ምዕራፍ ፳፬
እስራኤል ትሰበሰባለች፣ የሺህ ዓመት እረፍትን ትደሰትበታለች—ሉሲፈር በአመፅ ምክንያት ከሰማይ ተጥሏል—እስራኤል ባቢሎንን (ዓለምን) ድል ታደርጋታለች—ኢሳይያስ ፲፬ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ ጌታ በያዕቆብ ላይ ምህረቱን ያወርዳልና፣ በድጋሚም እስራኤልን ሀይመርጣል፣ በራሳቸውም ምድር ላይ ያኖራቸዋል፤ ለእንግዳዎቹም ከእነርሱ ጋር ይገናኛሉ፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።
፪ ሀእናም ህዝቡ ይዘው ወደ ራሳቸው ቦታ ያመጧቸዋል፤ አዎን፣ ከሩቅም እስከምድር ዳርቻም፤ እናም ወደ ለቃል ኪዳን ምድራቸውም ይመለሳሉ። የእስራኤልም ቤት ባለቤት ያደርጓቸዋል፣ እናም የጌታ ምድር እንደ ወንድና ሴት ሐገረዶች ይሆናሉ፤ የማረኩአቸውንም ይማርካሉ፤ እናም ጨቋኞቻቸውን ይገዛሉ።
፫ እናም በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል ጌታ ከሀዘናችሁ፣ ከፍርሃታችሁም፣ እናም ከአስከፊው እንድታገለግሉ ከተደረጋችሁባት ባርነት ሀእረፍት ይሰጣችኋል።
፬ እናም በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ይህንን ምሳሌ ሀበባቢሎን ንጉስ ላይ አንስታችሁ እንዲህ ትላላችሁ—አስጨናቂው እንዴት ፀጥ አለ፣ ወርቃማዋስ ከተማ እንዴት አረፈች!
፭ ጌታ የኃጥአንን በትር፣ የመሪዎችንም ዘንግ ሰብሯል።
፮ ህዝቡን ያለማቋረጥ በጭካኔ የመታ፣ ሀገሮችን በቁጣ የመራ፣ ስደት ይሆንበታል፣ እናም ማንም አያስጥለውም።
፯ መላው ምድር እረፍት ላይ ነው፣ ፀጥታም ሆኖአል፣ ሀበዝማሬም ተነስተዋል።
፰ አዎን፣ ሀጥድና የሊባኖስ ዝግባ አንተ ለከተጋደምክ ጀምሮ ማንም ሐይቆርጠን ዘንድ አልመጣብንም ብለው በአንተ ደስ አላቸው።
፱ ሀሲኦል ከበታች አንተ በመምጣትህ ልትገናኝህ ታወከች፤ ለየሞቱትንም የምድር ታላላቆች ለአንተ አንቀሳቀሰች፤ የሃገሮችን ነገስታቶች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ለአንተ አስነሳች።
፲ ሁሉም ይናገራሉ ለአንተም እንዲህ ይላሉ—አንተም ደግሞ እንደ እኛ ደካማ ሆንክን? አንተ ልክ እንደ እኛ ሆንክን?
፲፩ ውበትህ ወደ መቃብር መጥቷል፤ የበገናህም ድምፅ አይሰማም፤ ብል ከበታችህ ተነጥፏል፣ ትልም ይሸፍንሃል።
፲፪ አቤቱ ሀሉሲፈር፣ አንተ የንጋት ልጅ ሆይ! ለእንዴት ከሰማይ ወደቅህ? አንተ ሀገሮችን ያዋረድክ፣ እንዴት ከምድር በታች ተቆረጥህ!
፲፫ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ሀአርጋለሁ፣ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ አደርጋለሁ፤ ለበሰሜን ዳርቻም በመሰብሰቢያውም ተራራ ደግሞ እቀመጣለሁ፤
፲፬ ከደመናዎችም ከፍታ በላይ አርጋለሁ፤ እንደ ልዑልም እሆናለሁ ብለሃል።
፲፭ ነገር ግን ወደ ሲዖል፣ ወደጥልቁም ሀጉድጓድ ትወርዳለህ።
፲፮ የሚያዩህም ሀያተኩሩብሃል፣ ያስተውሉሀልም፣ እናም ይላሉ—ምድርን ያንቀጠቀጠ፣ መንግስታትን ያናወጠ ሰው ይህ ነውን?
፲፯ እናም ዓለምን ምድረበዳ ያደረገ፣ ከተሞቿንም ያጠፋ፣ የእስረኞቹንም በር ያልከፈተው ይህ እርሱ አይደለምን?
፲፰ የሁሉም ሀገሮች ንጉሶች፣ አዎን፣ ሁላቸውም፣ እያንዳንዳቸውም ሀበየቤታቸው በክብር አንቀላፍተዋል።
፲፱ ነገር ግን አንተ ሀእንደረከሰ ቅርንጫፍ፣ በሰይፉም ተወግተው እንደተገደሉት፣ ወደ ጉድጓዱ ለድንጋዮች አዘቅት እንደወረዱት ቅሪቶች በእግሮች ስር እንደተረገጠም ሬሳ ከመቃብርህ ተጥለሃል።
፳ ምድርህን አጥፍተሀልና ህዝብህንም ገድለሀልና፤ ከእነርሱ ጋር በመቃብር አንድ አትሆንም፣ ሀየክፉ አድራጊዎች ለዘር በፍፁም አይከበርም።
፳፩ እንዳያንሰራሩም ምድሪቷንም እንዳይዙ፣ የምድርንም ገፅ በከተሞቻቸው እንዳይሞሉ፣ በአባቶቻቸው ሀኃጢያት ምክንያት ልጆቹን ለግድያ አዘጋጁ።
፳፪ እኔም በእነርሱ ላይ እነሳለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ እናም ከባቢሎን ሀስምና ቅሪት ዘርንና ወንድ ልጅንና ለየወንድምን ወይም የእህትን ልጅ እቆርጣለሁ ይላል ጌታ።
፳፫ የጃርት ሀመኖሪያ የውሃም መቆሚያ አደርጋለሁ፤ በጥፋትም ለመጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ።
፳፬ የሰራዊት ጌታ እንዲህ ሲል ምሏል—በእርግጥም እኔ እንዳቀድኩት ይሆናል፤ እኔ እንደወሰንኩትም ይቆማል—
፳፭ ሀአሶርን በምድሬ አመጣታለሁ፣ ለበተራራዬም ላይ በእግሬ ስር እረግጠዋለሁ፤ ከዚያም ሐቀንበሩ ከእነርሱ ላይ ይወርዳል፣ ሸክሙም ከትከሻቸው ይወርዳል።
፳፮ በምድር ላይ ሁሉ የታቀደው ዕቅድ ሀይህ ነው፤ እናም በሃገር ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይህ ነው።
፳፯ የሰራዊት ጌታ ይህንን አቅዶአል፣ የሚያከሽፈውስ ማነው? እጁም ተዘርግታለች የሚያስመልሳትስ ማነው?
፳፰ ንጉስ ሀአካዝ በሞተበት ለዘመን ይህ ሸክም ነበር።
፳፱ እናንተ ፍልስጤም ደስ አይበላችሁ፣ ምክንያቱም እናንተን የመታው በትሩ ተሰብሯል፤ ከእባቡ ስር እፉኝት ይመጣል፣ ፍሬውም የሚበር ቁጡ እባብ ይሆናል።
፴ እናም የድሆች በኩር ይመገባል፣ ችግረኞችም በሰላም ይኖራሉ፤ እኔም ስራችሁን በረሃብ እገድላለሁ፣ እርሱ ደግሞ ቅሪቶቻችሁን ይገድላል።
፴፩ አንተ መግቢያ ሆይ ወዮ በል፤ አንቺ ከተማ ሆይ አልቅሺ፤ ፍልስጤም ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣልና፣ እናም በእርሱ ቀነ ቀጠሮ ጊዜያት ማንም ብቸኛ አይሆንም።
፴፪ እንግዲህ ለሀገር መልዕክተኞች ምን ይመለሳልን? ጌታ ሀፅዮንን እንደመሰረተና፣ የሀገሮቹም ለድሆች በውስጧ ሐእንደሚጠጉ ነው።