2010–2019 (እ.አ.አ)
በነብት ቃላት መሰረት ኑሩ
ኦክተውበር 2014


በነብት ቃላት መሰረት ኑሩ

ከሰማይ መለኮታዊ አላማዎች ጋር ለመስማማት ነብዩን እንደግፋለን እናም እንደ ቃሎቹ ለመኖር እንመርጣለን፡፡

የሰማይ አባታችን ሁሉንም ልጆቹን ይወዳል እና የእርሱን የደስታ እቅድ እንዲማሩ እና እንዲረዱይመኛል። ስለሆነም፣ በኃይል እና በስልጣን ለልጆቹ ደህንነት ሲል በእግዚአብሔር ስም ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነቢያትን ይጠራል። የፅድቅ መልዕክተኞች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ እና የሀጢያት ክፍያው ዘላለማዊ ኃይል ምስክሮች ናቸው።በመሬት ላይ የእግዚአብሔርን መንግስ ቁልፍ ይዘዋል እናም የመዳን ስነ-ስርዓቶችን ክንውን ፍቃድ ይሰጣሉ።

በጌታ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ “እነዚህ የክህነት ኃይሎች እና ቁልፎች የሚሾሙበት በምድር ላይ በአንድ ሰአት ከአንድ በላይ የለም።”1 ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰንን እንደ ነብያችን፣ ባለራዕይ እና ገላጫችን እንደግፋቸዋለን። መላ ቤተክርስቲያናችንን ለመምራት እና አቅጣጫ ለማስያዝ የጌታ ቃልን ይገልፃል። ፕሬዘደንት ጄ. ሩበን ክላርክ እንዳብራራው፣ “ለቤተክርስቲያኗ እርሱ ብቻ ነው ራዕይ የመቀበል መብት ያለው።… ወይም በምንም አይነት መልኩ የቤተክርስቲያኗን ትምህርት መቀየር የሚችለው።”2

በሕይወት ያለውን ነቢይ በተመለከተ፣ ጌታ የቤተክርስቲያኑን ህዝቦች ያዛል፥

“በሙሉ ቅድስና ከፊቴ እየተራመደ በሚቀበላቸው ሰአት የሚሰጣችሁን መላ ቃሎቹን እና ትዕዛዞቹን መስማት አለባችሁ፤

“ከእኔ አንደበት እንደተቀበላችሁ ያክል በሙሉ ትዕግስት እና እምነት ቃሎቹን ተቀበሉ።

“እነዚህን ነገሮች በማድረጋችሁ የሲኦል ደጃፍ አይከፈትባችሁም።”3

ከሰማይ መለኮተዊ አላማ ጋር በመስማማት፣ ነብዩን እንደግፈዋለን እንዲሁም በቃሎቹ መሰረት ለመኖር እንመርጣለን።

የፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንን አማካሪዎች እንዲሁም የአስራሁለት ሐዋርያት ምልአተ ጉባኤዎችንም እንደ ነብዮች፣ ባለራዕይ እና ገላጮች እንደግፋለን። ለቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት ተጠሪ በመሆን የጌታን አእምሮ እና ፍቃድ ለማወጅ መብቱ፣ ኃይሉ እና ስልጣኑ አላቸው።4 በክርስቶስ ስም ይናገራሉ። በክርስቶስ ስም ይተነብያሉ። ሁሉንም ነገሮች በክርስቶስ ስም ያደርጋሉ። በቃላቸው ውስጥ የጌታ ፍቅር ይሰማናል።“በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገፍተው የሚናገሩት ነገር በሙሉ ቅዱስ መጽሐፍ ይሁናል፣ እናም ለደህንነት የእግዚአብሔር ኃይል ይሆናል።”5 ጌታ እራሱ እንዲህ ብሎ ተናግሯል፥ “በራሴ ድምፅም ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ፣ አንድ ነው ።”6

“በሐዋርያት እና ነብያት መሰረት ላይ ታንፃችኋል፣ የማዕዘኑም ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” 7 እንደዚህ ለሆነው ቤተክርስቲያን እጅግ አመስጋኝ ነን። ጌታ ቤት የስነ-ስርዓት ቤት ነው እናም ለጥያቄዎቻችን ወይም የትኛውን ድምፅ መከተል ስላለብን መልስ ለመፈለግ መሸወድ የለብንም።“በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም መንሳፈፍ” 8 የለብንም።“ሁላችን የአግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፣ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመስራት እና ለክርስቶስ አካል ሕንፃ ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ” 9 እግዚአብሔር ቃሎቹን በተሾሙት አገልጋዮቹ አማካኝነት ይገልፃል። ልክ እን ነብያት ቃሎች ለመኖር ስንመርጥ፣ ወደ ዘላለማዊ ፍፁምነት ወደሚያመራው የቃል-ኪዳኑ መንገድ ላይ ነን።

ከአንድ የድርቅ ወቅትን ለመቋቋም እየተቸገረች ካለች እናት፣ ነቢይን መደገፍ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንማራለን። ጌታ ነብዩ ኤሊያስን ባሏ የሞተባትን ሴት እግዚአብሔር እንድትደግፈው ያዘዛትንወደሚያገኝበት ወደ ሰራፕታ እንዲሄድ አዘዘው። ኤሊያስ ወደ ከተማው ሲቃረብ፣ እንጨቶችን እየሰበሰበች አያት። ጠራትና “የጠጣው ጥቂት ውኃ በፅዋ ታመጪልኝ ዘንድ እለምንሻለው አላት።”10

“ውኃም ልታመጣ በሄደች ጊዜ ወደ እርስዋ ጠርቶ ቁራሽ እንጀራ በአጅሽ ይዘሽ ትመጪ ዘንድ እለምንሻለው አላት።

“እረርስዋም አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፤ እነሆም ገብቼ ለእኔ እና ለልጄ እጋግረው ዘንድ በልተነውም አንሞት ዘንድ ጥቂት እንጨት እሰበስባለው አለች።”

ኤልያስም አላት፣ “አትፍሪ ይልቅስ ሄደሽ እንዳልሽው አድርጊ፣ አስቀድመሽ ግን ከዱቄቱ ለእኔ ታናሽ እንጎቻ አድርገሽ አምጪልኝ፣ ከዚያም በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ አድርጊ።”11

የተራበችን እናት ነብዩ ምን ይጠይቃት እንደነበር ያለውን ከባድነት ለተወሰነ ጊዜ አስቡ። በእርግጥ፣ እግዚአብሔር እራሱ ለአማኝ አገልጋዩ ምገብ ማዘጋጀት ይችል ነበር። ነገር ግን በጌታ ስም እየሰራ ኤሊያስ ውዷ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ያላትን ነገር ነብዩን ለመደገፍ መሰዋት እንድታደርግ እንደታዘዘው አደረገ።

ነገር ግን ኤሊያስ ለታዛዥነት በረከት ቃል ገብቷል፥“የእስራኤል አምላክ አግዚአብሔር እነዲህ ይላልና። በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፣ ዘይቱም ከማሰሮው አይግድልም።”12 ጌታ ባሏ ለሞተባት ሴት የነብዩን ቃሎች ለማመን እና ለመታዘዝ እንድትመርጥ እድል ሰጣት።

በፅድቅ ቸነፈር እና በመንፈሳዊ ረሀብ እየተስፈራራች ባለች አለም ውስጥ፣ ነብዩን እንድንደግፍ ታዘናል። ነቢያዊ ቃልን ስንሰማ፣ ስንደግፍ እና ስናረጋግጥ፣ በትህትና ለጌታ ፍቃድ፣ ጥበብ እና ጊዜ እምነቱ እንዳለን እንመሰክራለን።

ምክንያታዊ፣ የማይመች እና ተስማሚ ባይመስልም እንኳን ነብያዊ ቃልን እንሰማለን። እንደ አለም ደንብ መሰረት ነቢይን መከተል ያልተለመደ፣ በፖለቲካዊ ስህተት የሆነ ወይም በማህበራዊ ተቀባይነት የሌለው ሌሆን ይችላል። ነገር ግን ነቢይን መከተል ሆሌም ትክክል ነው።“ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።”13 “በፍፁም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በስራህም ማስተዋል አትደገፍ።”14

ጌታ ነብያዊ አመራርን የሚሰሙትን ያከብራል እንዲሁም ይመርጣል። ለሰራፕታዋ ባል የሞተባት ሴት፣ ኤልያስን መታዘዝ ሕይወቷን እና በመጨረሻም የልጇን ሕይወት አድኖላታል። ነብዩ ቃል እንደገባው፣ “እርስዋ እና እርሱ ቤትዋም ብዙ ቀን በሉ።… በኤልያስ እጅ እንደተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል።”15

“ጌታ የሚያምኑትን ይመግባል።”16 የነብያት ቃሎች ለነፍሳችን ልክ እንደ መና ናቸው። ስንካፈላቸው፣ እንባረካለን፣ እንጠበቃለን እናም በጊዚያዊ እና በመንፈሳዊ እንጠበቃለን። ቃላቶቻቸውን ስንመገባቸው፣ ወደ ክርስቶች እንዴት ለመምጣት እና ለመኖር እንደምንችል እንማራለን።

ሽማግሌ ብሩስ አር. መካንኬ በነብያቶች አማካኝነት “ጌታ የመዳንን አውነታዎች ይገልፃል፣…በክርስቶስ ያለውን ደህንነት፤ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያመራውን መንገድ ይነድፋል። በእንዳንዱ እድሜ ጌታ ለህዝቦቹ በፈተናቸው እና በአደጋቸው ጊዜ የሚፈልጉትን ምሪት ይሰጣል። እናም በእርግጠኝነት፣ ወደፊት ባለው ቀናት የእግዚአብሔር ጥበብ እንጂ ሌላ ነገር በማይኖርበት ጊዜ ከሰማይ በመውረድ እና ከነብያዊ ከንፈሮች በመውጣት ህዝቦቹን ያድናል” ብለው ፃፉ።17

ለእኔ፣ በተከበረው አስተማሪዬ የተማርኳቸው የነብያት ቃሎች የቃል-ኪዳን ጋብቻ ግንኙነት ምን አይነት ሊመስል እንደሚችል ራዕይ ሰጥቶኛል። የነብያት ቃሎች እንድዘጋጅ እና ደስተኛ ቤት እንዳገኝ እምነት እና ተስፋ ሰጠኝ። በተደጋጋሚ የጥንት እና የዘመናዊ ነብያትን ትምህርቶች ማጥናት ኃይለኛ እና በብዛት አድካሚ አመታት በሆኑት ሰባት ልጆችን የመውለድ፣ የማስተማር እና የመመገብ ወቅት ውስጥ ደገፈኝ። በመጽሐፍ ቅዱሳት ውስጥ የወጡ እና ከዚህ መነጋገሪያ የምንማራቸው የነብያት ቃሎች ማፅናኛ፣ የፍቅር፣ የጥንካሬ እና እንደተለመደው ሁላችንንም የሚያቅፈው የመልካም ደስታ ቃሎች ናቸው።

ነብያትን ቃሎች ስንሰማ፣ ቤታችንን እና ሕይወታችንን በዘላለማዊ መሰረት ላይ፣ “የአዳኛችን አለት ላይ፣ እሱም በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ላይ እንገነባለን።… ዲያብሎስ ኃይሉን፣ ንፋሱን፣ አዎን በአውሎ ነፋስ እንደሚወረወር ዘንጉን በላከ ጊዜ፣ በረዶው እናም ሀይለኛው ውሽንፍር በሚመታችሁ ጊዜ እናንተን ወደ ስቃይና መጨረሻ ወደሌለው ባህረ ሰላጤ ጎትቶ ለመጣል ኃይል አይኖረውም።”18

ምርጫ አለን። በተሾሙት የእርሱ አግልጋዮች የተነገረውን የክርስቶስን ቃሎች ችላ ለማለት፣ ዋጋ ላለመስጠት፣ ለማዋረድ ወይም ለማወክ መምረጥ እንችላለን። ነገር ግን አዳኙ ይሄን የሚያደርጉ ሰዎች ከቃል-ኪዳ ህዝቦቹ እንደሚቆረጡ አስተማረ። 19

በፀሎት መንፈስ ሆነን ቅዱስ ነብያዊ ቃልን እምነት በሙሉ ልብ በክርስቶስ በማድረግ ስናነብ እና ስናጠና፣ መንፈስ ቅዱስ እውነታን ለአእምሮአችን እና ልባችን ይናገራል። ጆራችንን ለመስማት፣ ልባችንን ለመረዳት እና አእምሮአችንን የእግዚአብሔርነ ምስጢራት ወደ እይታችን እንዲከፈቱ ለማድረግ እንክፈታቸው። 20

የሴፍ ስሚዝ ነቢይ እንደነበር እና እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እና የእርሱን ክህነት ወደ ምድር መልሶ ለማቋቋም የጠራው ነቢይ እንደነበር እምሰክራለው። ዛሬ በፕሬዘደንት ሞንሰን እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ እየተመራን እንደሆነ እመሰክራለው። ከነብያቶች ጋር አብረን ለመቆም እና በእምነት አንድ እስከምንሆን፣ በክርስቶስ እስከምንጠራ እና በእግዚአብሔር ልጅ እውቀት እስክንሞላ ድረስ እንደ ቃሎቻቸው ለመኖር እንምረጥ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።