ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ግንቦት 20–26 : ”የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ገብተናል” ሞዛያ 18–24


“ግንቦት 20–26 : ”የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ገብተናል” ሞዛያ 18-24፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 20–26 ሞዛያ 18-24 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
የሊምሂ ሰዎች እያመለጡ

ሚነርቫ ቴይቸር (1888–1976 (እ.አ.አ))፣ የንጉሥ ሊምሂ እና የህዝቡ ማምለጥ፣ 1949–1951 (እ.አ.አ)፣ ዘይት በሜሶናይት ላይ፣ 35 7/8 × 48 ኢንች። የብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጥበብ ሙዚየም፣ 1969 (እ.አ.አ)።

ግንቦት 20–26 : ”የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ገብተናል”

ሞዛያ 18–24

ሞዛያ 1823–24 ውስጥ የአልማ እና የህዝቡ ታሪክ “ወደ እግዚአብሔር በረት [መምጣት]” ምን ማለት እንደሆነ ያሳያል (ሞዛያ 18፡8)። የአልማ ሰዎች በተጠመቁ ጊዜ፣ “እሱን [ለማገልገል] እናም ትእዛዛቱን [ለመጠበቅ]” ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ገቡ (ሞዛያ 18፡10)። ይህ ለእግዚአብሔር የተደረገ የግል ቁርጠኝነት ቢሆንም፣ እርስ በርስ ከሚያደርጉት ግንኙነትም ጋር የተያያዘ ነበር። አዎን፣ ወደ ሰማይ አባት የሚደረገው ጉዞ ግላዊ ነው፣ እናም ማንም ሰው ቃል ኪዳናችንን ሊጠብቅልን አይችልም፤ ነገር ግን ያ ማለት ብቻችንን ነን ማለት አይደለም። አንዳችን ለሌላው እናስፈልጋለን፡፡ እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነት፣ በመንገዳችን ላይ “[አንዳችን የሌላችንን] ሸክም በመሸከም” (ሞዛያ 18፡8–10)፣ በመረዳዳት እና በማገልገል እግዚአብሔርን ለማገልገል ቃል እንገባለን። ልክ እንደ እኛ የአልማ ሰዎች በእርግጠኝነት የሚሸከሙት ሸክሞች ነበሯቸው። ጌታ “[ሸክማችንን] ማቅለል [እንድንችል]” (ሞዛያ 24፡15) የሚረዳን አንዱ መንገድ፣ እኛም ለእነርሱ ቃል እንደገባነው ከእኛ ጋር ሊያዝኑ እና ሊያጽናኑን ቃል የገቡልንን የቅዱሳን ማህበረሰብ በመስጠት ነው።

በተጨማሪም “ጌታ የአልማ እና የሊምሂን የቃል ኪዳን ሕዝቦች ያድናል” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር ሀሳቦች

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

ሞዛያ 18፡1–17

ስጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ።

ሞዛያ 18 ላይ የተገለጹት አማኞች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን ጥልቅ ስሜት ተመልከቱ። ስለ እሱ ለማወቅ በታላቅ ስጋት በድብቅ መገናኘት ነበረባቸው (ቁጥር 3 ይመልከቱ)። በጥምቀት ቃል ኪዳን ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማሳየት እድል በተሰጣቸው ጊዜ፣ “በደስታ አጨበጨቡ፣ ይህ የልባችን ፍላጎት ነው ብለው ጮኹ” (ሞዛያ 18፡11)።

እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ቃል ኪዳኖቻችሁ ለእናንተ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ለማሰላሰል ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። በተለይ ሞዛያ 18፡8–14ን ስታጠኑ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቡ፡-

  • በጥምቀት ጊዜ ስለገባችሁት ቃልኪዳን ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተማራችሁ? እግዚአብሔር ምን ቃል ገባ? (ቁጥር 10፣ 13 ይመልከቱ)።

  • እግዚአብሔርን የማገልገል ቃል ኪዳን እርስ በርስ ለማገልገል ከምናደርገው ጥረት ጋር እንዴት ይዛመዳል? (ቁጥር 8-9 ይመልከቱ)።

  • “የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድ” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ቁጥር 9)።

  • የጥምቀት ቃል ኪዳናችሁን መጠበቃችሁ “በመንፈስ [እንድትሞሉ]” የሚረዳችሁ እንዴት ነው? (ሞዛያ 18፥14)። ቃል ኪዳናችሁን እንድትጠብቁ መንፈስ እንዴት ይረዳችኋል?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ለምን ቃል ኪዳኖች እና ስነስርዓቶች ለእግዚአብሔር አስፈላጊ እንደሆኑ እንድታሰላስሉ ያደርጓችኋል። በሽማግሌ ጌሪት ደብሊው ጎንግ መልእክት “Covenant Belonging” (ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 80–83) ወይም በፕሬዘዳንት ጂን ቢ.ቢንግሃም መልእክት “ከእግዚአብሔር ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳኖች ያጠነክራሉ፣ ይጠብቁናል እና ለዘለአለም ክብር ያዘጋጁናል” (ሊያሆና ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 66–69)) ውስጥ ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። ስለ ቃል ኪዳኖቻችሁ ለምን አመስጋኝ ናችሁ? የገባችሁትን ቃል ለመጠበቅ ምን እያደረጋችሁ ነው?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች፣ “ጥምቀት፣”፤ “ሽማግሌው አልማ አስተማረ እንዲሁም በሞርሞን ውሃ አጠመቀ” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መፃህፍት ውስጥ ይመልከቱ።

ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ከኋለኛው ቀን ነቢያት እውነትን አስተምሩ። ስታስተምሩ—እና ስትማሩ—በክርስቶስ ላይ እምነትን ለመጨመር ከምርጥ መንገዶች አንዱ በቅዱሳት መጻህፍት እና በኋለኛው ቀን ነቢያት ቃላት ላይ ማተኮር መሆኑን አስታውሱ (ሞዛያ 18፡19 ይመልከቱ)።

ሞዛያ 18:17–30

እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ እና እንዲተባበሩ ያዛል።

አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያስባሉ፣ ቤተክርስቲያን ለምን ያስፈልገናል? የአልማ ሰዎች “በክርስቶስ ቤተክርስቲያን” (ሞዛያ 18፡17) ውስጥ በመሰብሰብ ያገኙትን ዋጋ በመፈለግ ሞዛያ 18፡17–31ን አስሱ። በአልማ ዘመን እና በእኛ ዘመን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምን ተመሳሳይነት ታያላችሁ?

የተደራጀ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ ነው ብሎ ለማያምን ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ? የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ ለምን አመስጋኝ ናችሁ?

የአጥብያ ወይም የቅርንጫፍ አባሎቻችሁ “በአንድነት እና በፍቅር የተጣመሩ እንዲሆኑ” (ሞዛያ 18፡21) ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም ዳሊን ኤች ኦክስን፣ “የቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነት”፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2021 *(እ.አ.አ)፣ 24–26፣ “እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፣” መዝሙሮች፣ ቁ. 308 ይመልከቱ።

ሞዛያ 21-24

ሸክሜን እንድሸከም እግዚአብሔር ይረዳኛል።

የሊምሂ እና የአልማ ሰዎች ምንም እንኳን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆኑም በባርነት ውስጥ ወድቀዋል። በሞዛያ 19–22 ያሉትን የሊምሂን ሰዎችን እና በሞዛያ 1823–24 የአልማ ሰዎችን ታሪክ በማነጻጸር ምን መማር ትችላላችሁ? ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ ለህይወታችሁ ተግባራዊ የሚሆኑ መልዕክቶችን ፈልጉ። ለምሳሌ “ቀስ በቀስ መበልፀግ” ምን ማለት ነው? (ሞዛያ 21፥16)። ይህን መሠረታዊ ሥርዓት እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

ሞዛያ 23:21–2424:8–17

በጌታ መታመን እችላለሁ።

ምንም እንኳን ለኃጢአታቸው ንስሃ ቢገቡም፣ አልማ እና ህዝቡ አሁንም እራሳቸውን በባርነት ውስጥ አግኝተዋል። በጌታ መታመን እና ቃል ኪዳኖቻችንን መኖር ፈተናዎቻችንን ሁልጊዜ እንደማይወስድልን ነገር ግን እንድንሸነፍ እንደሚረዳን የእነሱ ልምድ ያሳየናል። ሞዛያ 23፡21–24 እና 24፡8–17ን ስታነቡ፣ ሁኔታችሁ ምንም ይሁን ምን በጌታ መታመንን ለመማር የሚረዱ ቃላትን እና ሀረጎችን አስተውሉ።

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናርን፣ “ሸክማቸውን በቀላሉ ተሸከሙ [Bear Up Their Burdens with Ease]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 87–90 ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማ የሚረዱ ሀሳቦች

ሞዛያ 18፡7–17

ስጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ።

  • ልጆቻችሁ ለጥምቀት እንዲዘጋጁ ለመርዳት አንዱ አስፈላጊ መንገድ ሲጠመቁ ስለሚገቡት ቃል ኪዳን ማስተማር ነው። ይህ በዚህ ሳምንት መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ምስል እንደማሳየት እና በሞዛያ 18፡9–10 ውስጥ ከእነርሱ ጋር ስላለው ቃል ኪዳን ማንበብ ያህል ቀላል ሊሆን ይችላል። ለታናናሾች ልጆች ይህን እንዲያስተምሩ አስቀድሞ የተጠመቀ ልጅን ለመጋበዝ አስቡ። ልጆቻችሁ ስለ ጥምቀታችሁ ሲሰሙ ደስ ሊላቸው ይችላል። ከእግዚአብሔር ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳኖች መጠበቅ ህይወታችሁን እንዴት ባረከው?

  • የተጠመቁ ልጆች ስለገቡት ቃል ኪዳኖች ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን መጠቀም እና በየሳምንቱ በቅዱስ ቁርባን ወቅት ማደስ ይችላሉ። ምናልባት ልጆቻችሁ በሞዛያ 18፡8–10 የተገለጸውን የጥምቀት ቃል ኪዳን ከቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች ጋር ሊያወዳድሩ ይችሉ ይሆናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፡77፣ 79 ይመልከቱ)። ልክ እንደ ጥምቀታችን ቅዱስ ቁርባንን ልዩ፣ የአክብሮት ጊዜ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ምስል
ወጣት ልጅ እየተጠመቀች

ስንጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንገባለን።

ሞዛያ 18፡17–28

ስጠመቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል እሆናለሁ።

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ምን ማለት እንደሆነ ልጆቻችሁ ያውቃሉ? በሞዛያ 18፡17–28 ውስጥ የቤተክርስቲያኗ አባላት ያደረጓቸውን ነገሮች የሚወክሉ ምስሎችን እንዲያገኙ ለመርዳት አስቡ። ለምሳሌ፣ የክህነት ሥርዓት እና የአሥራት ክፍያ ሥዕሎች (የወንጌል ጥበብ መጽሐፍቁጥር 106፣ 113) ቁጥር 18 እና 27-28ን ሊወክሉ ይችላሉ። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ ንገሯቸው።

  • ልጆች “በአንድነት እና አንዱ ለሌላኛው ባለው ፍቅር [እንደተጣበቁ]” (ሞዛያ 18፡21) እንዲሰማቸው መርዳት በሕይወታቸው ሙሉ ከቤተክርስቲያን ጋር እንዲገናኙ ያግዛቸዋል። ሞዛያ 18፡17–28ን እንዲያነቡ ልጆቻችሁን ለመጋበዝ አስቡ። በአልማ ዘመን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እርስ በርስ ለመዋደድ እና አንዳቸው ሌላውን ለማገልገል ምን አደረጉ? ይህንን በአጥኒያ፣ በቅርንጫፍ ወይም በማህበረሰብ ውስጥ እንዴት ማድረግ እንችላለን? እንደ “ከአንተ ጋር እራመዳለሁ” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 140) ያለ የፍቅር መዝሙር ይህን መልእክት ሊያጠናክር ይችላል።

ሞዛያ 24:8–17

እግዚአብሔር ሸክሜን ቀላል ሊያደርግልኝ ይችላል።

  • ቀላል የተግባር ትምህርት መማርን የበለጠ የማይረሳ ያደርጋል። አንድን ቦርሳ በከባድ ዕቃዎች መሙላት (ሸክሞችን ለመወከል) እና አንድ ልጅ ቦርሳውን እንዲይዝ ለመጋበዝ አስቡ። ሞዛያ 24፡8–17ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ አልማ እና ህዝቡ በሸክማቸው የእግዚአብሔርን እርዳታ ለመጠየቅ ስላደረጉት ነገር በሰሙ ቁጥር አንድን ነገር ከቦርሳው እንዲያወጡ ጠይቋቸው። የሰማይ አባት የእርሱን እርዳታ በምንፈልግበት ጊዜ ሸክማችንን እንዴት እንደሚያቀል ከእነሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
ሰዎች እየተጠመቁ

የሞርሞን ውሃ፣ በጆርጅ ኮኮ