትም ይናገራሉ። እነዚህ ሉሲፈርን የተከተሉ እና በቅድመ ምድራዊ ህይወት ከእግዚአብሔር ፊት እንዲወጡ ተደረጉ እና ወደ ምድር ተወረወሩ (ራዕ. ፲፪፥፩–፱፪ ኔፊ ፱፥፱፣ ፲፮ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፮–፴፯)።