እያንዳንዱ የአሮናዊ ክህነት ስልጣን ያለው ሰው መረዳት የሚገባው ነገር
የእናንተ የአሮናዊ ክህነት ሹመት የእግዚአብሔር ልጆች የክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ሀይል ለመቀበል ዋና ክፍል ነው።
ወንድሞች፣ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ውስጥ ከእናንተ ጋር በመሆኔ እድለኛ ነኝ። የሚስዮን ፕሬዘዳንት በነበርኩበት ጊዜ፣ የመጀመሪያ የሚስዮን ቡድናችንን ስንቀበል በጣም ደስተኛ ነበርኩኝ። ተጨማሪ ልምምድ ያላቸው አንዳንድ ወንጌል ሰባኪዎች ከእነርሱ ጋር ለትንሽ ጊዜ ለመገናኘት እየተዘጋጁ ነበር። የልጆችን ወንበሮች በግማሽ ክብ እንዳዘጋጁት ተመለከትኩኝ።
“እነዚህ ትንንሽ ወንበሮች ምንድን ነው ነገራቸው” ብዬ ጠየቅኩኝ።
“ለአዲሶቹ ሚስዮኖች ነው” ብለው ሚስዮኖቹ በእፍረት መለሱ።
ሌሎችን የምንመለከትበት መንገድ ማን እንደሆኑ እና ምን እንደሚሆኑ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አምናለሁ።1 በዛ ቀን ሚስዮኖቻችን በትልቅ ወንበር ላይ ተቀመጡ።
አንዳንድ ጊዜ፣ ለወንድ የአሮን ክህነት ስልጣን ተሸካሚ ወጣቶቻችን እግዚአብሔር ቅዱስ እምነትና ጠቃሚ የሆነ ስራ እንዲሰሩ እንደሰጣቸው እንዲመለከቱ ከመርዳት ይልቅ፣ የህፃን ወንበሮች እንዳንሰጣቸው እፈራለሁ።
ፕሬዘዳን ቶማስ ኤስ ሞንሰን ወጣት ወንዶች “የእግዚአብሔርን ክህነት ተሸካሚ መሆን ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እንዳለባቸው መከሩን። ወደተጠሩበት ቅዱሳዊ ጥሪ መንፈሳዊ ግንዛቤ መመራት አለባቸው።”2
ዛሬ፣ መንፈስ ቅዱስ ስለአሮናዊ ክህነት ኃይልና ቅድስና ለበለጠ መረዳት እንዲመራን እጸልያለሁ እንዲሁም በክህነት ሃላፊነታችና ላይ የበለጠ እንድናተኩር እንዲያነሳሳን እጸልያለሁ። መልዕክቴ፣ ለአሮናዊ ክህነት እንዲሁም ለመልከጸዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች በሙሉ ነው።
ሽማግሌ ዳለን ጂ ረንለንድ የክህነት አላማ ለእግዚአብሔር ልጆች ለኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ኃይል አቅርቦት መስጠት እንደሆነ አስተማሩ።3 የክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ ኃይል በሕይወታችን ውስጥ ለመቀበል፣ በእርሱ ማመን፣ ለሃጢያታችን ንስሃ መግባት፣ በስነስርዓቶች አማካኝነት ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን መግባትና መጠበቅ፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን መቀበል አለብን።4 እነዚህ ነገሮች በአንዴ የምንተገብራቸው መርሆዎች አይደሉም፣ ነገር ግን፣ ወደ ክርስቶስ መጥተን በእርሱ ፍጹማኖች እንሆን ዘንድ በህበረት እርስ በእርሳቸው ላይ በመገንባት ቀጣይነት ባለው ሂደት ውስጥ ይሰራሉ።5
ስለዚህ፣ በዚህ ውስጥ የአሮናዊ ክህነት ሀላፊነት ምንድን ነው? የክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ ኃይል አቅርቦት ለማግኘት እንዴት ይረዳናል? የመላዕክቶች አገልግሎትና የማዘጋጃ ወንጌል በሆነው የአሮናዊ ክህነት ቁልፍ ላይ መልሱ እንዳለ አምናለሁ።6
የመላዕክቶች አገልግሎት
በመላዕክቶች አገልግሎት አንድ ክፍል ላይ እንጀምር። የእግዚአብሔር ልጆች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ከሚኖራቸው በፊት፣ ሊያውቁትና ወንጌሉን ሊማሩ ይገባል። ሐዋርያው ፓውሎስ እንዳለው፤
“ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?
“ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? …
“እምነት ከመስማት ነው፣ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”7
ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር “… የክርስቶስን መምጣት ለሰው ልጆች ለማሳወቅ መላዕክቶችን ላኳል።”8 መላዕክቶች የእግዚአብሔርን መልዕክት የሚመሰክሩ ከሰማይ ናቸው።9 በእብራይስጥ እና በግሪክ የመልአክ ዋና ቃል ፍቺ “መልዕክተኛ” ማለት ነው።10
መላዕክቶች ቃሉን ሊያውጁ እና እምነትን ሊገነቡ በእግዚአብሔር ጥልጣን ያላቸው መልእክተኞች እንደሆኑ ሁሉ፣ የአሮን ክህነት የምንሸከም ሰዎች “ሁሉንም ለማስተማርና ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ለመጋበዝ”11 ተሸመናል።ወንጌልን መስበክ የክህነት ሃላፊነት ነው። ከዚህ ሃላፊነት ጋር የተገናኘው ኃይል ለነብያቶች ወይም ለሚስዮኖች ብቻ አይደለም። ይህ ለእናንተም ነው!12
ይህን ኃይል እንዴት ነው የምናገኘው? የ12 ዓመት ዲያቆን ወይም አንዳችን እንዴት ነው እምነት በክርስቶስን ወደ እግዚአብሔር ልጆች ልብ የምናመጣው? ኃይሉ በእኛ ውስጥ እንዲሆን ቃሎቹን በማከማቸት እንጀምራለን።13 ይህን ካደረግን “ሰዎች ለማሳመን የእግዚአብሔር ሀይል”14 እንደሚኖረን ቃል ገብቷል። በምልዓተ ጉባኤ ውስጥ ማስተማር ወይም የአባልን ቤት መጎብኘት እድል ሊሆን ይችላል። ከጓደኛ ወይም ከቤተሰባ አባል ጋር መነጋገርን ጨምሮ ትንሽ ኢመደበኛ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ ዝግጁ ከሆንን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መላዕክቶች እንደሚያስተምሩት ወንጌልን እናስተምራለን።15
በቅርብ በፓፑአ ጊኒ የአሮን ክህት ተሸካሚ የሆነውን ጄከብ ስለመጽሐፈ ሞርሞን ኃይል እና መጥፎ ነገርን እንዴት እንደሚቋቋም እና መንፈስን እንዴት እንደሚከተል እንደረዳው ሲመሰክር ሰማሁት። ቃላቶቹ የእኔን እና የሌሎችን እምነት አሳደገ። እንዲሁም የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎችን ንግግር በሸንጎ ስብሳባዎች ውስጥ ስሰማ እምነቴ አድጓል።
ወጣት ወንዶች፣እናንተ ስልጣን ያላችሁ መልእክተኞች ናችሁ። በቃላቶቻችሁ እና በስራዎቻችሁ በኩል፣ በእግዚአብሔር ልጆች ልብ የክርስቶስን እምነት ለማምጣት ትችላላችሁ።16 ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት፣ “ለእነርሱ እንደአገልጋይ መላእክቶች ትሆናላችሁ።”17
የማዘጋጃው ወንጌል
በክርስቶስ ላይ ያደገ እምነት ሁሌም ወደ መለወጥ መሻትን ወይም ወደ ንስሃ ያመራል።18 ስለዚህ የመላዕክት አገልግሎት ቁልፍ “የንስሃና ጥምቀት እንዲሁም የሃጢያት ስርየት ወንጌል” በሆነው በማዘጋጃ ወንጌል ቁልፍ መከተሉ ተገቢ ነው።19
የአሮናዊ ክሀነት ሃላፊነታችሁን ስታጠኑ፣ ሌሎችን ንስሃ እንዲገቡና እንዲሻሻሉ የሚደነግግ ግብዣን ታያላችሁ።20 ያ በመንደግ ማዕዘን ላይ ቆመን ንስሃ ግቡ እያን መጮኽ ማለት አይደለም! ያ ማለት እኛ ንስሃ እንድንገባ፣ እኛም በይበልጥ ሌሎችን ይቅር እንድንል እና ሌሎችን ስናገለግል ንስሃ የሚያመጣውን ተስፋና ሰላም ስለተለማመድለነው ለሌሎች ማቅረብ ማለት ነው።
የአሮናዊ ክህነት ተሸካዎች የራሳቸውን የምልዓተ ጉባኤ አባሎችን ሲጎበኙ አብሬአቸው ነበርኩኝ። የሳሳ ልባቸውን እንዲሁም ወንድሞቻቸውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሰማቸው ሲረዱ ተመልክቻለሁ። አንድ ወጣት ለጓደኞቹ ስለንስሃ ኃይል ሲመሰክር ሰምቻለሁ። ይህን ሲያደርግ ልቦች ሳሱ፣ ሃላፊነቶች ተደረጉ እንዲሁም የክርስቶስ የፈዋሽነት ኃይል ተሰማ።
ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ እንዳስተማሩት፥ “ንስሃ መግባት አንድ ነገር ነው። ሃጢያታችን መሻሩ ወይም ይቅር መባሉ ሌላ ነገር ነው። ይህንን የማምጣት ሃይል ያለው የአሮንዊ ክህነት ላይ ነው።”21 የጥምቀትና የቅዱስ ቁርባን የአሮናዊ ክህነት ስነስርዓቶች ለኃጢያት ስርየት የምንገባውን ንስሃችንን ይመለከታሉ እንዲሁም ያጠናቅቃሉ።22 ይህንን ፕሬዘዳንት ዳለን ኤች ኦክስ እንደዚህ ገለፁ፥ “ለሃጢያትችን ንስሃ እንድንገባ እና ወደ ጌታ በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ እንድንመጣ እና ቅዱስ ቁርባን እድንካፈል ታዘናል። … በዚህ መንገድ የጥምቀት ቃልኪዳናችንን ስናድስ፣ ጌታ የጥምቀት ማፅጃ ውጤትን በዳግም ያድሳል።”23
ወንድሞች፣ ይህም በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ሀይል በኩል ንስሀ ለገቡ ልቦች የኃጢያቶች ስርየት ስርዓቶችን የማቅረብ ቅዱስ እድል ነው።24
ቅዱስ ቁርባንን ለመጀመሪያ ጊዜ በመባረክ እራሱን ለመግለጽ ስለተቸገረ ስለ አንድ ካህን ተነገረኝ። ይህን ሲያደርግ ኃይለኛ የሆነ መንፈስ በእሱ እና በታዳሚዎቹ ላይ መጣ። ከዛ በኋላ፣ በዛ ስነስርዓት ላይ ስለተሰማው ስለእግዚአብሔር ኃይል ትንሽ ነገር ግን ግልፅ የሆነ ምስክርነት ሰጠ።
በሲድኒ አውስታሊያ ውስጥ፣ አራት የካህን ክፍል አባሎች የምቡሎንጎ ቤተሰቦችን አጠመቁ። ከእነዚህ ካህናት እናቶች አንዷ አንድ ሀይለኛ አጋጣሚ ልጇን እንዴት እንደነካው ነገረችኝ። እነዚህ ካህናት “በኢየሱስ ክርስቶስ ተመድበው”25 ማለት ምን እንደሆነ ለመረዳት ችለዋል።
በቤተመቅደስ ውስጥ ካህኖች ለሌሎች የመጠመቅ ስነስርዓቶችን መፈጸም እንደሚችሉ ታውቃላችሁ። የ17 ዓመት ወንድ ልጄ ለተወሰኑ ዘሮቼ አጠመቀኝ። ሁለታችንም ለአሮናዊ ክህነት እና ለእግዚአብሔር ልጆች ደህንነት መተግበር መቻል ጥልቅ የሆነ ምስጋና ተሰማን።
ወጣቶች፣በክህነት ሀላፊነቶቻችሁ በትጋት ስታገለግሉ፣ እናንተም “የሰውን አለሟችነት እና የዘለአለም ህይወት ለማምጣት”26 በሆነው በእግዚአብሔር ስራ እየተሳተፋችሁ ናችሁ። እንደእዚህ አይነት ልምምዶች ፍላጎታችሁን ያሳድጉታል እናም እንደ ወንጌል ሰባኪዎች ንስሀ ለማስተማር እና ተቀያሪዎችን ለመጠቅ ያዘጋጇችኋል። እነርሱም ደግሞ በእልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ ለህይወት ሙሉ አገልግሎት ያዘጋጇችኋል።
መጥምቁ ዮሀንስ፣ ምሳሌአችን
የአሮን ክህነት ተሸካዎች፣ እኛ ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር አገጋዮች የመሆን እድልና ሃላፊነት አለን። ዮሐንስ ስለክርስቶስ እንዲመሰክር እና ሁሉንም ንስሃ እንዲገቡ እና እንዲጠመቁ እንዲጋብዝ ስልጣን እንደተሰጠው መልዕክተኛ ተላከ። ያ ማለት ስለተወያየንበት የአሮናዊ ክህነት ቁልፍ ተለማመደ ማለት ነው። ዮሐንስ ከዚያም አወጀ፣ “እኔስ ለንስሃ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፣ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ … እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳት ያጠምቃችኋል”27
ስለዚህ የአሮናዊ ክህነት፣ ከመላዕክት አገልግሎት ጋር፣ የማዘጋጃ ወንጌሉን ማገልገል፣ ለእግዚአብሔር ልጆች በመልከጸዴቅ ክህነት አማካኝነት በዚህ ሕይወት ውስጥ ከምንቀበላቸው ታላቅ ስጦታዎች ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን እንዲቀበሉ መንገዱን ያዘጋጃል።28
ለአሮናዊ ክህነት ተሸካዎች እግዚአብሔር ምን ዓይነት ከፍተኛ ሃላፊነትን ነው የሰጠው!
ግብዣና ቃል-ኪዳን
ወላጆችና የክህነት ተሸካሚዎች፣ የፕሬዘዳንት ሞንሰንን “የእግዚአብሔርን ክህነት ተሸካሚ መሆን ምን ማለት እንደሆነ” የሚለውን ምክር ጠቀሜታ ይሰማችኋን?29 የአሮናዊ ክህነትን መረዳት እና ማጉላት አማኝ የመልከጸዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች፣ ኃይል የተሞሉ ሚስዮኖች እና ፃድቅ ባሎችና አባቶች እንዲሆኑ ልንሰጣቸው የምንችለው ማዘጋጃ ነው። በአገልግሎታቸው አማካኝነት፣ ለእግዚአብሔር ልጆች ደህንነት በክርስቶስ ስም የመተግበር የክህነት ኃይልን እውንነት ይረዳሉ እናም ይሰማቸዋል።
ወጣት ወንዶች፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ስራ አለው።30 የእናንተ የአሮናዊ ክህነት ሹመት የእርሱ ልጆች የክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ ኃይል ለመቀበል የመርዳት ማዕከላዊ ነው። እነዚህን ቅዱስ ሃላፊነቶች የሕይወታችሁ ማዕከላዊ ስታደርጉት የእግዚአብሔርን ኃይል በበለጠ እንደሚሰማችሁ ቃል እገባለሁ። ስራውን እንዲተገብር ቅዱስ በሆነ ጥሪ እንደተጠራ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ማንነታችሁን ትረዳላችሁ። እናም፣ እንደ መጥምቁ ዮሀንስ፣ለልጁ መምጣት መንገድን ታዘጋጃላችሁ። ስለዚህ እውነታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።