ምዕራፍ ፰
ያዕቆብ ከኢሳይያስ ማንበብ ቀጠለ፥ በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ ጌታ ፅዮንን ያፅናናል እንዲሁም እስራኤልን ይሰበስባል—የዳኑትም ወደ ፅዮን በታላቅ ደስታ ተከበው ይመጣሉ—ኢሳይያስ ፶፩ እና ፶፪፥፩–፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናንተ ፅድቅን የምትከተሉ ስሙኝ። የተቆረጣችሁበትን ሀድንጋይ፣ እንዲሁም የተቆፈራችሁበትን ጉድጓድ ተመልከቱ።
፪ ወደ ሀአባታችሁ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ለሣራ ተመልከቱ፤ ብቻውን ጠራሁት፣ እናም ባረክሁትም።
፫ ጌታ ሀፅዮንን ያፅናናል፣ በእርሷ ባድማ የሆነውን ቦታ ሁሉ ያፅናናል፤ እናም ለምድረበዳዋንም እንደ ዔድን፣ እናም በረሃዋን እንደ ጌታ የአትክልት ስፍራ ያደርገዋል። ደስታና ተድላ፣ ምስጋና እና የዝማሬ ድምፅ ይገኝባታል።
፬ ሕዝቤ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ወገኔ ሆይ፣ ስሙኝ፤ ሀህግ ከእኔ ይወጣልና፣ እና ፍርዴን ለህዝብ እንደ ለብርሃን እንዲያርፍ አደርጋለሁ።
፭ ፅድቄ ቀርቧል፤ ሀማዳኔም ወጥቷል፣ እናም ክንዴ በህዝቡ ይፈርዳል። ለደሴቶች እኔን ይጠባበቃሉ፣ እናም በክንዴ ይታመናሉ።
፮ ዐይኖቻችሁን ወደ ሀሰማያት አንሱ፣ እናም ወደታች ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደጢስ በንነው ለይጠፋሉ፣ ምድርም እንደልብስ ሐታረጃለች፤ እናም የሚኖሩባት እንዲሁ ይሞታሉ። ነገር ግን ማዳኔ ለዘለዓለም ይሆናል፣ ፅድቄም አይፈርስም።
፯ ፅድቅን የምታውቁ፣ ህጌንም በልባችሁ የፃፍኩባችሁ እኔን አድምጡኝ፣ የሰዎችን ዘለፋ አትፍሩ፣ ወይም ስድባቸውንም ሀአትፍሩ።
፰ እንደልብስም ብል ይበላቸዋልና፣ እናም ትል እንደሱፍ ይበላቸዋል። ነገር ግን ፅድቄ ለዘለዓለም፣ እናም ማዳኔ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናል።
፱ የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ! ተነስ! ሀኃይልንም ልበስ፣ እንደጥንቱ ቀናት ተነሳ። ረዓብን የቆራረጥክ፣ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
፲ ባህሩን፣ የታላቁን ጥልቅ ውሃ ያደረቅህ፣ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጥልቁን ባህር ሀመንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?
፲፩ ስለዚህ፣ ጌታ ሀያዳናቸው ይመለሳሉ፣ ለበዝማሬም ወደ ፅዮን ይመጣሉ፤ እናም የዘለዓለም ደስታና ቅዱስነት በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ እናም ደስታና ተድላን ያገኛሉ፤ ሀዘንና ሐልቅሶም ይሸሻሉ።
፲፪ ሀእኔ እርሱ ነኝ፤ የማፅናናችሁ እኔ ነኝ። እነሆ፣ የሚሞተውን ሰውና ለእንደሳርም የሚሆነውን የሰው ልጅ ሐትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?
፲፫ እናም ሰማያትን የዘረጋውንና፣ የምድርን መሰረት የሰራውን፣ ጌታ ፈጣሪህን ሀረሳህ፣ እናም ሊያጠፉህ የተዘጋጁ ይመስል በአስጨናቂዎችህ ቁጣ ምክንያት ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈራህ? እናም የአስጨናቂዎችህ ቁጣ የት አለ?
፲፬ ምርኮኛ እንዲፈታ፣ እና እርሱ በጉድጓድ እንዳይሞት፣ ወይም እንጀራም አይጐድልበት ይፈጥናል።
፲፭ ነገር ግን ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን ሀየማናውጥ ጌታ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ስሜም የሰራዊት ጌታ ነው።
፲፮ እናም ሰማያትን እዘረጋና ምድርንም እመሰርት ዘንድ፣ እናም ለፅዮን፣ እነሆ፣ አንቺ ሀህዝቤ ነሽ እንድላት ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፣ እንዲሁም በእጄ ጥላ ጋርጄሃለሁ።
፲፯ ከጌታ እጅ ሀየቁጣውን አተላ ለበፅዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ ንቂ፣ ንቂ፣ ቁሚ፣ ከሚያንገደግድ ዋንጫ መራራን ጠጥተሻል—
፲፰ እናም ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል የሚመራትም የለም፤ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።
፲፱ እነዚህ ሁለቱ ሀወንዶች ልጆች ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ ላንቺ ማን ያዝንልሻል—መደምሰስሽና መውደምሽ፣ ረሃብና ሰይፍም—እንዲሁም በማን አፅናናሻለሁ?
፳ ከእነዚህ ከሁለቱ በስተቀር ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በአደባባይ ላይ ተኝተዋል፤ በወጥመድ እንዳለ የሜዳ ኮርማ በጌታ ቁጣ፣ በአምላክሽ ተግሳፅ ተሞልተዋል።
፳፩ ስለዚህ አሁን ይህን ስሚ፣ አንቺ ተሰቃዪና ያለ ወይን ጠጅ ሀየሰከርሽ፥
፳፪ ጌታሽ ይላል፣ ጌታ እና አምላክሽ የወገኑ ጉዳይ ሀይማፀናል፤ እነሆ፣ የሚያንገደግድን ፅዋ፣ የቁጣዬንም ዋንጫ አተላውን ከእጅሽ ወስጃለሁ፣ ደግመሽም ከእንግዲህ አትጠጪውም።
፳፫ ነገር ግን ነፍስሽን እንሻገር ዘንድ ዝቅ በይ በሚሉት በአስጨናቂዎችሽ እጅ ሀአኖረዋለሁ፥ እናም ሰውነትሽንም ለሚሻገሩበት እንደ መሬት መንገድ አድርገሽ ዘርግተሽዋል።
፳፬ ሀፅዮን ሆይ ለንቂ፣ ንቂ ሐሀይልሽን ልበሺ፤ ቅድስት ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ቆንጆ ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘና እርኩስ ከእንግዲህ መአይገባብሽምና።
፳፭ ትቢያን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ሀተነሺ፣ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የፅዮን ሴት ልጅ ሆይ የአንገትሽን ለእስራት እራስሽ ፍቺ።