2010–2019 (እ.አ.አ)
“ጌታ፣ እኔ እሆንን?”
ኦክተውበር 2014


“ጌታ፣ እኔ እሆንን?”

ኩራትን ወደ ጎን መተው፣ ከራስ ወዳድነታችን በላይ መመልከት፣ እና በትህትና “ጌታ፣ እኔ እሆንን?” ብለን መጠየቅ አለብን።

የተወዳጁ አዳኛችን በሟችነት የመጨረሻው ሌሊት ነበር፣እራሱን በክፍያ ለሰው ዘር በሙሉ ከመስጠቱ በፊት ያለ አመሻሽ። ከደቀመዛሙርቱ ጋር ዳቦውን ሲቆርስ፣ የእነርሱን ልብ በላታቅ ንቃት እና ጥልቅ ሀዘን የሞላ ነገር ተናገረ። “ከእናንተ አንዱ ይከዳኛል፣” አላቸው።

የተናገርውን እውነታ ደቀመዛሙርቱ አልተጠራጠሩም። ወደዙርያውም በመመልከት፣ ወደ አንድ ሌላ ሰው በመጠቆም፣ “እሱ ነው?” አላሉም።

ይልቁንም፣ እነርሱ “በጣም በማዘን፣ እና እያንዳንዳቸው ጌታ ፣ እኔ እሆንን?1 ብለው አሉት።

ያንን ጥያቄ በአደኝ ብንጠየቅ እያንዳንዳችን ምን እንደምናደርግ ያሳስበኛል። በዙርያችን ያሉትን ተመልክተን እና፣ “ምናልባትም ስለ ወንድም ጆንሰን ነው የሚያወራው። እኔ ስለ እሱ ሁሌ እገረማለሁ።” ወይም “ወንድም ብራውን እዚህ በመኖሩ ደስተኛ ነኝ። እሱ ይህንን በጣም መስማት አለበት።”እንል ይሆን። ወይም፣ እንደ ድሮዎቹ ደቀመዛሙርት፣ ወደ ውስጣችን ተመልክተን እና “እኔእሆንን?” በማለት ያንን ጥልቅ ጥያቄ እንጠይቅ ይሆን?

“ጌታ፣ እኔ እሆንን?” በሚሉት ቀላል ጥያቄዎች ውስጥ የጥበብ መጀመሪያ ይገኛል እና የግል መቀየር እና የማያልቅ ለውጥ ይገኛል።

የዳንዴሊየን አረም ምሳሌ

በአንድ ወቅት በአጎራባቹ አከባቢ የእግር ጉዞ ማድረግ የሚወድ አንድ ሰው ነበር። በተለይም የጎረቤቱን ቤት አልፎ ለመጓዝ ይጓጓ ነበር። ይህ ጎረቤት የግቢውን ሳር በትክክል የተቆረጠ፣ አበቦቹ ሁሌም ያበቡ፣ ዛፎቹ ጤናማ እና ጥላ የሚሰጡ አድርጎ ይጠብቅ ነበር። ያ ጎረቤት ግቢውን ለማሳመር የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ እርግጥ ነው።

ነገር ግን አንድ ቀን ሰውየው የጎረቤቱን ቤት እያለፈ ሲጓዝ፣ በዚያበሚያምር ግቢ መሀል ላይ አንድ፣ ትልቅ፣ ቢጫ የዳነዴሊየን አረም መኖሩን አስተዋለ።

ከቦታ በጣም ወጣ ብሎ ስለሚታይ ተገረመ። ለምንድን ነበር ጎረቤቱ ያልነቀለው? ሊታየው አልቻለም? አረሙ ለተጨማሪ አረሞች ስር የሚሰጡ ዘሮችን ሊበትን እንደሚችል አላወቀም?

ይሄ ወጣ ያለ አረም ከሚባለው በላይ አስገረመው፣ እና በሱአንድ ነገር ማድረግ ፈለገ። ነቅሎ ያውጣው? ወይም በአረም ማጥፊያ ይርጨው? በእርግጥ በምሽት ተገን ቢሄድ በሚስጥር ማስወገድ ይችላል።

ወደ ቤቱ እየተጓዘ ይሄ ሀሳብ አይምሮውን ሞልቶት ነበር። በራሱ የፊት ግቢ የሞላውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ቢጫ የዳንዴሊየን አረሞችን ቀናም ብሎ ሳያይ ወደ ቤቱ ገባ።

ጉድፍ እና ምሰሶ

ይሄ ታሪክ የአዳኝን ቃላትን ያስታውሰናል?

“በወንድምህ አይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፣ በአይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለምን አትመለከትም?”...

“… አስቀድመህ ከአይንህ ምሰሶውን አውጣ፣ ከዚያ በኋላ ከወንድምህ አይን ጉዱፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”2

ይሄ የጉድፍ እና ምሰሶ ጉዳይ እኛ እራሳችንን አጥርተን ማየት ካለማየት ጋር በጣም ይቀራረባል። እኛ የራሳችንን ማየት እያስቸገረን፣ የሌሎች ሰዎችን ችግር በተሻለ መመርመር እና መፍትሄ መጠቆም ለምን እንደምንችል እርግጠኛ አይደለሁም።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ በፊቱ ላይ የሎሚ ጭማቂ ካሸ ከካሜራ እይታ ውጪ እሆናለሁ ብሎ ስላመነ ሰው የዜና ታሪክ ነበር። ስለዚህ የሎሚ ጭማቂ ፊቱ ላይ በሙሉ በማድረግ፣ ወጣ፣ እና ሁለት ባንኮችን ዘረፈ። ብዙም ሳይቆይ ነበር ምስሉ በአመሻሽ ዜና ላይ ተለቆ የታሰረው። የራሱን ምስል ከጥበቃ ካሜራ ላይ ፖሊስ ለሰውየው ሲያሳየው፣ አይኑን አላመነም። “ግን የሎሚ ጭማቂ ፊቴ ላይ ነበረ!” በማለት ተቃወመ።3

በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ሳይንቲስት ይሄን ታሪክ ሲሰማ፣ ሰውየው ከሚገባው በላይ የራሱን መሀይምነት አለማወቁ አስደነቀው። ይሄ አጠቃላይ ችግር መሆኑንን ለማጣራት፣ ሁለት አጥኚዎች በተለያየ የህይወት ሙያ ላይ በሚደረግ ተከታታይ ሙከራ እንዲሳተፉ የኮሌጅ ተማሪዎችን ጋበዙ። በአናሳ የፈጸሙት ተማሪዎች የራሳቸውን ስራ በመገምገም ትክክል ከመሆን የራቁ ነበሩ---አንዳንዶቹ በትክክል ከሆኑት አምስት እጥፍ የበለጠ ለራሳቸው ውጤት ግምት ሰጡ።4

ይሄ ጥናት በተለያየ መልኩ ተመስሏል፣ በተደጋጋሚ አንድ አይነት ማጠቃለያን በማረጋገጥ፤ አብዛኞቻችን እራሳችንን በትክክል እንደሆንነው ማየት እንቸገራለን፣ እና ስኬታማ ሰዎችም እንኳን የራሳቸውን አስተዋጽኦ በበለጠ የተረጉማሉ እና ሌሎች የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ያጣጥላሉ።5

በምን ያህል መልኩ መኪና እንደምንነዳ ወይም የጎልፍ ኳስ እንደምንነዳ አግኖ ማየት ጠቃሚ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን በቤት፣ በስራ፣ እና ቤተክርስቲያን ያለን አስተዋጽኦ ከሆነው በላይ መሆኑን ማመን ስንጀምር፣ ከበረከቶች እና በአስፈላጊ እና ተገቢ መልኩ ለመሻሻል ያለውን የራሳችንን እድል እናጨልማለን።

የመንፈሳዊ ስውር ቦታዎች

በአንድ ቅርንጫፍ ውስጥ የእኔ ወዳጅ በቤተክርስቲያን ውስጥ በታላቅ ብዛት ይኖሩ ነበር--ተሳትፎ ብዙ ነበር፣ የቤት ለቤት ትምህርት ቁጥር ብዙ ነበር፣ የፕራይመሪ ህጻናት ሁሌም ጥሩ ጸባይ ነበራቸው፣ የቅርንጫፍ እራት አባላት በመሰብሰቢያ ቤቱ ወለል ላይ የማያንጠባጥቡት ምርጥ ምግቦችን ያጠቃልላል፣ እና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ምንም ክርክር አልነበረም ብዬ አስባለሁ።

ጓደኛዬ እና የእሱ ሚስት ቀጥሎ ወደ ሚስኦን ተጠሩ። ከሶስት አመት በኋላ ሲመለሱ፣ እነርሱ በሚስኦን ላይ ሳሉ፣ ትዳሮች በፍቺ መጠናቀቃቸውን ሲያውቁ ተገረሙ።

ቅርንጫፉ የእምነት እና ጥንቃሬ ውጫዊ ምልከታ ቢኖረውም፣ ጠሩ ያለሆነ ነገር በአባላት ልብ እና ህይወት ውስጥ እየተከሰተ ነበር። እና የሚረብሸው ነገር ይሄ ሁኔታ የተለየ አይደለም። እነዚህ ክፉ እና አላስፈላጊ ነገሮች የቤተክርስቲያን አባላት ከወንጌል መርሆዎች ውጪ ሲሆኑ የሚከሰት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለመሆን በስተጀርባ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ከልባቸው ውስጥ ከአዳኛቸው እና ከትምህርቱ የነጠለ ነበር። ከመንፈስ ቅዱስ ነገሮች ውጪ ቀስ በቀስ ዞረው እና ወደ አለም ነገሮች የተጠጉ ናቸው።

በአንድ ወቅት ብቁ የክህነት ተሸካሚዎች ለእነርሱ ሳይሆን ቤተክርስቲያኗ ለሴቶች እና ህጻናት ጥሩ ነች በማለት ለራሳቸው መንገር ጀመሩ። ወይም አንዳንዶቹ የተወጣጠረው ጊዜያቸው የተለየ ሁኔታዎቻቸው ከመንፈስ ቅዱስ ቅርብ የሚያደርጋቸውን የየቀን መሰጠት እና አገልግሎት ከመስጠት እንደተወገዱ እራሳቸውን አሳምነዋል። በዚህ እራስን ነጻ የማድረግ እና የመኩራት ጊዜ፣ በቋሚ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር አለመቅረብ፣ የቅዱስ መጽሀፍት ጥናት ጊዜን ማስተላለፍ፣ የቤተክርስቲያን ስብሰባን እና የቤተሰብ ምሽት አለማድረግ፣ ወይም ታማኝ አስራት እና በኩራት ላለማድረግ ምክንያት ለመፍጠር ቀላል ነው።

ወንድሞች፣ እባካችሁ ወደ እራሳችሁ ውስጥ በመመልከት፤ “ጌታ፣ እኔ እሆንን” የሚለውን ቀላል ጥያቄ ትጠይቃላችሁ?

በጥቂቱም እንኳን ቢሆን---“ከተባረከው የእግዚአብሔር ወንጌል፣ ለእናንተ እምነት ከተሰጠው” ተነጥላችኋል?6 “የዚህ አለም አማልክት” አይምሮአችሁን “ከክርስቶስ ክቡር የወንጌል ብርሀን” እንዲያጨልም ፈቅዳችኋል?7

የተወደዳችሁ ጓደኞቼ፣ ውድ ወንድሞቼ፣ “ሀብቴ ወዴት ነው?”፣ ብላችሁእራሳችሁንጠይቁ።

ልባችሁ በዚህ አለም አመቺ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፣ ወይስ በትጉሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረ ነው? “ሀብታችሁ ባለበት፣ ልባችሁም ይገኛል።”8

የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ይገኛል? በእግዚአብሔር እና ባለንጀራዎቻችሁ ፍቅር “ጠልቃችኋል እና ተሰጥታችኋል?” ለትዳራችሁ እና ቤተሰባችሁ ደስታ ለማምጣት በቂ ጊዜ ትሰጣላችሁ? ለሚያምር የመረዳት እና መልሶ ለተቋቋመው የኢየሲስ ክርስቶስ የወንጌል “ስፋት፣ እርቀት፣ ጥልቀት እና ቁመት” የመኖር አላማ ሀይላችሁን ሰጥታችኋል?9

ወንድሞች፣ የ“እምነት፣ ቅድስና፣ እውቀት፣ እርጋታ፣ ትግስት፣ ወንድማዊ ደግነት፣ መለኮታዊነት፣ ልግስና፣ ትህትና፣ እና አገልግሎት፣”10 በሆኑት የክርስቶስ ባይሪያት ለማደግ ታላቅ ፍላጎታችሁ ከሆነ፣ ለብዙ ነብሳት መዳን የሰማይ አባት በእጁ መሳሪያ ያደርጋችኋል።11

የተፈተሸ ህይወት

ወንድሞች፣ ከትክክለኛው መንገድ መውጣታችንን ማንኛችንም መቀበል አንፈልግም። በብዘት በጥልቅ ወደ ነብሳችን መመልከት እና ድክመታችንን፣ ገደባችንን እና ፍራቻችንን መጋፈጥን ለማስወገድ እንሞክራለን። በውጤቱም፣ ህይወታችንን ስንፈትሽ፣ በማጋነን፣ ምክንያት ድርደራ፣ እና ብቁ ያልሆኑ አስተሳሰብ እና ድርጊቶችን ለማመካኘት በምንናገራቸው ታሪኮች ማጣሪያ ውስጥ እንመለከታለን።

ነገር ግን እራሳችንን አጥርቶ ማየት መቻል ለመንፈሳዊ እድገታችን እና ደህንነት ወሳኝ ነው። ድክመታችን እና ስህተቶቻችን በጥላ ውስጥ ተደብቀው ከቆዩ፣ የአዳኝ ቤዛ ሀይል ሊያድናቸው እና ጥንካሬዎች ሊያደርጋቸው አይችልም።12 በተቃራኒው፣ ሰው በመሆናችን ላለን ድክመት መታወር በእያንዳንዳችን ውስጥ የሰማይ አባት ሊያሳድግ የሚፈልገውን መለኮታዊ አቅም እንዲታወር ያደርጋል።

ስለዚህ የእግዚአብሔርን እውነት ንጹህ ብርሀን በነብሳችን ውስጥ እንዲበራ እና እርሱ እንደሚመለከትን እኛ እራሳችንን ማየት የምንችለው እንዴት ነው?

ቅዱስ መጽሀፍት እና በአጠቃላይ ጉባኤ የሚሰጡ ንግግሮች እራሳችንን ለመፈተሽ መያዝ የምንችላቸው ተገቢ መስታውት እንደሆኑ እጠቁማለሁ።

የጥንት እና የአሁን ነብያትን ቃላት ስትሰሙ ወይም ስታደምጡ፣ እንዴት ቃላቶቹ ስለ ሌላ ሰው መሆናቸውን ከማሰብ ተቆጠቡ እና “ጌታ፣ እኔ ነኝ?” የሚለውን ቀላል ጥያቄ ጠይቁ።

የዘለአለማዊ አባታችን በተሰበረ ልብ እና ሊማር በሚችል አእምሮ መቅረብ አለብን። ለመማር እና ለመለወጥ ፍቃደኛ መሆን አለብል። እናም፣ የሰማይ አባታችን ለእኛ እንዳቀደው ህይወትን ለመኖር በመሰጠት የምናገኘው እጅግ ብዙ ነው።

ለመማር እና ለመለወጥ የማይሹ ምናልባትም አይለወጡም እና በአብዘኛውም ቤተክርስቲያን የምታደርግላቸው ነገር ስለመኖሩ መወዛገብ ይጀምራሉ።

ማሻሻል እና ማደግ የሚፈልጉ ግን፣ ስለ አዳኝ የሚማሩ እና እንደ እርሱ መሆን የሚፈልጉ፣ እራሳቸውን እንደ ህጻን ትሁት የሚያደርጉ እና ከሰማይ አባት ጋር ሀሳባቸውን እና ድርጊቶቻቸውን ማዛመድ የሚፈልጉ--- የአዳኝን የሀጢያት ክፍያ ተአምራት ይለማመዳሉ። በእርግጥም የእግዚአብሔር ድንቅ መንፈስ ይሰማቸዋል። የየዋህ እና ትሁት ልብ ፍሬ የሆነውን ማብራራት የማይቻል ደስታ ቀምሳሉ። እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት በመሆን ፍላጎት እናስረአት ይባረካሉ።

የመለካም ሀይል

በህይወት ቆይታዬ ላይ፣ ይህች ጥቂት አለም ካፈራቻቸው ብቁ እና አዋቂ ሰዎች ትከሻ የመዳበስ እድል አጋጥሞኛል። ወጣት ሳለሁ፣ በተማሩት፣ በተሳካላቸው እና በአለም እውቅና ባገኙ ሰዎች እደነቅ ነበር። ከአመታት በኋላ ግን፣ ድንቅ እና የተባረከ ነብሳት ባላቸው እውነተኛ መልካም እና ያለ ክፋት በሆኑት በጣም በበለጠ መደነቄን ለማስተዋል በቃሁ።

ወንጌል ስለእዚህ ብቻም አይደል እና የሚያደርግልንስ ይህንኑ አይደለም? መልካም ዜና ነው እና መልካም ወደመሆን እንድንመጣ ይረዳናል።

የሐዋርያው ያዕቆብ ቃላት ዛሬ ለኛ ይሆናል፤

“እግዚአብሔር ኩራተኛን ይገታል፣ ነገር ግን ለትሁት ጸጋን ይሰጣል።

“በጌታ እይታ እራሳችሁን ትሁት አድርጉ፣ እና እርሱ ከፍ ያደርጋችኋል።”13

ወንድሞች፣ ኩራታችንን ወደ ጎን መተው፣ ከእራስ ወዳድነታችን ባሻገር መመልከት፣ እና በትህትና፣ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ነኝ?” ብለን እንጠይቅ።

ምላሹ “አዎ፣ ልጄ፣ ማሻሻል ያሉብህ ነገሮች አሉ፣ እንድታሸንፋቸው የምረዳህ ነገሮች አሉ” ከሆነ፣ ሀጢያቶቻችንን እና መሳሳታችንን እና መንገዳችንን እንድንቀይር በትህትና ይህንን መልስ መቀበል እንድንችል እጸልያለሁ። ከዚህ ጊዜ በኋላ በአዳኝ የተባረከ መንገድ በሙሉ ሀሳባችን እንጓዝ---እራሳችንን አጥርቶ መመልከት የጥበብ መጀመሪያ ነው።

እንዲህ ስናደር፣ ለጋሱ እግዚአብሔር እጃችንን ይዞ ይመራናል። “ጠንካራ እና ከላይ የተባረከን” እንደረጋለን።14

ተወዳጅ ጓደኞቼ፣ በአስገራሚው እና አመርቂው የደቀመዛሙርትነት መንገድ ላይ የመጀመሪያው ደረጃ ይህን ቀላል ጥያቄ መጠየቅ ነው፤

“ጌታ ሆይ፣ እኔ ነኝ?”

ስለዚህ የመሰከርኩት እና በረከቴን የምተውላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።