2023 (እ.አ.አ)
አሁን ክርስቶስ ተነስቷል
መስከረም 2023 (እ.አ.አ)


“አሁን ክርስቶስ ተነስቷል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)

አሁን ክርስቶስ ተነስቷል

ሐዋርያው​ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ያስተማረውን እወቁ።

ምስል
ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ

ከሞት የተነሳው ክርስቶስ፣ በዊልሰን ጄ. ኦንግ

አሁን ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነስቷል

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞተ፣ ተቀበረ እናም በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ።

ላንቀላፉት በኩራት

በኩራት ለሚለውን እዚህ ጋር የተጠቀሙት የግሪክ ቃል የዓመቱ የመጀመሪያ ሰብል ማለት ነው። በቅድሚያ የሚሰበሰበው ነው—ገና ከሚመጡት ከብዙዎቹ መጀመሪያው ነው።

ላንቀላፉት የሚለው ሐረግ “ለሞቱት” ማለት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ለማድረግ የመጀመሪያው ነበር፣ እና ከትንሳኤውም በኋላ፣ ሁሉም ሰዎች ይነሳሉ።

ሞት በሰው በኩል መጣ

ይህ የሚናገረው ስለ አዳም ነው። የእርሱ ውድቀት ትርጉም ወደ ዓለም የሚመጡ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ ማለት ነው። (ሙሴ 4ን ተመልከቱ።)

ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ

በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ሁሉም ሰዎች ከሞት ይነሳሉ። ይህ ማለት የኖረ ወይም የሚኖር ሁሉ ከሞት ይነሳል ማለት ነው። መንፈሳችን ከአካላችን ጋር ይገናኛል፣ እናም ሰውነታችን ፍጹም እና የማይሞት ይሆናል። (አልማ 11፥43–45 ተመልከቱ።)