ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የካቲት 19–25 ፦ “አቤቱ የአምላካችን ዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው።” 2 ኔፊ 6–10


“የካቲት 19–25 ፦ ‘አቤቱ የአምላካችን ዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው።’ 2 ኔፊ 6–10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 19–25 2 ኔፊ 6–10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ኢየሱስ በገትሰመኔ ሲጸልይ

የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ፣ በሄሪ አንደርሰን

የካቲት 19–25 ፦ “አቤቱ የአምላካችን ዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው”

2 ኔፊ 6–10

የሌሂ ቤተሰብ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ቢያንስ 40 ዓመታት አልፈዋል። ከኢየሩሳሌም ግማሽ ዓለም ርቆ በሚገኝ አዲስ ምድር ላይ ነበሩ። ሌሂ ሞተ፣ እናም የእሱ ቤተሰብ በኔፋውያን—“የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያዎችንና ራዕይ [ባ]መኑ”—እና በላማናውያን ማለትም ባላመኑ መካከል ለክፍለ ዘመናት የሚዘልቀውን ግጭት ጀመሩ (2 ኔፊ 5፥6)። የኔፊ ታናሽ ወንድም የሆነው እና ለኔፋውያን እንደ አስተማሪ የተሾመው ያዕቆብ፣ የቃል ኪዳኑን ሕዝብ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማይረሳቸው እንዲያውቁ እንዲሁም እርሱን ፈጽሞ እንዳይረሱት ፈለገ። ይህ ዛሬ በእርግጥ የሚያስፈልገን መልእክት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥15–16 ይመልከቱ)። “እናስታውሰው … አልተጣልንምና። … የጌታ ቃል ኪዳን ታላቅ ነው፣” በማለት ያዕቆብ አወጀ (2 ኔፊ 10፥20–21)። ከእነዚያ ቃል ኪዳኖች መካከል ሞትን እና ሲኦልን ለማሸነፍ “ወሰን [ከ]ሌለው የኃጢያት ክፍያ” ቃል ኪዳን የበለጠ ምንም ታልቅ ነገር የለም (2 ኔፊ 9፥7)። “ስለዚህ፣” አለ ያዕቆብ “ልባችሁን አስደስቱ!” (2 ኛኔፊ 10፥23)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ኔፊ 6–8

እግዚአብሔር ለህዝቡ መሐሪ ነው እናም ቃል ኪዳኖቹን ይፈጽማል።

ህዝቦቹ የእስራኤል ቤት አካል እንደነበሩ እና የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳኖች ማመን እንደሚችሉ እንዲገነዘቡ ለመርዳት በ2 ኔፊ 6–8.ውስጥ የተመዘገቡ የኢሳይያስን ትንቢቶች ያዕቆብ ጠቀሰ። ያ መልእክት ለእናንተም ጭምር ነው ምክንያቱም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝብ አካል ስለሆኑ ነው። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ እንደሚከተሉት ዓይነት ጥያቄዎችን አስቡ።

  • አዳኙ ለእኔ ስላለው የቤዛነት ፍቅር ምን እማራለሁ? ምን ዓይነት ቃላት ወይም ሀረጎች ይህን ፍቅር በተለየ ሁኔት ይገልጻሉ?

  • አዳኙ እርሱን ለሚፈልጉ ሰዎች ምንን ያቀርባል?

  • ለአዳኙ እና ቃል ለተገቡት በረከቶች በበለጠ ታማኝነት “ለመጠበቅ” ምን ማድረግ እችላለሁ?

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 9፥1–26

ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢያት እና ከሞት ያድነኛል።

ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን አድናቆት ለማሳደግ አንዱ መንገድ ካለእርሱ ምን ይፈጠር እንደሆን በማሰብ ነው። 2 ኔፊ 9፥1–26ን ስታነቡ፣ ካለ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኛ ላይ ምን ይፈጠር እንደነበር መዘርዘርን ወይም በአንድ ቀለም ምልክት ማድረግን አስቡ። ከዚያም፣ በሌላ ዝርዝር ወይም ቀለም በአዳኙ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ምን መቀበል እንደምንችል መለየት ትችላላችሁ። በምታነቡት ነገር መሰረት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ለምን እንደሚስፈልገን እንዴት ማስረዳት ትችላላችሁ? “የእግዚአብሔር[ን] ጥበብ፣ ምህረቱ[ን]ና ፀጋው[ን]” ለማመስገን የሚያነሳሳችሁን ምን አገኛችሁ? (2ኛ ኔፊ 9፥8)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከምን እንዳዳነን ከማስተማር በተጨማሪ ያዕቆብ እንዴት እንዳደረገውም ግንዛቤዎችን ሰጥቷል። በ2 ኔፊ 9፥11–15፣ 20–24 ውስጥ የምታገኙትን መመዝገብን አስቡ።

ያዕቆብ በእግዚአብሔር የቤዛነት ዕቅድ ከመደነቁ የተነሳ “አቤቱ የአምላካችን ዕቅድ እንዴት ታላቅ ነው” በማለት አወጀ። የእሱን እወጃ በ2 ኔፊ 9 ውስጥ ይመልከቱ (ብዙዎቹ በቁጥር 8–20 ውስጥ ይገኛሉ)። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ምን ትማራላችሁ? ያዕቆብ የተሰማውን የተወሰኑ ስሜቶች እንዲሰማችሁ የረዷችሁ ምን ዓይነት ልምዶች አሏችሁ? እንደ የአምልኳችሁ እና የጥናታችሁ አካል፣ ስለ እርሱ የሚሰማችሁን ስሜት የሚገልፅን መዝሙር ለመፈለግ aስቡ “How Great Thou Art” (መዝሙር፣ ቁጥር 86)።

በተጨማሪም “ፍትህ፣ ፍቅር እና ምሕረት የሚገናኙበት [Where Justice, Love, and Mercy Meet]፣” “ያዕቆብ ስለ ትንሣኤ ያስተምራል [Jacob Teaches of the Resurrection]” (ቪድዮዎች)፣ የወንጌል ቤተ መጽሐፍት፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ [Atonement of Jesus Christ]፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍትን ይመልከቱ።

2 ኔፊ9፥7

የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ማለቂያ የለውም።

የኢየሱስ ክርስቶስን “ማለቂያ የሌለው የሃጢያት ክፍያ” የበለጠ ለመረዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (2 ኔፊ 9፥7)። ምናልባት በቁጥር ወሰን የሌላቸው የሚመስሉ ነገሮችን—በሜዳ ላይ የሣር ቅጠሎችን፣ በባህር ዳርቻ ላይ ያለ አሸዋ ወይም የሰማይ ላይ ከዋክብትን መመልከት ትችላላችሁ። የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ማለቂያ የሌለው እንዴት ነው? ግላዊም የሆነው እንዴት ነው? በ2 ኔፊ 9 ውስጥ አዳኙ ላደረገላችሁ የአመስጋኝነት ስሜት እንዲሰማችሁ የትኞቹ ሃረጎች ይረዷችኋል?

2 ኔፊ 9፥27–54

ወደ ክርስቶስ መምጣት እና የእግዚአብሔርን እቅድ መከተል እችላለሁ።

2 ኔፊ 9 ውስጥ፣ ያዕቆብ ሁለት ኃይለኛ እና የሚቃረኑ ሃረጎችን ተጠቅሟል፦ “ምህረት የተሞላበት የታላቁ የፈጣሪ ዕቅድ ይፈጸም” እና “የክፉ የብልጠት ዕቅድ (2 ኔፊ 9፥6፣ 28)። ምናልባት መንገድን በመሳል የሰማይ አባት ዕቅድ በማለት ልትሰይሙት ትችላላችሁ። ከዚያም 2 ኔፊ 9:፥7–52ን መርምሩ። ያዕቆብ ይህንን እቅድ እንድንከተል እንዲረዳን የሰጠንን ማስጠንቀቂያዎች እና ግብዣዎች ፈልጉ። ያገኛችሁትን ከመንገዱ ዳር ፃፉ። ሰይጣን ከእግዚአብሔር እቅድ ሊያርቀን የሚሞክረው እንዴት ነው? ለያዕቆብ ማስጠንቀቂያዎች እና ግብዣዎች ምላሽ ምን ለማድረግ ተነሳስታችኋል?

2 ኔፊ 10፥20፣ 23–25

የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ደስታ ሊያመጣልኝ ይችላል።

የያዕቆብ መልዕክት አስደሳች ነበር። “እነዚህን ነገሮች ለእናንተ የምናገረው እንድትደሰቱና ራሳችሁን ለዘለዓለም እንድታነሱ ነው” (2 ኔፊ 9፥3) በማለት ተናግሯል። 2 ኔፊ 10፥20፣ 23–25ን ስታነቡ ልባችሁን የሚያስደስት ነገር ምን ታገኛላችሁ? የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሲሰማችሁ እነዚህን ነገሮች ለማስታወስ ምን ታደርጋላችሁ?

በተጨማሪም ዮሐንስ 16:33፤ ዲ.ታድ ክርስቶፈርሰን፣ “የቅዱሳን ደስታ [The Joy of the Saints]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 15–18፤ “ያዕቆብ ኔፋውያን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ያበረታታል [Jacob Encourages the Nephites to Be Reconciled with God]” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ኔፊ 9፥6–10፣ 19–24

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።

  • ልጆቻችሁ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሰማቸው እና እንዲገነዘቡ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ሊረዳ ይችላል። የጉድጓድ እና የመሰላልን ቀላል ምሳሌ ይጠቀማል። ለኢየሱስ ክርስቶስ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ ከልጆቻችሁ ጋር ለማውራት 2 ኔፊ 9፥21–22ን መጠቀምን አስቡ።

  • ልጆቻችሁ ለምን አዳኝ እንደሚያስፈልገን እንዲገነዘቡ የሚረዳ አንዱ መንገድ ስለ ውድቀት ማስተማር ነው። የአዳም እና የሔዋንን ፣ እንደ ከኤደን ገነት መውጣት [Leaving the Garden of Eden] (የወንጌል ቤተ መጻሕፍት)፣ እና በመስቀል ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል ማሳየት ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ሥዕል ላይ ምን እየሆነ እንዳለ እንዲገልፁ እነሱን መጠየቅን አስቡ። እኛ እንደ አዳም እና ሔዋን የሆንነው እንዴት ነው? ምናልባት 2 ኔፊ 9፥6–10 ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሚያደርገውን እንዲያዩ ሊረዳቸው ይችላል። ልጆቹ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ስሜት እንዲያካፍሉ መጋበዝን አስቡ። እንደ “የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 74–75 መዝሙር ሊረዳቸው ይችላል።

እውነትን በታሪኮች እና በምሳሌዎች አስተምሩ። የምትጠቀሙት ታሪኮች እና ምሳሌዎች እውነትን እንደሚያስተምሩ እርግጠኛ ሁኑ። ለምሳሌ፣ የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ስትጠቀሙ፣ ወደ ላይ ስንወጣ በእያንዳንዱ ደረጃ ሊረዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ “ጉድጓድ” እንደሚወርድ አስተምሩ።

2 ኔፊ 9:20፣ 28–29፣ 42–43፣ 49

“ልቤ በጻድቅነት ትደሰታለች።”

  • ልጆቻችሁ “በጻድቅነት [እንዲደሰቱ]” ወይም ጌታን በደስታ እንዲታዘዙ ለማበረታታት (2 ኔፊ 9፥49)፣ ምናልባት አንድ ልጅ ጥሩ ምርጫን ወይም መጥፎ ምርጫን የሚያደርግበት ምሳሌዎችን ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ምርጫው ደስታን በሚያመጣበት ጊዜ ልጆች እንዲቆሙ፣ ምርጫው ሀዘንን በሚያመጣበት ጊዜ ደግሞ እንዲቀመጡ ጋብዙ። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ስለመረጥን መቼ ነው ደስታ የተሰማን?

  • ልጆቻችሁ የጌታ ትእዛዛት የማይረቡ ወይም ያረጁ እንደሆኑ ከሚያስቡ ሰዎች ጋር የመገናኘት እድል ይኖራቸዋል (እስካሁን ከሌላቸው) ። ትእዛዛትን ለመጠበቅ ለምን ደስተኛ እንደሆንን ለማስረዳት ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ መናገር ትችላላችሁ። ሙሉ በሙሉ ባንረዳውም እንኳን በእግዚአብሔር ምክር መታመን አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? እነዚህን ጥያቄዎች ለማሰብ እና ለመወያየት እርዳታ ለማግኘት 2 ኔፊ 9፥20፣ 28–29፣ 42–43ን እንዲመለከቱ ማበረታታት ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ሰዎችን ሲፈውስ

እርሱ ብዙ የተለያዩ ህመሞችን ፈወሰ፣ በጄ.ከርክ ሪቻርድስ