ምዕራፍ ፳፫
የባቢሎን ጥፋት በዳግም ምፅአት የሚኖረው ጥፋት ምልክት ነው—የቁጣና የበቀል ቀን ይሆናል—ባቢሎን (አለም) ለዘለዓለም ትወድቃለች—ኢሳይያስ ፲፫ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስ የተመለከተው ሀየባቢሎን ለሸክም።
፪ ከፍ ባሉ ተራራ ላይ ሀአርማን አቁሙ፣ ድምፃችሁንም ወደ እነርሱ ከፍ አድርጉ፣ ወደ ልዑላት ደጃፍ ይሄዱ ዘንድ ለጠቁሙአቸው።
፫ ሀቅዱሳኖቼን አዝዤአለሁ፣ ኃያላኖችንም ጠርቻቸዋለሁ፣ ቁጣዬ በእኔ ታላቅነት በሚደሰቱት ላይ አይደለችምና።
፬ በተራሮቹ ያሉት ህዝቦች ጩኸት እንደ በርካታ ሰዎች ነው፣ ከመጠን በላይ የሚንጫጩ ሀገሮች ሀመንግስታት ተከማችተዋል፣ የሰራዊት ጌታ የጦር ሰራዊቱን ለይሰበስባል።
፭ እነርሱ፣ አዎን፣ ጌታ እና የእርሱ የቁጣው መሳሪያ ምድርን ሊያጠፋት ከሩቅ ሀገር፣ ከሰማይ ዳርቻም መጥተዋል።
፮ የጌታ ቀን ቀርባለችና አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚገዛ እንደጥፋት ትመጣለች።
፯ ስለዚህ ሁሉም እጆች ይዝላሉ፣ የሁሉም ሰዎች ልብ ትቀልጣለች።
፰ እናም እነርሱ ይፈራሉ፣ ኃይለኛ ህመምና ሀዘንም ይይዛቸዋል፤ አንዱም በሌላው ይደነቃል፤ ፊቶቻቸው በእፍረት እንደነበልባል ይሆናሉ።
፱ እነሆ፣ ጨካኝ በሆነ ቁጣና ከኃይለኛ ንዴት ጋር ምድርን ባድማ ሊያደርጋት የጌታ ቀን ይመጣል፤ ኃጢአተኞችንም ከውስጧ ሀያጠፋል።
፲ የሰማይ ከዋክብትና ህብር ከዋክብቶች ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ሀፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
፲፩ እናም ዓለምን በመጥፎ ስራዋ፣ ክፉዎችንም ለግፍ ስራቸው ሀእቀጣለሁ፤ ለየትዕቢተኞችንም ኩራት አስቆማለሁ፣ የጨካኞችንም ኩራት አዋርዳለሁ።
፲፪ ሀሰውንም ከነጠረ ወርቅ የበለጠ የከበረ አደርገዋለሁ፤ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።
፲፫ ስለዚህ፣ በሰራዊት ጌታ መዐት እናም በታላቁ ቁጣው ቀን እኔ ሰማያትን አናውጣለሁ ምድርንም ከቦታዋ ሀፈቀቅ አደርጋታለሁ።
፲፬ እናም ሀእንደሚሳደድ ድብ፣ ማንም ሰው እንደማይሰበስባቸው በጎች ይሆናሉ፤ እናም ሁሉም ሰው ወደ ራሱ ህዝብ ይዞራል፣ እናም ሁሉም ወደ ራሱ ምድር ይሸሻል።
፲፭ የሚኮራ ሰው ሁሉ ይወጋል፣ አዎን፣ ከኃጢአተኞች የተቀላቀለ ሰው ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።
፲፮ ልጆቻቸውም በዐይኖቻቸው ፊት ይከሰከሳሉ፤ ቤቶቻቸው ይበዘበዛል፣ ሚስቶቻቸውም ይደፈራሉ።
፲፯ እነሆ፣ ብር እና ወርቅ የማይሹትንና በዚህም የማይደሰቱትን ሜዶናውያንን በላያቸው አስነሳለሁ።
፲፰ ፍላፃዎቻቸውም ወጣቶቻቸውን ይጨፈጭፏቸዋል፤ ለማህፀኑም ፍሬ ምህረት አይኖራቸውም፤ ዐይኖቻቸውም ህፃናትን በህይወት አይተዉም።
፲፱ እናም የመንግስታት ክብር፣ የከለዳውያን ሀቆንጆ ክቡር የሆነችው ባቢሎን እግዚአብሔር ለሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደነበረ ትሆናለች።
፳ ለዘለዓለም ሀየሚቀመጥባት አይገኝም፣ ከትውልድ እስከትውልድም የሚኖርባት አይኖርም—አረባውያንም ቢሆኑ ድንኳኑን በዚያ አይተክልም፤ እረኞችም ቢሆኑ እንኳ መንጋቸውን በዚያ አያሰማሩም።
፳፩ ነገር ግን የበረሃ ሀየዱር አራዊት በዚያ ያርፋሉ፤ ሰጎኖችም ቤቶቻቸውን ይሞሉታል፣ ጉጉቶችም በዚያ ይኖራሉ፤ ለአጋንንትም በዚያ ይጨፍራሉ።
፳፪ እናም የደሴቶቹ አውሬዎች በባዶ ሀቤቶቻቸው፣ ለቀበሮዎችም በአስደሳች ስፍራዎቻቸው ይጮሃሉ፤ እናም ጊዜዋ ቀርቧል፣ ቀኗም አይራዘምም። እኔ በፍጥነት አጠፋታለሁና፤ አዎን፣ እኔ ለህዝቦቼ መሃሪ እሆናለሁና፣ ነገር ግን ኃጢአተኞች ይጠፋሉ።