2010–2019 (እ.አ.አ)
የሚቀጥል ራዕይ
ኦክተውበር 2014


የሚቀጥል ራዕይ

የህይወት አስፈላጊ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሰው ፍርድ ወይም ምክንያታዊ አስተሳሰብ በቂ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ከእግዚአብሔር መገለጥ ያስፈልገናል።

ዛሬ ለእኛ ያለኝ ተስፋ ከእግዚአብሔር ፍቅር እና ብርሀን እንዲሰማን ነው። ዛሬ ያ የሰማይ አባታችን የግል መገለጥ በረከት በጣም የሚያስፈልጋቸው ብዙዎች እየደመጡ ነው።

ለሚስኦን ፕሬዘዳንቶች፣ ትግል ላይ ያለን ሚስኦናዊ እንዴት ማበርታት እንደሚቻል ለማወቅ ጽኑ ጸሎት ሊሆን ይችላል። በአለም ውስጥ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ አባት ወይም እናት፣ ቤተሰባቸውን ደህንነት ወዳለበት ቦታ ማዘዋወር ወይም እዚያው ያሉበት መቆየት እንዳለባቸው ማወቅ በጣም ይፈልጋሉ። የጠፋውን በግ በማዳን ጌታን እንዴት መርዳት እንዳለባቸው ለማወቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ የካስማ ፕሬዘዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሶች ዛሬ ጸሎጽ ላይ ናቸው። እና ለነብይ፣ ለቤተክርስቲያን እና በማጥ ውስጥ ላለ አለም ጌታ ምን እንዲል እነደሚፈልግ ማወቅ ይፈልጋል።

የህይወት አስፈላጊ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሰው ፍርድ ወይም ምክንያታዊ አስተሳሰብ በቂ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ከእግዚአብሔር መገለጥ ያስፈልገናል። እና በጭንቀት ጊዜ አንድ ብቻ መገለጥ አይደለም የሚያስፈልገን፣ ነገር ግን በቀጣይነት የሚታደስ መሆን አለበት። አንድ ብቻ የብርሀን እና የምቾት ብልጭታ ብቻ አይደለም የሚያስፈልገን፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ቀጣይ የመነጋገር በረከት ያስፈልገናል።

የቤተክርስቲያኑ የመኖር መነሻ ወጣት ልጅ እውነታውን ከማወቁ የመነጨ ነው። ወጣቱ ዮሴፍ ስሚዝ የትኛውን ቤተክርስቲያን መቀላቀል እንዳለበት በራሱ ማወቅ እንደማይችል አውቆ ነበር። የያዕቆብ መጽሀፍ ማድረግ ትችላለህ እነዳለው እግዚአብሔርን ጠየቀ። አብ እና ልጁ በዛፎች ውስጥ ተገለጡለት። ለመመለስ ከዮሴፍ አቅም በላይ የነበረውን ጥያቄ መለሱ።

ከዛም እውነተኛውን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንዲያቋቋም በእግዚአብሔር መጠራት ብቻም ሳይሆን፣ ነገር ግን በዚያም ከእግዚአብሔር መገለጥን ቀጣይ የሚያደርግ መንፈስ ቅዱስ የማስነሳት ሀይልንም መለሰ።

እውነተኛውን ቤተክርስቲያን የሚለየውን ይንን ምልክት ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዲህ ገልጾታል፤ “ነብዩ ለቤተክርስቲያኑ” ፕሬዘዳንት ለካስማው፣ ለሚስኦኑ፣ ወይም ጉባኤው፤ ኤጲስ ቆጶሱ ለአጥቢያው፣ አባት ለቤተሰቡ፤ ግለሰብ ለእራሱ በመቀበል፣ መገለጥ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቀጥሏል።”1

ያ ድንቁ የመገለጥ ሂደት እኛ ግላዊ መገለጥ ስንቀበል ይጀምራል፣ ያልቃል፣ እና ይቀጥላል። የሌሂ ልጅ፣ ታላቁ ኔፊን እንደ ምሳሌያችን አድርገን እንውሰድ። አባቱ ህልም ታይቶት ነበር። ሌሎቹ የኔፊ ቤተሰቦች ህልሙን እንደ የአእምሮ ግራ መጋባት አመልካች አዩት። የህልሙ ክፍል ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር ይዘውት እንዲሄዱ የሌሂ ወንድ ልጆች በመጥፎው ስጋት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ እና የእግዚአብሔርን ቃል የያዙትን መዛግብቱን እንዲያመጡ የእግዚአብሔር ትእዛዝን ያካተተ ነበር።

አባታቸው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ሲያዛቸው የነበረውን የኔፊን ቆራጥ አዋጅ በየጊዜው እንጠቅሳለን። ቃላቶቹን ታውቋቸዋላችሁ፤ “እሄዳለሁ እና ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ።2

ኔፊ እነዚህን ቃላት መናገሩን ሌሂ ሲሰማ፣ ቅዱስ መጽሀፍ በ“ታላቅ ደስታ” እንደነበር ይናገራል።3 የተደሰተው ህልሙ ከእግዚአብሔር ጋር በእውነት መነጋገር እንደነበረ በሚያረጋግጠጥ መገለጥ ኔፊ እንደተባረከ በማወቁ ነበር። ኔፊ፣ “እሄዳለሁ እና አባቴ አድርግ ያለኝን አደርጋለሁ” አይደለም ያለው። በምትኩ እንዲህ አለ፣ “እሄዳለሁ እና ጌታ የዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለዉ።”

በራሳችሁ የቤተሰብ ተሞክሮአችሁ፣ ሌሂ ለምን “በታላቅ ደስታ” እንደነበረ ታውቃላችሁ። ደስታው የመጣው ኔፊ የማረጋገጫ መገለጥን መቀበሉን በማወቁ ነው።

ብዙ ወላጆች ወጣት ልጆች ምሽት ወደቤት መመለስ ስላለባቸው ጊዜ የቤተሰብ ህጎችን ያወጣሉ። ነገር ግን ልክ በቅርብ አንድ ወላጅ እንደተማረው፣ ከቤት የሄደች አንድ ልጅ ለራሷ ገደብ ማውጣት ብቻ ሳይሆን ልክ እቤት እንደተማረችው ሰንበትን መጠበቋን ሲያውቁ የሚሰማቸውን ደስታ አስቡት። የወላጅ መገለጥ በልጅ የሚቀጥለው ግላዊ መገለጥ ላይ የማያልቅ ተጽእኖ አለው።

እናቴ ያንን የመገለጥ መርህ በእርግጥም ገብቷት ነበር። እንደ ወጣት፣ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት ስመጣ ቀስ ብዬ የኋላውን በር እዘጋ ነበር። ወደ እራሴ ክፍል መንገድ ላይ የእናቴን መኝታ ክፍል ማለፍ ነረብኝ። እንዴትም በጸጥታ ብሄድ፣ በእርሷ ግማሽ ክፍት በር ስደርስ፣ በጣም በዝግታ ድምጼ ሲጠራ እሰማለሁ፣ “ሀል፣ እንዴ ግባ እስቲ።”

እገባና በአልጋዋ ጠርዝ ላይ እቀመጣለሁ። ክፍሉ ይጨልማል። ብትሰሙት፣ ስለ ህይወት የጓደኝነት ንግግር ብቻ ነበር የሚመስለው። ነገር ግን እስከ ዛሬ፣ የፓትሪያርክ በረከቴን ጽሁፍ ሳነብ በሚሰማኝ ሀይል፣ እሷ ያለችኝ ወደ አይምሮዬ ተመልሶ ይመጣል።

በእነዚያ ምሽቶች እኔን እየጠበቀች በጸሎት ምን ስትጠይቅ እንደነበረ አላውቅም። በከፊል ስለ ደህንነቴ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። ነገር ግን ቡራኬ ከመስጠቱ በፊት ፓትሪያርክ እንደሚጸልየው መጸለዩዋን እርግጠኛ ነኝ። እንደ እሱ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ቃላቱ ለተቀባዩ እንዲደርስ ይጸልያል። ለዚያ በረከት የእናቴ ጸሎት በጭንቅላቴ ውስጥ ተመልሷል። በመንፈስ አለም ውስጥ ነች እና ላለፉት 40 አመታትም እዚያ ነበረች። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንደጠየቀችው እኔ በመስማት በመባረኬ በጣም ደስተኛ እንደነበረች እርግጠኛ ነኝ። እኔም ደሞ ለመሄድ እና እርሷ ተስፋ እንዳደረገችው ለማድረግ ሞክሬያለሁ።

ያንን ተመሳሳይ የመገለጽ መቀጠል ተአምር በካስማ ፕሬዘዳንት እና ኤጲስ ቆጶስ በቤተክርስቲያን ውስጥም ተመልክቻለሁ። እና፣ በቤተሰብ መሪዎች መገለጥ እውነት እንደሆነው፣ የመገለጡ ዋጋ በማረጋገጫ መገለጥ በሚመሩት ላይ የተወሰነ ነው።

ያንን የመገለጥ ተአምር በአይደሆ 1976 የቴተን ግድብ ሲሰበር በነበረው ውጤት አይቻለሁ። ብዙዎቻችሁ የተከሰተውን ታሪክ ታውቃላችሁ። ነገር ግን በካስማ ፕሬዘዳንት የተላለፈው የመገለጥ ቀጣይነት ትምህርት በሚቀጥሉት ጊዜያት ሁላችንንም ይባርካል።

ቤታቸው መውደሙን ተከትሎ ሺዎች ተፈናቅለው ነበር። የአከባቢው ካስማ ፕሬዘዳንት የእርዳታ ጥረት አለመሳካቱን ጠቆመ። ከጥፋቱ ጥቂት ቀናት በኋላ እኔ በሪክስ ኮሌጅ ክፍል ውስጥ ነበርኩ። ከፌደራል የአደጋ ተቋም አንድ መሪ ደረሰ። የካስማ ፕሬዘዳንቱ ኤጲስ ቆጶሶችን እ ሚኒስተሮችን በሰበሰበበት ትልቅ ክፍል ውስጥ እርሱ እና ዋና አጋዦቹ መጡ። እኔ እዚያ ነበርኩት ብዙ የተረፉ ሰዎች እዚያ እንክብካቤ እያገኙ ስለበረ እና እኔ ፕሬዘዳንት በነበርኩበት የኮሌጁ ካምፓስ ውስጥ መጠለያ ስለተደረገላቸው ነበር።

ስብሰባው ሲጀምር፣ ከፌደራል የአደጋ ተቋም የመጣው ተወካይ ቆመ እና ምን መደረግ እንዳለበት በባለስልጣን ድምጽ ተናገረ። ወሳኝ ናቸው ካለው አምስ ወይም ስድስት ድርጊቶች ዝርዝር በኋላ፣ የካስማ ፕሬዘዳንቱ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “ያንን አድርገናል።”

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ የፌደራል አደጋ ተቋሙ ሰውዬ እንዲህ አለ፣ “ለጊዜው ልቀመጥ እና ልመልከት።” ከዛም ኤጲስ ቆጶሶች እና የክህነት ጉባኤ ፕሬዘዳንቶች ያደረጉትን ሲገልጹ እርሱ እና አጋዦቹ አደመጡ። ከመሪያቸው ያገኙትን እና የተከተሉትን ምሬት ገለጹ። ቤተሰቦችን እና የቤታቸውን ቅሬቶች ሲያገኙ ምን ለማድረግ እንደተነሳሱም ተናገሩ። እረፍዶ ነበር። ስለ ህዝቡ ፍቅር እንጂ የበለጠ ስሜት ለማሳየት በጣም ደክሟቸው ነበር።

የካስማው ፕሬዘዳንት የመጨረሻ ጥቂት ምሬቶችን ለኤጲስ ቆጶሶች ሰጡ፣ እና ለማሳወቂያ ስብሰባ ለቀጣዩ ጠዋት ሰአት አሳወቀ።

በቀጣዩ ጠዋት የፌደራል ቡድን መሪ የማሳወቂያ እና የስራ ስብሰባ ከመጀመሩ 20 ደቂቃ በፊት ቀድሞ ደረሰ ለካስማ ፕሬዘዳንቱ በዝግታ እንዲህ ሲል ሰማሁ፣ “ፕሬዘዳንት፣ እኔ እና የቡድኔ አባላት ምን እንድናደርግ ትፈልጋለህ?”

ያ ሰው ያየውን እኔም በመላው አለም ጭንቀት እና ፈተና ውስጥ አይቼዋለሁ። ፕሬዘዳንት ፓከር ትክክል ነበሩ። የመገለጥ መቀጠል የሚመጣው የካስማ ፕሬዘዳንቶችን ከራሳቸው ጥበብ እና አቅም በላይ ከፍ እንዲሉለማድረግ ነው። እና፣ ከዛም በላይ፣ ትእዛዛቱ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር እንደሚመጡ የማረጋገጫ ምስክር ጌታ ፕሬዘዳንቱ ለሚመራቸው ይሰጣል።

ህይወቴን አብዛኛው ክፍል የተነሳሱ መሪዎችን እንድከተል በመጠራት ተባርኬያለሁ። በጣም ወጣት ሳለሁ፣ የክህነት ጉባኤ ፕሬዘዳንት አማካሪ እንድሆን ተጠርቼ ነበር። በተራዬም ለሁለት የአውራጃ ፕሬዘዳንቶች አማካሪ፣ ለቤትርስቲያኑ አጠቃላይ ኤጲስ ቆጶስ፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባል፣ እና ለሁለት የቤተክርስቲያን ፕሪዘዳንቶች አማካሪ ሆኜአለዉ። ለእነርሱ እና ለተከታዮቹ የተሰጡትን በረከቶች ለማየት ተባርኬያለሁ።

ያ ሁላችንም የምንጓጓለት የግል መገለጥ፣ በቀላሉ አይመጣም፣ ስለተጠየቀም በቀላሉ አይመጣም። ጌታ ይህን ደረጃ የሰጠው ከእግዚአብሔር ምስክር ለመቀበል አቅም እንዲሆን ነው። ይሄ ሁላችንም ማድረግ እንዳለብን የግል መገለጥ ለሚሻ ሁሉ መሪ ነው።

“ሆዳችሁ በሌሎች ሰዎች ዙሪያ በልግስና የተሞላ ይሁን፣ እና በእምነት አንድ ላይ ላሉ፣ እና ቅድስና አስተሳሰባችሁን ያለማቋረጥ ያንጽ፤ ከዛም በራስ መተማመናችሁ በእግዚአብሔር እይታ ላይ የጠነከረ ይሁን፤ እና የክህነት ትምህርት ከሰማይ እንደሚወርድ ነብሳቹ ላይ ይፍሰስ።

“መንፈስ ቅዱስ ቋሚ ጓደኛችሁ ይሆናል።”4

ከዚያ ለሁላችንም ምክርን ሳልኩ። ከእግዚአብሔር ነብይ ፍቅር የምታገኙትን ስሜት በቀላሉ አትዩት። በቤተክርስቲያን የትም ብሄድ፣ በወቅቱ ማንም ይሁን ነብዩ፣ አባላት እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፣ “ወደ ቤተክርስቲያኑ ዋና ማእከል ስትመለስ፣ እባክህ ለነብዩ ምን ያህል እንደምንወደው ትነግርልናለህ?”

ያ ጀግና ከማክበር ወይም ለጀግና አይነቶች አንዳንዴ ካለን ስሜት የበለጠ ነው። ከእግዚአብሔር የሚመጣ ስጦታ ነው። እንደ ጌታ ነብይነቱ በቢሮው ሲናገር የማረጋገጫ የመገለጥ ስጦታን በቀላሉ እንድታገኙ ያደርጋችኋል። የሚሰማችሁ ፍቅር ጌታ ለሚናገሩለት ሁሉ እንዳለው ፍቅር ነው።

ጌታ በብዛት ህዝቡ ለመቀበል የሚያስቸግሩ ምክሮችን እንዲሰጡ ነብያቱን ስለሚጠይቅ ያንን ስሜት በቀጣይነት ማግኘት ቀላል አይደለም። የነብሳችን ጠላቶች ወደ ንዴት መመራትን እንድንወስድ እና የነብያትን ከእግዚአብሔር መጠራት እንድንጠራጠር ለማድረግ ይጥራሉ።

በማረጋገጫ መገለጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ትሁት ደቀመዝሙር ለመጠበቅ መንፈስ ቅዱስ እንዴት የሳሳ ልብን መንካት እንደሚችል አይቻለሁ።

በትንሽ ከተማ ውስጥ ላለ ሰው የመታተምን ቅዱስ ሀይል እንዳበረክት በነብዩ ተልኬ ነበር። ለቀዳሚው ሐዋርያ ለጴጥሮስ ጌታ የሰጠው ቅዱስ ሀይል ለማን እንደሚሰጥ የመወሰን ቁልፍ የእግዚአብሔር ነብይ ብቻ ነው ያለው። ያንን ተመሳሳይ የማተም ሀይል እኔ ተቀብዬ ነበር፣ ነገር ግን በቤተክርስቲያን ፕሬዘዳንት ምሬት ብቻ ነው ወደ ሌላ መስጠት የምችለው።

ስለዚህ፣ ከሶልት ሌክ ራቅ ባለ የቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ፣ በነብዩ የማተም ሀይልን እንዲቀበል የተመረጠው ሰው እራስ ላይ እጄን ጫንኩ። እጆቹ እብቃቅቶ ለኖር የህይወት ጊዜ የአፈር ቁፋሮ ምልክትን ያሳዩ ነበር። ቀጭኗ ሚስቱ ከእሱ በቅርብ ተቀመጠች።

በነብይ የተሰጡኝን ቃላት ተናገርኩ። “በዚህ ጊዜ ሁሉንም የክህነት ቁልፎች በያዘው”፣ ከዛ የነብዩ ስም አለ፣ “ስልጣን እና ሀላፊነት ውክልና ስር”፣ እና ስሙን እና እንደ አታሚ የሚያገለግልበትን ቤተመቅደስ ስም ሰጠሁ።

እንባ ወደ ጉንጮቹ መጡ። ሚስቱ እያነባች መሆኑንም አየሁ። እነርሱ እንዲገናኙ ትንሽ ጠበኳቻ። ቆመች እና ወደ እኔ ተራመደች። ወደ ላይ ተመለከተች እና ደስ እንዳላት እናም ግን እንዳዘነች በዝግታ ተናገረች። ወደ ቤተመቅደስ ከባሏ ጋር አብራ መሄድ በጣም እንደምትወድ ተናገረች፣ ግን አሁን እግዚአብሔር እርሱን በጣም ለከበረ እና ቅዱስ መታመን ስለጠራው አብራው መሄድ እነደማትችል እንደሚሰማት ተናገረች። ከዛም ከእረሱ ጋር ቤተመቅደስ ለመሄድ ብቁ እንዳልሆነች የተሰማት ምክንያት ማንበብ እና መጻፍ አለመቻሏ መሆኑን ተናገረች።

ታላቅ መንፈሳዊ ሀይል ስላላት ከእርሱ ጋር ወደ ቤተመቅደስ በመሄዷ ባለቤቷ ቅብር እንደሚሰማው ማረጋገጫ ሰጠኋት። በምችለው ያህል በቋንቋዋ ከምድር ትምህርት በላይ የሆኑ ነገሮች እግዚአብሔር እንደገለጸላት ነገርኳት።

ለምትወደው ባሏ እግዚአብሔር ታላቅ መታመንን እንደሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ አወቀች። የማተም ሀይል የመስጠት ቁልፍ አይታው ከማጣውቀው እና እራሷ በህይወት እንደ ሚኖር በምታውቀው ነብይ መያዙን በራሷ አውቃ ነበር። ከነዋሪ ምስክር ሳይነገራት፣ በባሏ ስም ላይ ነብይ መጸለዩን አውቃ ነበር። እግዚአብሔር እንደመለሰ ለራሷ አውቃ ነበር።

ባሏ የሚፈጽመው ስርአት ሰዎችን ለዘለአለም በመጀመሪያው መንግስተ ሰማይ እንደሚያስር ታውቅ ነበር። ጌታ ለጴጥሮስ የገባው ቃል አሁንም በቤተክርስቲያን መቀጠሉን በአእምሮዋ እና በልቧ አረጋግጣለች፤ “በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል።” 5 ከእግዚአብሔር በመገለጥ፣ ለራሷ አውቃ ነበር።

ወደ ጅማሬ ነጥባችን እንመለስ። “ነብዩ ለቤተክርስቲያኑ” ፕሬዘዳንት ለካስማው፣ ለሚስኦኑ፣ ወይም ጉባኤው፤ ኤጲስ ቆጶሱ ለአጥቢያው፣ አባት ለቤተሰቡ፤ ግለሰብ ለእራሱ በመቀበል፣ መገለጥ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቀጥሏል።”6

ያ እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። የሰማይ አባት ጸሎታችሁን ይሰማል፣ ይወዳችኋል፣ እና ስማችሁን ያውቃል። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ እና የእኛ አዳኝ መረዳት ከሚቻለው በላይ ይወዳችኋል።

እግዚአብሔር፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ በልጆቹ ላይ መገለጥን ያፈሳል። ዛሬ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ለሆነው፣ በምድር ላለው ነብዩ ይናገራል። በምድር ያለውን የክህነት ቁልፎች እንደሚይዝ እና እንደሚለማመድ እመሰክራለሁ።

በዚህ ጉባኤ እግዚአብሔር እንዲናገሩ የጠራቸውን ቃላት ስትሰሙ፣ በታተመ ቤተሰብ ለዘለአለም ከእርሱ ጋር ለመኖር ወደ ቤት ጉዞ መንገዳችሁን እንድታገኙ የሚያስፈልጋችሁን የማረጋገጫ መገለጥ እንድታገኙ እጸልያለሁ። በቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶ ስም፣ አሜን።