ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ግንቦት 27–ሰኔ 2 : “እነርሱ የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው ተጠርተዋል።” ሞዛያ 25–28


“ግንቦት 27–ሰኔ 2 : ‘እነርሱ የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው ተጠርተዋል።’ ሞዛያ 25-28፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 27–ሰኔ 2 ሞዛያ 25-28 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
መልአክ ለአልማ እና ለሞዛያ ልጆች ተገለጠ

የታናሹ አልማ መለወጥ፣ በጋሪ ኤል.ካፕ

ግንቦት 27–ሰኔ 2 : “እነርሱ የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው ተጠርተዋል።”

ሞዛያ 25–28

ለሦስት ትውልዶች ያህል በተለያዩ አገሮች ከኖሩ በኋላ፣ ኔፋውያን እንደገና አንድ ሕዝብ ሆኑ። አሁን የሊምሂ፣ የአልማ፣ እና የሞዛያ—ከኔፊ ያልተወለዱ የዛራሔምላ ሰዎች ሳይቀሩ—ሁሉም “ከኔፋውያን ጋር ተቆጠሩ” (ሞዛያ 25፡13)። ብዙዎቹም እንደ አልማ ሰዎች የጌታ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ፈለጉ። ስለዚህ “የክርስቶስን … ስም [በራሳቸው] ለመውሰድ የፈለጉ” ሁሉ ተጠመቁ፣ “እናም የእግዚአብሔር ሰዎች [ተባሉ]” (ሞዛያ 25፡23–24)። ከዓመታት ግጭት እና ምርኮ በኋላ፣ ኔፋውያን በመጨረሻ የሰላም ጊዜ የሚያገኙ ይመስል ነበር።

ብዙም ሳይቆይ ግን የማያምኑት ቅዱሳንን ማሳደድ ጀመሩ። ይህን በተለይ ልብ የሚሰብር ያደረገው ብዙዎቹ የማያምኑት የአማኞቹ የራሳቸው ልጆች መሆናቸው ነው—የሞዛያ ልጆች እና አንድ የአልማ ልጅ ጨምሮ “በማደግ ላይ ያሉ ትውልዶች” (ሞዛያ 26፡1) ነበሩ። ታሪኩ አንድ መልአክ ስላደረገው ተአምራዊ ጉብኝት ይናገራል። ነገር ግን የዚህ ታሪክ እውነተኛ ተአምር የመላእክት ለአመጸኛ ልጆች መገለጥ ብቻ አይደለም። መለወጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በሁላችንም ውስጥ ሊከሰት የሚገባው ተአምር ነው።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር ሀሳቦች

ሞዛያ 26፡1–6

ሌሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ መርዳት እችላለሁ።

መለወጥ ግላዊ ነው —ለልጅ ልጅ እንደ ውርስ ሊተላለፍ አይችልም። ሞዛያ 26፡1–6ን ስታነቡ፣ “በማደግ ላይ ያሉ ትውልዶች” የወደቁበትን ምክንያቶች አስቡ እንዲሁም አለማመናቸው የሚያስከትለውን መዘዝ አስተውሉ። ወደ ክርስቶስ ልታመጧቸው ስለምትፈልጓቸው ሰዎችም ታስቡ ይሆናል። በሞዛያ 25–28 ላይ ባደረጋችሁት ጥናት ሁሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲያሳድጉ ለመርዳት ልታደርጓቸው የምትችሏቸውን ነገሮች መንፈስ በሹክሹክታ ሊናገር ይችላል።

ሞዛያ 26፡6–39

የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋዮች ፈቃዱን ለማድረግ ይፈልጋሉ።

አንዳንድ ጊዜ እንደ አልማ ያለ የቤተክርስቲያን መሪ ምን ማድረግ እንዳለበት ሁል ጊዜ በትክክል ያውቃል ብለን እናስብ ይሆናል። በሞዛያ 26 ውስጥ አልማ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላጋጠመው ችግር እናነባለን። አልማ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምን አደረገ? ( ሞዛያ 26፡13–14፣ 33–34፣ 38–39 ይመልከቱ)። በቤተሰባችሁ ወይም በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዴት መፍታት እንደምትችሉ የአልማ ልምድ ምን ይጠቁማል?

ሞዛያ 26፡15–32 ውስጥ ጌታ አልማን ምን አስተማረው? አንዳንድ የጌታ መልሶች ለአልማ ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ እንዳልነበሩ አስተውሉ። ይህ ስለ ጸሎት እና የግል መገለጥ ምን ይጠቁማል?

መርሆች ዘላለማዊ ናቸው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉት ታሪኮችና ትምህርቶች በሕይወታችሁ ላይ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ አስቡ። ለምሳሌ፣ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ፣ “እንደ አልማ ያሉ ምን ገጠመኞች አሉኝ?” ወይም “በአልማ የተነገሩ የትኞቹ እውነቶች ሊረዱኝ ይችላሉ?”

ሞዛያ 26፡15–31

ንስሃ ስገባ እና ሌሎችን ይቅር ስል እግዚአብሔር በነጻ ይቅር ይለኛል።

ንስሃ እና ስርየት በሞዛያ 26–27 ውስጥ ያሉ ተደጋጋሚ ጭብጦች ናቸው። በሞዛያ 26፡22–24 29–31 27፡23–37 ስለ ንስሐ እና ስርየት የሚያስተምሩ ቃላትን እና ሀረጎችን ፈልጉ።

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር በእርግጥ ይቅር ብሏቸው እንደሆን ያስቡ ይሆናል። ሽማግሌው አልማ ይህ ለሚያሳስበውን በዛራሔምላ የሚገኘን የቤተክርስቲያን አባል እንዴት የሚመክረው ይመስላችኋል? አልማ ይህንን የቤተክርስቲያኗን አባል ሊረዳው የሚችለውን ከሞዛያ 26፡15–31 ከጌታ ምን ተማረ? (በተጨማሪም ሞሮኒ 6፡8ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፡16–1858፡42–43 ይመልከቱ)።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

ሞዛያ 27፡8–3728፡1–4

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ ተሻለ ሁኔታ መለወጥ እችላለሁ።

ታናሹ አልማ መንፈሳዊ ዳግም መወለድ እንደሚያስፈልገው ግልጽ ነበር። እሱ እና የሞዛያ ልጆች “ከሁሉ በላይ መጥፎ የሆኑ ኃጢአተኞች” (ሞዛያ 28፡4) ነበሩ። ነገር ግን ከተለወጠ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣ መለወጥ ለሁሉም አስፈላጊ እንደሆነ አልማ መስክሯል፡- “አትደነ[ቁ] … ሁሉም… በድጋሚ መወለድ ይገባቸዋል” (ሞዛያ 27፡25፤ አጽንዖት ተጨምሮበታል) ሲል ተናግሯል፣።

ሞዛያ 27፡8–37 ውስጥ ስላለው የአልማ ልምድ ስታነቡ፣ ራሳችሁን በሱ ታሪክ ውስጥ ለማስገባት አስቡ። በእናንተ ውስጥ መለወጥ ስላለባቸው ነገሮች ማሰብ ትችላላችሁ? እንደ አልማ አባት “በታላቅ እምነት” ማን እየጸለየላችሁ ሊሆን ይችላል? “[እናንተን] የእግዚአብሄርን ኃይልና ሥልጣን ለማሳመን” የረዱት የትኞቹ ተሞክሮዎች ናቸው? ( ሞዛያ 27፥14) ጌታ ለእናንተ ወይም ለቤተሰባችሁ “ማስታወስ” ያለባችሁን ምን “ታላቅ ነገር” አደረገ? (ሞዛያ 27፥16) ዳግመኛ መወለድ ምን ማለት እንደሆነ ከትንሹ አልማ ቃል እና ድርጊት ምን ተማራችሁ? ምን ምሳሌዎችን አያችሁ?

ምንም እንኳን ገጠመኞቻችሁ እንደ አልማ አይነት ድራማዊ ወይም ድንገተኛ ባይሆኑም አዳኙ እንድትቀየሩ ወይም እንደገና እንድትወለዱ የሚረዳችሁን አንዳንድ መንገዶች ለመመዝገብ ትንሽ ጊዜ ውሰዱ። እንደ “I Stand All Amazed” አይነት ስሜታችሁን የሚገልጽ መዝሙር ልትዘምሩ ወይም ልትሰሙ የምትችሉት መዝሙር አለ? (መዝሙሮች፥ ቁጥር 193)። የእናንተን ተሞክሮ በመስማት ማን ሊጠቀም ይችላል?

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ዳግመኛ መወለድን ኪያር ወደ ኮምጣጤነት ከሚቀየርበት ሂደት ጋር አነጻጽሮታል (“ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ [Ye Must Be Born Again]ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ)፣ 19–22 ይመልከቱ)። ይህ ንጽጽር ስለ መለወጥ ምን ያስተምራል?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁኑ [Become like Jesus Christ]፣” የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፤ “አልማ ከእግዚአብሔር መወለዱን ይመሰክራል [Alma Testifies He Has Been Born of God]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ይመልከቱ።

ሞዛያ 27፡8–24

እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰምቶ እንደ ፈቃዱ እና ጊዜው መልስ ይሰጣል።

ምናልባት እናንተ አጥፊ ምርጫዎችን በሚያደርግ የቤተሰብ አባል ምክንያት በአዛውንቱ አልማ ሁኔታ ውስጥ ገብታችሁ ይሆናል። ከሞዛያ 27:8–24 ላይ ተስፋ የሚሰጣችሁን ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች ለሌሎች በምትጸልዩ ጊዜ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶችን እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞዛያ 26:30–31

ጌታ ይቅር እንድል ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ ጌታ አልማን ስለ ይቅርታ ያስተማረውን እንዲያውቁ ለመርዳት ሞዛያ 26፡29–31ን እንዲያነቡ እና “ይቅር [ማለት]” የሚለው ቃል ስንት ጊዜ እንደሚገኝ እንዲቆጥሩ አድርጓቸው። እነዚህ ጥቅሶች ሌሎችን ይቅር ስለማለት ምን ያስተምራሉ? (በተጨማሪም “እርዳኝ ውድ አባት፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ 99 ይመልከቱ።)

  • የአዳኙን የይቅርታ ምሳሌ ለማጉላት፣ በመስቀል ላይ የእሱን ምስል ማሳየት እና ሉቃስ 23፡33–34ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰቀሉትን ሰዎች የሰማይ አባት ምን እንዲያደርግ ጠየቀ? ከዚህ ውይይት በኋላ ልጆቻችሁ እርስ በርሳቸው ይቅር የመባባል ጨዋታ መጫወት ይችላሉ።

  • አንዳንድ ጊዜ ስህተት ስንሠራ ራሳችንን ይቅር ማለት ከባድ ነው። እግዚአብሔር ለአልማ የተናገራቸው ቃላት እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? ልጆቻችሁ እግዚአብሔር ይቅር ይለኛል ብሎ ከማያስብ ሰው ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ሊያስመስሉ ይችላሉ። በሞዛያ 26፡22–23፣ 29–30 ውስጥ ያንን ሰው ሊረዳ የሚችል ነገር እንዲፈልጉ ልጆቻችሁን ጋብዟቸው።

ሞዛያ 27፡8–37

ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ እሱን እንድመስል ይረዳኛል።

  • የታናሹ አልማ እና የሞዛያ ልጆች መለወጥ በአዳኙ ኃይል ማንም ሰው መለወጥ እንደሚችል ለልጆቻችሁ ሊያሳይ ይችላል። እናንተ ወይም ልጆቻችሁ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች፣ የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ እና የተወሰኑ ቁልፍ ጥቅሶችን ከሞዛያ 27፡8–37 በመውሰድ ታሪኩን ለመንገር ልትጠቀሙ ትችላላችሁ (በተጨማሪም በ“ምዕራፍ 18፡ ታናሹ አልማ ንስሃ ገባ” የሚለውን የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 49-52 ይመልከቱ)። አልማ ንስሃ እንደገባ እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲለውጥ እንደረዳው ለማስተማር ለቁጥር 24 ልዩ ትኩረት ስጡ። ከፈለጉ ልጆቻችሁ ታሪኩን እንዲተውኑ አድርጉ።

ምስል
ታናሹ አልማ ወደ አባቱ ቤት ሲወሰድ

አባቱ ተደሰተ፣ በዋልተር ሬን

ሞዛያ 27፡8–24

የምወዳቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲባርክ መጸለይ እና መጾም እችላለሁ።

  • አንድ ላይ ሞዛያ 27፡8–24 አንብቡ፤ ከዚያም ልጆቻችሁ አልማ እና ህዝቡ ታናሹን አልማ ለመርዳት ያደረጉትን ነገር እንዲለዩ ጠይቋቸው። ለሆነ ሰው ጾማችሁ እና ጸልያችሁ ታውቃላችሁ? ተሞክሮዎቻችሁን ለልጆቻችሁ አካፍሉ እንዲሁም የራሳቸውን እንዲያካፍሉ አድርጉ።

  • እናንተ ወይም ልጆቻችሁ የእግዚአብሔርን እርዳታ የሚፈልግ ሰው ታውቃላችሁ? የአልማን ምሳሌ በመከተል፣ ምናልባት አንድ ላይ ለዚያ ሰው መጸለይ እንዲሁም ልጆቻችሁ ከቻሉ መጾም ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
መልአክ ለታናሹ አልማ ታየ

ለታናሹ አልማ የታየ መልአክ ምስል በኬቨን ኪሌ