ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፲፫


ክፍል ፲፫

በግንቦት ፲፭፣ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ አጠገብ ስለነቢዩ እና ኦሊቨር ካውድሪ የአሮናዊ የክህነት ሹመት ሥርዓት አፈፃጸም ታሪክን የሚናግር ከጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ውስጥ የተውጣጣ ምንባብ። የሹመቱ ስርዓት የተከናወነው በአዲስ ኪዳን መጥምቁ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራ በነበረው፣ እራሱን ዮሐንስ ብሎ በገለጸው መልአክ እጅ ነበር። መልአኩ ይህንን ስርዓት ያከናወነው የመልከ ጼዴቅ ክህነት የሚባለውን የታላቁን ክህነት ቁልፍ በያዙት ጴጥሮስ፣ ያእቆብ፣ እና ዮሐንስ ተብለው በተጠሩት የጥንት ኃዋሪያት ስር በመሆን እንደነበረ ገልጿል። በተገቢው ጊዜ ይህ ከፍተኛ ክህነት እንደሚሰጣችው ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውድሪ የተስፋ ቃል ተሰጥቷቸው ነበር። (ክፍል ፳፯፥፯–፰፣ ፲፪ን ተመልክቱ።)

የአሮናዊ ክህነት ቁልፎች እና ሀይላት ተዘርዝረዋል።

አገልጋይ ባልንጀሮቼ፣ የመላእክትን፣ እና የንስሀን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት ቁልፎች የያዘውን የአሮንን ክህነት በመሲሁ ስም ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፤ እናም የሌዊ ወንድ ልጆች ዳግም መስዋዕት ለጌታ በጽድቅ እስኪሰዉ ድረስ ይህ ከምድር ላይ ዳግመኛ በፍጹም አይወሰድም።