ምዕራፍ ፲፱
ኢሳይያስ ስለመሲሁ ተናገረ—በጨለማ ያለ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ያያል—ህፃን ልጅ ተወልዶልናል—እርሱም የሠላም አለቃ ይሆናል በዳዊትም ዙፋን ላይ ይነግሳል—ኢሳይያስ ፱ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ ይሁን እንጂ፣ ጭጋግም በጭንቀት በነበረሽ አይነት አይሆንም፣ በመጀመሪያ ሀየዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር በቀላል መታ፣ እና በኋላ ግን በዮርዳኖስ በስተጀርባ ያሉትን የገሊላ ሀገሮች በቀይ ባህር አምርሮ መታ።
፪ ሀበጨለማ የሄደ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድርም ለኖሩት ብርሃን ወጣላቸው።
፫ ህዝብህን አብዝተሃል፣ ደስታንም ሀጨምረሃል—በመከር ደስ እንደሚላቸው፣ እና ምርኮንም ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሰዎች በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
፬ አንተም የሸክሙን ቀንበር፣ የጫንቃውንም በትር፣ የአስጨናቂውንም በትር ሰብረሃልና።
፭ ሁሉም የተዋጊው ጦርነት በሁከት የተሞላ ነውና፣ እናም ልብሶች በደም ተጨማልቀዋል፤ ነገር ግን ይህኛው በመቃጠልና በእሳት ማቃጠያ ይሆናል።
፮ ሀህፃንም ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ ለአለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ፣ መካሪ፣ ሐሀያል አምላክ፣ መየዘለአለም አባት፣ ሠየሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
፯ ከዛሬ ጀምሮ እስከዘለዓለም ድረስ በፍርድና በፅድቅ ያፀናውና ይደግፈው ዘንድ፣ በዳዊት ዙፋንና ሀበመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ ለአይኖረውም። የሰራዊት ጌታ ቅንዐት ይህንን ያደርጋል።
፰ ጌታ ቃሉን ለያዕቆብ ላከ ሀበእስራኤልም ላይ ወደቀ።
፱ እናም ሁሉም ህዝብ ኤፍሬምም ቢሆን እንኳ እናም የሰማርያ ሰዎች፣ በትዕቢትና በኩራት እንዲህ የሚሉት ሁሉ ያውቃሉ፤
፲ ጡብ ወድቋል፣ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሰራለን፣ የሾላው ዛፍ ተቆርጦአል፣ ነገር ግን በዝግባ እንተካዋለን።
፲፩ ስለዚህ ጌታ ሀበረአሶን ላይ ጠላቶችን ያስነሳል፣ ጠላቶቹንም በአንድነት ይሰበስባል።
፲፪ ሶርያን ከፊትና ፍልስጤምን ከኋላ፤ እናም እስራኤልን በተከፈተ አፍ ሀይበሉአታል። በዚህ ሁሉ እንኳን ለቁጣው አልበረደችም፣ ነገር ግን አሁንም እጁን እንደዘረጋ ነው።
፲፫ ወደ እርሱ ሀያልተመለሱት ተመተዋልና፣ የሰራዊት ጌታንም አልፈለጉም።
፲፬ ስለዚህ ጌታ ራስንና ጅራትን፣ ቅርንጫፍና እንግጫን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቆርጣል።
፲፭ ሽማግሌው እርሱ ራስ ነው፣ ሀሰትን የሚያስተምረው ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።
፲፮ የዚህ ህዝብ መሪዎች ህዝቡን እንዲሳሳት ያደርጉታልና፣ እናም ተመሪዎቹ ደግሞ ይጠፋሉ።
፲፯ ሰው ሁሉ ግብዝና ክፉ ሰሪ ነውና፣ አፉም ሁሉ ሀስንፍናን ይናገራልና፣ ስለዚህ ጌታ በወጣቶቻቸው ደስ አላለውም፣ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶችም ለምህረት አይኖረውም። በዚህም ሁሉ እንኳን ቁጣው አልበረደለትም፣ ነገር ግን ሐእጁ ገና ተዘርግታለች።
፲፰ ኃጢያት እንደእሳት ትቃጠላለችና፤ ይህም ኩርንችቱንና እሾህንም ትበላለች፣ እና ጥቅጥቅ ያለውንም ጫካ ታቃጥላለች፣ እናም እንደጢስም ወደ ላይ ይነሳሉ።
፲፱ በሰራዊት ጌታ ቁጣ የተነሳ ምድር ትጨልማለች፣ ሰዎች ለእሳቱ እንደማገዶ ይሆናሉ፣ ሀማንም ሰው ወንድሙን አያድንም።
፳ እና እርሱ በቀኙ እጅ ይመነጭቃልና ይራብማል፤ በግራ እጅም ሀይበላል አይጠግቡምም፤ እያንዳንዱም የራሱን ክንድ ስጋ ይበላል—
፳፩ ሀምናሴ፣ ለኤፍሬም፤ እናም ኤፍሬም፣ ምናሴ፤ እነርሱ በአንድነት ሐበይሁዳ ላይ ይነሳሉ። ይህም ሁሉ ተፈፅሞ እንኳን ቁጣው ገና አልበረደችምና፣ ነገር ግን አሁንም እጁ ተዘርግታለች።