ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የካቲት 5–11፦ “በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ [መሆን]።” 2 ኔፊ 1–2


የካቲት 5–11 ፦ ‘በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ [መሆን]።’ 2 ኔፊ 1–2፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 5–11 2 ኔፊ 1–2፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከኤደን የአትክልት ስፍራ ሲወጡ

አዳም እና ሔዋን፣ በዳግላስ ፍራየር

የካቲት 5–11 ፦ “በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ [መሆን]”

2 ኔፊ 1–2

ህይወታችሁ እንደሚያበቃ ብታውቁ፣ በጣም ለምትወዱት ሰዎች ምን የመጨራሻ መልዕክት ለማካፈል ትፈልጋላችሁ? ነቢዩ ሌሂ ወደ ህይወቱ መጨረሻ እየቀረበ እንደሆነ ሲሰማው፣ ለመጨረሻ ጊዜ ቤተሰቡን ሰበሰበ። የሰማይ አባት ለእሱ የገለፀለትን ለእነሱ አካፈለ። ስለ መሲሁ ምስክርነቱን ሰጠ። የሚወደውን የወንጌል እውነቶች ለሚወዳቸው ሰዎች አስተማረ። ስለ ነፃነት፣ ታዛዥነት፣ የአዳም እና ሔዋን ውድቀት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት እና ደስታ አስተማረ። ሁሉም ልጆቹ ያስተማረውን ነገር ለመኖር አልመረጡም—ማንኛችንም እነዚህን ምርጫዎች ለምንወዳቸው ሰዎች ማድረግ አንችልም። ነገር ግን “ነፃነትን እና ዛላለማዊ ህይወትን ለመምረጥ [ነፃ]” ስለ ሚያደርገን ቤዛ ማስተማር እና መመስከር እንችላለን (2 ኔፊ 2፥26–27 ይመልከቱ)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ኔፊ 1፥13–29

“[መንቃት] ከትቢያም ላይ [መነሳት]” እችላለሁ።

2 ኔፊ 1፥13–29 ውስጥ፣ የላማንን እና የልሙኤልን መንፈሳዊ ሁኔታ ለመግለጽ ሌሂ የተጠቀመውን ቃላት አስተውሉ። ከመንፈሳዊ “ጥልቅ እንቅልፍ” እንድትነቁ ምን ረዳችሁ? በህይወታችሁ ውስጥ መንፈሳዊ “ሰንሰለ[ታችሁን]” እንድትበጥሱ ምን ረዳችሁ? ስለ ሌሂ ምስክርነት በቁጥር 15 ውስጥ እና ስለ ግብዣው በቁጥር 23 ውስጥ አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሰማይ አባት ለእናንተ ምን መልዕክት አለው?

ምስሎችን ተጠቀሙ። ምስሎችን መጠቀም ተማሪዎች የወንጌል እውነቶችን እንዲገነዘቡ እና ለረጅም ጊዜ እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል። ከዚህ ዝርዝር ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ ምን ምስሎችን እንደምትጠቀሙ አስቡ። ለምሳሌ፣ የወረቀት ሰንሰለት በ2 ኔፊ 1፥13 ወይም 2 ኔፊ 2፥27 ውስጥ የሌሂን ቃላት ተማሪዎች እንዲገነዘቡ ምናልባት ሊረዳቸው ይችላል።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 2

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት “ነፃነትን እና ዛላለማዊ ህይወትን ለመምረጥ [ነፃ]” ነኝ።

የሌሂ ቤተሰብ በዚህ ሰዓት በአዲስ ምድር ውስጥ በአዲስ አማራጮች ተከበው ነበር። በዚህ አዲስ ምድር ውስጥ የሚያደረጉት ምርጫዎች ለስኬታቸው እና ለደስታቸው ጠቃሚ ይሆናል። በ2 ኔፊ 2 ውስጥ ሌሂ ልጁ ያዕቆብን ስለ ነፃ ምርጫ ወይም ምርጫዎችን ስለማድረግ ችሎታ ያስተማረው ምናልባት ለዚህ ይሆናል። ቁጥር 11–30ን ስታጠኑ ለእነዚህ ጥያቄዎች ሊሆኑ የሚችሉ መልሶችን ጻፉ።

  • ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ጎጂ በሆኑ መንገዶች ቢጠቀሙትም ነፃ ምርጫ ለሰማይ አባት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ጠላት ነፃ ምርጫችሁን ለማዳከም ወይም ለማጥፋት የሚሞክረው እንዴት ነው?

  • “ነፃነትን እና ዛላለማዊ ህይወትን ለመምረጥ” አዳኙ እንዴት ነው የሚረዳችሁ (ቁጥር 27)?

2 ኔፊ 2 ውስጥ ስለ ነፃ ምርጫ መማርያ ሌላኛው መንገድ ይሄ ነው፦ ነፃ ምርጫ እንዲኖረን እና መለኮታዊ አቅም ላይ ለመድረስ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ፈልጉ። ለምሳሌ፦

ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ቢጠፉ በነፃ ምርጫችን ላይ ምን ይፈጠራል?

ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን ለማድረግ የሚረዳ መመሪያ እያንዳንዱ ስድስት ክፍሎች “ግብዣዎችን” እና “ቃል የተገቡ በረከቶችን” ይይዛሉ። ከእነዚህ ክፍሎች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ተመልከቱ እና በህይወታችሁ ውስጥ ተስፋ የምታደርጉትን ቃል የተገባለትን በረከትን ምረጡ። ይህንን በረከት ለመቀበል ምን ግብዣን ማድረግ ይኖርባችኋል? እነዚህን ግብዣዎች በመከተል ያገኛችሁትን በረከቶች ለአንድ ሰው ለማካፈል አስቡ።

በተጨማሪም፣ “ነፃ ምርጫ እና ተጠያቂነት [Agency and Accountability]፣”የወንጌል አርዕስቶችች፣ “ይህን እወቁ፣ እያንዳንዱ ነፍስ ነፃ ነው [Know This, That Every Soul Is Free]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 240 የወንጌል ቤተ መጽሐፍት ይመልከቱ።

2 ኔፊ 2፥1–4፣ 6–25

እግዚአብሔር ፈተናዎቼን ወደ በረከት መቀየር ይችላል።

ሌሂ ወጣት ልጁ ያዕቆብ በልጅነቱ ወቅት “በመከራዎች” እና “በበለጠ ሃዘን” እንደተሰቃየ ያውቅ ነበር (2 ኔፊ 2፥1)። በ2 ኔፊ 2፥1–3፣ 6–25 ውስጥ የሌሂ ምስክርነት ለያዕቆብ አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ለእናንተ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? በተለይ ኃይለኛ ሆነው ያገኛችሁትን ቃላት እና ሃረጎች ፈልጉ። እግዚአብሔር መከራችሁን በድጋሜ የቀደሰላችሁ እንዴት ነው ? (2 ኔፊ 2፥2 ይመልከቱ።)

እንዲሁም ሮሜ 8፥28፤ ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “Infuriating Unfairness፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 41–45 ተመልከቱ።

2 ኔፊ 2፥15–29

ውድቀት እና የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ የሰማይ አባት ዕቅድ አስፈላጊ አካሎች ናቸው።

ብዙ ሰዎች ውድቀት አሳዛኝ ነገር ብቻ እንደሆነ እና ሔዋን እና አዳም ፍሬውን ለመብላት ሲመርጡ ቋሚ ስህተትን እንደሰሩ ያምናሉ። በ2 ውስጥ 2፥15–28፣ ሌሂ ስለ ውድቀት እና በክርስቶስ አማካኝነት ስለ ቤዛነት ተጨማሪ እውነትን ያስተምራል። እነዚህን ጥቅሶች ስትመረምሩ፣ በኤደን ገነት ውስጥ ስለተከሰቱት እውነቶች ዝርዝር ፃፉ። እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ፦

  • ውድቀቱ ለምንድን ነበር ያስፈለገው?

  • የውድቀቱን ውጤቶች ለማሸነፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ሚናን ተጫወተ?

  • ውድቀትን በትክክል መረዳታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስፈላጊነት የበለጠ ለመረዳት የሚረዳን እንዴት ነው?

በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “ታላቁ የደስታ እቅድ [The Great Plan of Happiness]፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 1993 (እ.አ.አ)፣ 72–75 ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትም ይመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

ልባችሁ አይታወክ [Let Not Your Heart Be Troubled]፣ በሃዋርድ ሊዮን

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ኔፊ 1፥13፣ 15፣ 23

ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ውጤቶችን እንዳሸንፍ ይረዳኛል።

  • የሌሂን የሃጢያት “ሰንሰለት[ን] [የማውለቅ]” ግብዣ ልጆቻችሁ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ምናልባት በወረቀት ሰንሰለትን ለመስራት በጋራ መስራት ትችላላችሁ። በወረቀቶቹ ላይ ልጆቻችሁ ሰይጣን እንድናደርግ የሚፈትነንን ነገሮች ለመፃፍ ሊረዱ ይችላሉ። ከዚያም በጥቅሶቹ ውስጥ ያሉትን ሃረጎች በመተወን ማለትም የወረቀት ሰንሰለቱን በመበጠስ 2 ኔፊ 1፥13፣ 15፣ 23ን በጋራ ማንበብ ይችላሉ። ሃጢያት እንደ ሰንሰለት የሚሆነው እንዴት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ነው “ሰንሰለ[ቱን] [እንድናወልቅ]” የሚረዳን?

2 ኔፊ 1፥20

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስጠብቅ እባረካለው።

  • ለልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ከጫማ፣ ኮፍያ፣ ጓንት ወይም ከሚጠብቁን ሌሎች ነገሮች ጋር ማነፃፀር ሊረዳ ይችላል? ትእዛዛት እንዴት እንደሚጠብቁን በምታስተምሩበት ጊዜ ምናልባት እነሱ የተወሰኑትን እንዲለኩ ልትፈቅዱላቸው ትችላላችሁ። ትእዛዛቱን ስንጠብቅ “እንደምንበለፅግ” (እንደምንባረክ ወይም እንደምንጠበቅ) በማተኮር 2 ኔፊ 1፥20ን ማንበብ ትችላላችሁ። ትእዛዛትን በመጠበቃችሁ የተባረካችሁበትን ወይም የተጠበቃችሁበትን ጊዜ ተሞክሮ አካፍሉ።

  • በመበልጸግ እና ከግዚአብሔር መቆረጥ መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት (2 ኔፊ 1፥20 ይመልከቱ)፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ጤናማ ተክልን እና ከተክሉ የተቆረጠን ቅጠል ወይም ቅርንጫፍ ልትመለከቱ ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ ኔፊ እና ወንድሞቹ ያደረጉትን ምርጫዎች መከለስ ይችላሉ (1 ኔፊ 2፥11–163፥5–718፥9–11 ይመልከቱ)። የእነዚህ ምርጫዎች ውጤቶች ምንድን ነበሩ? ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኝተን እንድንቆይ የሚረዱን የትኞቹ ምርጫዎች ናቸው?

2 ኔፊ 2፥11፣ 16፣ 27

እግዚአብሔር የመምረጥ ነፃነትን ሰጥቶኛል።

  • ሌሂ ስለ ተቃራኒዎች እና ምርጫዎችን ስለማድረግ ያስተማረውን ልጆቻችሁ እንዲረዱ ለመርዳት፣ ቃልን የመጥራት ጨዋታን መጫወት ትችላላችሁ (ለምሳሌ ብርሃን ከዚያም ልጆቻችሁ ተቃራኒውን ጨለማ ይላሉ)። 2 ኔፊ 2፥11፣ 16ን በጋራ ስታነቡ ተቃርኖዎች ለምን የእግዚአብሔር እቅድ አካል እንደሆኑ እንዲያውቁ እርዷቸው። የተሳሳተ ምርጫን ለማድረግ ስለሚፈተን ልጅ ታሪኮችን ማካፈል ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የተሳሳተ ምርጫው ተቃራኒ ምን እንደሆነ ሊያካፍሉ እና ሊተውኑት ይችላሉ።

  • “በነፃነት” እና “በምርኮ” መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ (2 ኔፊ 2:27)፣ ልጆቻችሁ በብረት ቤት ውስጥ ያለን እና በተፈጥሮ አካባቢው ውስጥ ያለን የእንስሳ ስዕልን ሊስሉ ይችላሉ። ነፃ የሆነው የትኛው እንስሳ ነው? “ነፃ” የሚለውን ቃል በ2 ኔፊ 2፥27 ውስጥ ሲያነቡ ልጆቻችሁ ትክክለኛውን ምስል እንዲጠቁሙ ጋብዙ። ኢየሱስ ክርስቶስ ነፃ እንድሚያደርገን መስክሩ።

  • ትክክለኛውን ምረጡ [Choose the Right]፣” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 239) አይነት መዝሙርን በጋራ ዘምሩ። ከመዝሙሩ ምርጫን ስለማድረግ ምን እንማራለን?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
የሌሂ ቤተሰብ በባህር ዳርቻ ላይ ተንበርክከው

ሌሂ እና ህዝቡ ወደ አዲሱ ዓለም ደረሱ፣ በክላርክ ኬሊ ፕራይስ