ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ካቲት 12–18 ፦ “አስደሳች ህይወት ኖርን።” 2 ኔፊ 3–5


“የካቲት 12–18 (እ.አ.አ)፦ ‘አስደሳች ህይወት ኖርን።’ 2 ኔፊ 3–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 12–18 2 ኔፊ 3–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ኔፊ እና ባለቤቱ

የካቲት 12–18 ፦ “አስደሳች ህይወት ኖርን”

2 ኔፊ 3–5

1 ኔፊን ስታነቡ ኔፊ በሆነ መንገድ የተለየ እንደነበረ ሊሰማችሁ ይችላል። በአካል እንዲሁም በመንፈሳዊነት “አቋ[ሙ] ትልቅ ነበ[ረ]” (1 ኔፊ 2፥16)፣ እንዲሁም ባጋጠመው ፈተናዎች ያልተናወጠ ይመስል ነበር ወይም ቢያንስ የምናስበው ያንን ነው። የኔፊ እምነት የሚያስደንቅ ቢሆንም በ2 ኔፊ 4 ውስጥ የእሱ ቃላት ታማኝ ሰዎች እንኳን አንዳንዴ በፈተናዎች “[የመጎሳቆል]” እና “[የመቸገር]” ስሜት እንደሚሰማቸው ይገልፃሉ። እዚህ ላይ አንድን የሚሞክር፣ ደስተኛ ለመሆን የሚፈልግን ነገር ግን “በኃጢአ[ቱ] የተነሳ ል[ቡ] ያ[ዘነ]፤” ሰውን እናያለን። ይህን እና የሚከተለውን ተስፋ ያለው ቁርጠኝነት እንረዳለን፡ “ይሁን እንጂ በማን እንዳመንኩኝ አውቃለሁ” (2 ኔፊ 4፥15–19 ይመልከቱ)።

ኔፊ እና ህዝቦቹ “አስደሳች ህይወት” መኖርን ሲማሩ (2 ኔፊ 5፥27)፣ ደስታ በቀላሉ ወይም ካለ ምንም ሃዘን እንደማይገኝም ጭምር ተረድተዋል። በስተመጨረሻ “የፅድ[ቃችን] አለት” የሆነውን ጌታን በማመን ይመጣል (2 ኔፊ 4፥35)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 3፥6–24

ጆሴፍ ስሚዝ ወንጌልን ለመመለስ በእግዚአብሔር ተመርጦ ነበር።

ሌሂ ለልጁ ለዮሴፍ በግብፁ ዮሴፍ የተሰጠውን ትንቢትን አካፈለ። ትንቢቱ ስለ ወደፊት “የተመረጠ ባለራዕይ” ማለትም ስለ ጆሴፍ ስሚዝ ነበር። የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመባረክ ጆሴፍ ስሚዝ ምን እንደሚያደርግ ቁጥር 6–24 ምን ይላል? የጆሴፍ ስሚዝ ስራ ለእናንተ እንዴት “ትልቅ ዋጋ” እንደሆነ አስቡ። በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ውስጥ በዳግም የመመለስ ነቢያት [Prophets of the Restoration] ስብስብ ከጆሴፍ ስሚዝ ቪዲዮዎች የተወሰኑ ሃሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ። እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች አስቡ እንዲሁም መልሳችሁን መዝግቡ፦

  • ጆሴፍ ስሚዝ ባስተማረው ምክንያት ስለ ሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ታውቃላችሁ?

  • በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ጌታ በመለሰው ነገር ምክንያት ህይወታችሁ እንዴት ነው የተቀየረው?

  • ዳግም መመለሱ ባይከናወን ኖሮ ህይወታችሁ ምን ሊመስል ይችል ነበር?

የጆሴፍ ስሚዝ ተልዕኮ አንድ አስፈላጊ አካል መፅሐፈ ሞርሞንን ማምጣት ነበር። ከዚህ ምዕራፍ መፅሐፈ ሞርሞን ለምን እንደሚጠቅም ምን ትማራላችሁ? በተለይ፣ ምክንያቶችን ለማግኘት ቁጥሮች 7፣ 11–13፣ 18–24ን መመልከት ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 50፥24–38] (በመጽሐፍ ቅዱስ አባሪ ውስጥ)፤ የወንጌል አርዕስቶችች፣ “ጆሴፍ ስሚዝ፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍት፤ “ለሰውዬው ምስጋና [Praise to the Man]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 27 ይመልከቱ።

ምስል
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ

የጌታ ነቢይ፣ በዴቪድ ሊንድስሊ

2 ኔፊ 4፥15–35

“አቤቱ ጌታ፣ በአንተ ታምኛለሁ።”

“የነፍሴን ነገሮች …እፅፋለሁ” ብሎ ኔፊ ተናገረ (ቁጥር 15)። በ2 ኔፊ 4፥15–35 ውስጥ የፃፈውን ስታነቡ “የነፍ ነገሮች ምንድን ናቸው?” ብላችሁ ጠይቁ። ኔፊ እንዳደረገው እነሱን ለመጻፍን እና ለሌሎች ሰዎች ለማካፈል አስቡ።

ኔፊ የመጨነቅ እና የመረበሽ ስሜት ሲሰማው መፅናናትን እንዴት እንዳገኘ መመልከት ተመሳሳይ ስሜቶች ሲሰማችሁ ሊረዳችሁ ይችላል። በቁጥር 15–35 ውስጥ መፅናናትን የሚያመጣላችሁን ጥቅስ ፈልጉ። በእነዚህ ምንባቦች ውስጥ መፅናናትን ሊያገኝ የሚችል ሰውን ታውቃላችሁ?

በተጨማሪም ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣ “የነፍሴ ነገሮች [The Things of My Soul]፣” ሊያሆና፣ ሀዳር 2021 (እ.አ.አ) 39–41 ይመልከቱ።

2 ኔፊ 5

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመኖር ደስታን ማግኘት እችላለሁ።

ደስተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? ኔፊ ህዝቦቹ “አስደሳች ህይወት” እንደኖሩ ፃፈ (2 ኔፊ 5፥27)። ኔፊ እና ህዝቦቹ ደስተኛ እንዲሆኑ እንዲረዳቸው ያደረጉትን ምርጫዎች መመልከት ትችላላችሁ (ለምሳሌ 2 ኔፊ 5፥6፣ 10–17 ይመልከቱ)። እንደ ኔፊ ሰዎች የደስታ ህይወትን ለመገንባት ምን ሊረዳችሁ ይችላል?

2 ኔፊ 5፥20–21

በላማናውያን ላይ የመጣው እርግማን ምንድን ነው?

በኔፊ ዘመን የላማናውያን እርግማን “ከጌታ ፊት … በሃጢአታቸው የተነሳ [መለየት]” ነበር (2 ኔፊ 5፥20–21)። ይህም ማለት የጌታ መንፈስ ከሕይወታቸው ተነሳ ማለት ነው። ላማናውያን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሲቀበሉ፣ “የእግዚአብሔር እርግማን ከዚያን ጊዜ በኋላ አልተከተላቸውም” (አልማ 23፥18)።

ኔፊያውያን ከላማናውያን ከተለዩ በኋላ ላማናውያን ላይ ጥቁር የቆዳ ምልክት እንደመጣ መፅሐፈ ሞርሞን ይጠቅሳል። የዚህ ምልክት ተፈጥሮ እና ገጽታ ሙሉ በሙሉ አይታወቅም። መጀመሪያ ላይ ምልክቱ ላማናውያንን ከኔፋውያን ለያቸው። ኋላ ላይ፣ ኔፋውያን እና ላማናውያን እያንዳንዳቸው በክፋት እና በጽድቅ ጊዜ ውስጥ ሲያልፉ፣ ምልክቱ ተዛማጅነት የሌለው ሆነ።

በኛ ዘመን ጥቁር ቆዳ መለኮታዊ ሞገስ የማጣት ወይም የእርግማን ምልክት እንዳልሆነ ነቢያት ያረጋግጡልናል። ፕሬዝዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አወጁ፦ “በእግዚአብሔር ፊት አቋማችሁ በቆዳችሁ ቀለም እንደማይወሰን አረጋግጥላችኋለሁ። በእግዚአብሔር ዘንድ ያለ ሞገስ ወይም አለመወደድ ለእግዚአብሔር እና ለትእዛዛቱ ባደረጋችሁት ቁርጠኝነት ላይ እንጂ በቆዳችሁ ቀለም ላይ የተመሰረተ አይደለም” (“እግዚአብሔፍ ያሸንፍ [Let God Prevail]፣” ሊያሆና፣ ሀዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 94)።

ኔፊ እንዳስተማረው፣ “እናም ወደ እርሱ የሚመጡትን ማንንም፣ ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነፃውን …ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው።” (2 ኔፊ 26፥33)።

በተጨማሪም “ሁላችንም በእምነት አንድነት እስክንመጣ ድረስ [Till We All Come in the Unity of the Faith]” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍት ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ኔፊ 3፥6–24

ጆሴፍ ስሚዝ ነብይ ነበረ።

  • እግዚአብሔር በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ስላከናወነው ታላቅ ሥራ ልጆቻችሁን እንዴት እንደምታስተምሩ አስቡ። ለመጀመር ያህል፣ በ2 ኔፊ 3፥6 ውስጥ “ባለራዕይ” የሚለውን ቃል ልጆቻችሁ እንዲያገኙ ለመርዳት እና ነቢያት ባለራዕይ ተብለው የተጠሩት እኛ ማየት የማንችለውን ነገር እንዲያዩ የሰማይ አባት ስለሚረዳቸው እንደሆነ ማስረዳት ትችላላችሁ። ቤተክርስቲያንን የሚመራ ባለራዕይ ስላለ አመስጋኝ ለምን እንደሆናችሁ አካፍሉ።

  • የወንጌል ስነ ጥበብ መጽሐፍ እግዚአብሔር በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ያደረገውን ሥራ ለማስተማር ብዙ ምስሎች አሉት (ምስሎች 89–95 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ስለ ቅዱሳት መጽሐፍት የሚያውቁትን እንዲያካፍሉ አድርጉ። ጆሴፍ ስሚዝ “የተመረጠው ባለራዕይ” ተብሎ የተጠራው ለምንድነው? ጆሴፍ ስሚዝ “ታላቅ ጥቅም” ያለውን ነገር ምን አደረገ? (ቁጥር 7)።

2 ኔፊ 4፥15–35፤ 5

“[የ]ጌታ ነገሮች[ን]” እወዳለሁ።

  • ደስተኛ የሚያደርገን ምንድን ነው? ኔፊን ምን እንዳስደሰተው ለማውቀ ከ2 ኔፊ 4 ውስጥ ጥቅሶችን በጋራ ማንበብን አስቡ (ቁጥር 15–16፣ 20–25፣ 34–35 ይመልከቱ)። “የነፍሴ ነገሮች [The Things of My Soul]፣” በተሰኘው መልዕክቱ ውስጥ ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ ውድ የሆኑትን ሰባት “የጌታ ነገሮችን” አካፍለዋል (ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ) 39–41)። ምናልባት የእሱን ዝርዝሮች በጋራ ልትከልሱት እና ለእናንተ ውድ የሆኑትን “የጌታ ነገሮችን” ልትናገሩ ትችላላችሁ።

  • 2 ኔፊ 5 ኔፋውያን “አስደሳች ህይወት[ን]” እንዲኖሩ የረዳቸውን ነገሮች ይገልፃል (ቁጥር 27)። እነዚህን ነገሮች የሚወክሉ የተወሰኑ ቃላትን ወይም ምስሎችን በምዕራፍ 5 ውስጥ ካሉ ጥቅሶች ጋር ልጆቻችሁ እንዲያዛምዱ እርዷቸው። የተወሰኑት ምሳሌዎች ቤተሰብን (ቁጥር 6)፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት (ቁጥር 10)፣ ቅዱሳ መጽሐፍትን (ቁጥር 12)፣ ስራን (ቁጥር 15 እና 17)፣ ቤተመቅደስን (ቁጥር 16) እና የቤተክርስቲያን ጥሪን (ቁጥር 26) ያካትታሉ። እነዚህ ነገሮች ለእኛ ደስታን የሚያመጡት እንዴት ነው?

2 ኔፊ 5፥15–16

ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

  • 2 ኔፊ 5፥15–16ን ለልጆቻችሁ ሲያነቡ፣ ኔፊ ቤተመቅደስ እንዲገነባ እየረዱት እንደሆነ ሊያስመስሉ ይችላሉ። እንዲሁም ቤተመቅደስን ጨምሮ የተለያዩ ሕንፃዎችን ምስሎች ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ። ቤተመቅደሶች ከሌሎች ሕንፃዎች የሚለዩት እንዴት ነው? ቤተመቅደስ ለእናንተ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ (በተጨማሪም “I Love to See the Temple [ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ]የልጆች መዝሙር፣ 95 ይመልከቱ)።

የትኛውም ጊዜ ማስተማሪያ ጊዜ መሆን ይችላል። ቤተሰባችሁን ማስተማር በሳምንት አንዴ እንደሚደረግ መደበኛ ትምህርት ሳይሆን ሁል ጊዜ እንደምታደርጉት ነገር አስቡ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
ኔፋውያን ቤተመቅደስን እየገነቡ

የኔፊ ቤተመቅደስ፣ በማይክልቲ. ማልም