ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 10–16 ፤ “በልባችሁስ ይህንን ታላቅ ለውጥ ተለማምዳችኋልን?” አልማ 5–7


“ሰኔ 10–16 (እ.አ.አ)፤ ‘በልባችሁስ ይህንን ታላቅ ለውጥ ተለማምዳችኋልን?’ አልማ 5-7፤ “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 10-16 ። አልማ 5-7 “ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ታናሹ አልማ ዞራማውያንን እያስተማረ

ታናሹ አልማ ዞራማውያንን እያስተማረ

ሰኔ 10–16 (እ.አ.አ)፤ “በልባችሁስ ይህንን ታላቅ ለውጥ ተለማምዳችኋልን?”

አልማ 5–7

አልማ የዛሬውን የተጎዳን ወይም የታመመን ልብን ጤናማ በሆነ ሰው ልብ የሚተካበትን የህይወት አድን ንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገናዎች አያውቅም። ነገር ግን አዳኙ “ዳግም [በመወለድ]” የመንፈሳዊ ህይወት አዲስነት ስለሚሰጠን (አልማ 5፡14፣ 49 ይመልከት) ስለ ተአምረኛው “የልብ መለወጥ” (አልማ 5፡26) ያውቅ ነበር። አልማ ይህ የልብ ለውጥ በርግጥ ብዙዎቹ ኔፋውያን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ማየት ችሏል። አንዳንዶቹ ሀብታሞች ሌሎች ድሆች፣ አንዳንዶቹ ትዕቢተኞች ሌሎች ትሁታን፣ አንዳንዶች አሳዳጆች ሌሎች ደግሞ ስደተኞች ነበሩ (አልማ 4፡6–15 ይመልከቱ)። ነገር ግን ሁሉም፣ እንደ ሁላችንም ለመፈወስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት አስፈልጓቸው ነበር። ኩራትን ለማሸነፍም ሆነ መከራዎችን ለመታገስ እየፈለግን ብንሆን፣ የአልማ መልእክት አንድ ነው፤ “ኑ አትፍሩ” (አልማ 7፡15)። አዳኙ የደነደነ፣ ኃጢአተኛ ወይም የቆሰለ ልብን ወደ ትሁት፣ ንጹህ እና አዲስ ይለውጥ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 5፡14–33

ታላቅ የልብ ለውጥ ሊኖረኝ እና በቀጣይነት ሊሰማኝ ይገባኛል።

ፕሬዘደንት ኤም ሩሰል ባላርድ እንዲህ አሉ፡- “እራሴን ‘እንዴት ነኝ?’ ብዬ ለመጠየቅ በየጊዜው ጊዜ መስጠት አለብኝ… በዚህ ግላዊ ግምገማ ወቅት ለእኔ እንደመመሪያ፣ በአልማ አምስተኛ ምዕራፍ ላይ የሚገኙትን ውስጠ-ቃላትን ማንበብ እና ማሰላሰል እወዳለሁ” (“ተመለስ እና ተቀበል [Return and Receive]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 64)።

እራሳችሁን ቃለ መጠይቅ እንደምታደርጉ እና ልባችሁን እንደምትመረምሩ በማሰብ አልማ 5፡14–33ን ለማንበብ አስቡ። ለጥያቄዎች ምላሾቻችሁን ለመመዝገብ ትፈልጉ ይሆናል። ስለ ራሳቸሁ ምን ትማራላችሁ? በቃለ መጠይቃችሁ ምክንያት ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ዴል ጂ ረንላንድ፣ “የልብ ኃያል ለውጥን መጠበቅ [Preserving the Heart’s Mighty Change]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ)፣ 97–99 ይመልከቱ።

ምስል
ሴት ልጅ አልጋ አጠገብ እየጸለየች

ወደ እግዚአብሄር ስንመለስ “የልብ [ለውጥ]” ሊኖረን ይችላል።

አልማ 5፡44–51

በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የራሴ የሆነ የአዳኙን እና የትምህርቱን ምስክርነት ማግኘት እችላለሁ።

አልማ 5 ውስጥ፣ አልማ የአዳኙን ምስክርነት እንዴት እንዳገኘ ሲገልጽ፣ መልአክን የማየት ልምዱን አልጠቀሰም (ሞዛያ 27፡10–17 ይመልከቱ)። አልማ ለራሱ እውነትን እንዴት አወቀ? ምናልባት በአልማ 5፡44–51 ያገኛችሁትን የኢየሱስ ክርስቶስን እና የትምህርቱን ምስክርነት ለማግኘት “የአዘገጃጀት መመርያ” ለመጻፍ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። አልማ የትኞቹን “ግብአቶች” (የወንጌል እውነቶችን) እና “መመሪያዎች” (እውነትን ለማግኘት ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ነገሮች) አካተተ? ከራሳችሁ ተሞክሮ ወይም በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት ሌሎች ልምዶች ለአሰራራችሁ ምን “ግብአቶች” እና “መመሪያ” ማከል ትችላላችሁ?

አልማ 7

“እናንተ በጽድቅ ጎዳና እንደሆናችሁ ተገንዝቢያለሁና።”

አንዳንድ ጊዜ ለንስሃ መጠራት እንደነበረባቸው በዛራሔምላ እንደነበሩ ሰዎች ነን (አልማ 5፡32 ይመልከቱ)። ሌላ ጊዜ ደግሞ “በጽድቅ ጎዳና” (አልማ 7፡19) ለመራመድ እየሞከሩ እንደነበሩ እንደ ጌዴዎን ሰዎች። አልማ በዛራሔምላ (በአልማ 5) ከተናገረው ጋር ተመሳሳይ የሆነ በጌዲዮን (በአልማ 7) መልእክት ላይ ምን ታገኛላችሁ? ምን ልዩነቶች አስተውላችኋል? አልማ ያስተማራቸውን “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በሆነው ጎዳና ላይ” እንድትቀጥሉ የሚረዳችሁን ነገሮች ፈልጉ (አልማ 7፡19)።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

አልማ 7፥7-16

አዳኙ ኃጢአቶቼን፣ ህመሜን እና መከራዎችን በራሱ ላይ ወስዷል።

ማንም ሰው የእናንተን ችግር ወይም ፈተና እንደማይረዳ ሆኖ ተሰምቷችሁ ያውቃል? እንደዚያ ከሆነ፣ አልማ ያስተማረው እውነት ሊረዳችሁ ይችላል። ስታነቡ፣ እነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኙ መስዋዕትነት ዓላማዎች የሚያስተምሩትን አስቡ። አዳኙ የተቀበለው መከራ እና የተሰቃየበት ምክንያት በሚሉ ርዕሶች ሰንጠረዥ ስሩ፤ ከዚያም በአልማ 7፡7–16 ያገኛችሁትን ነገር ዘርዝሩ (በተጨማሪም ኢሳያስ 53፡3–5 ይመልከቱ)። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን ስለተሠቃየባቸው የተወሰኑ ጊዜያት ታስታውሳላችሁ? ከቅዱሳት መጻሕፍት የተወሰኑ ምሳሌዎች እነሆ፡- ማቴዎስ 4፡1–1326:55–5627:39–44ማርቆስ 14:43–46ሉቃስ 9፡58። ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ተጨማሪ ነገር ወደ ዝርዝራችሁ ማከል ትችላላችሁ?

አዳኙ ስለ እናንተ እንደተሰቃየ ማመን አንድ ነገር ነው። ነገር ግን የእርሱ መሰቃየት በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ላይ ለውጥ የሚያመጣው እንዴት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት “[እንደሚረዳችሁ]” የሚያሳዩ አንዳንድ ጥቅሶች እዚህ ይገኛሉ፣ ኢኖስ 1፡5–6ሞዛያ 16፡7–821:1524:14–153 ኔፊ 17፡6–7ኤተር 12:27–29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፡7–10። ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተማራችሁ? እናንተን ለመርዳት የሚመጣባቸው ሌሎች መንገዶች ምንድናቸው? የእሱን እርዳታ መቼ አገኛችሁ?

እንደ “በየሰዓቱ እፈልግሃለሁ” ወይም “አዳኜ እንደሚኖር አውቃለሁ” (መዝሙሮች፣ ቁ. 98፣ 136) ያሉ መዝሙሮች ለአዳኙ እርዳታ ያላችሁን አድናቆት ጥልቅ ያደርጋሉ። በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ ለእርሱ ያላችሁን ስሜት የሚገልጹት ሐረጎች የትኞቹ ናቸው?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶችን፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት፣ “የእሱ ጸጋ” (የቪዲዮ ስብስብ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ላይ ይመልከቱ።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስክሩ። ስለ አዳኙ እና ስለ አምላክነቱ፣ ስለጸጋው እና ስለ ፍቅሩ ምስክርነታችሁን የምታካፍሉበትን መንገዶች አስቡ። የምታስተምሯቸው ሰዎች ስለ እርሱ ያላቸውን ስሜት እንዲያካፍሉ የሚገፋፏቸውን ጥያቄዎች በመጠየቅ ስለ እርሱ እንዲመሰክሩ ማበረታታት ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 5፡44–48

የራሴን ምስክርነት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ማግኘት እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ የእራሳቸውን ምስክርነት ማሳደግ እንዲማሩ ለማገዝ ከታች ያለውን ምስል አሳይታችሁ ህጻናት እንስሳት እንዲያድጉ እንዴት እንደምናግዝ ጠይቋቸው። ይህን ምስክርነታችንን ከመንከባከብ ጋር ማያያዝ ትችላላችሁ። ምስክሮቻችን ምን ዓይነት እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል? እያደጉ መሆናቸውንስ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

    ምስል
    ሁለት ወንድ ልጆች ከትንንሽ እንስሳት ጋር

    ወንጌልን መቀበል አዲስ ሕይወት እንደመጀመር ነው።

  • አልማ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠንካራ ምስክርነቱን ያገኘው እንዴት ነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከልጆቻችሁ ጋር አልማ 5፡44–46ን ማንበብ ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ ምስክርነታቸውን ለማጠናከር በዚህ ሳምንት አንድ ነገር ለማድረግ እቅድ ሊጽፉ ይችሉ ይሆናል።

አልማ 7፥10-–13

አዳኙ ኃጢአቶቼን፣ ህመሜን እና መከራዎችን በራሱ ላይ ወስዷል።

  • ልጆቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስብላቸው እና እንደሚረዳቸው እንዲያውቁ አልማ 7፡10–13ን እንዲረዱ እንዴት ማገዝ ትችላላችሁ? ምናልባት ሲታመሙ ወይም ሌላ ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ያሳዘናቸውን ነገር እንዲናገሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ሌሎች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የረዷቸው እንዴት ነው? አዳኙ እነዚህን ነገሮች እንደገጠሙት ምስክርነታችሁን ስጡ፣ እናም እሱ ያጽናናችሁ እና የረዳችሁን ጊዜ ተናገሩ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ አልማ 7፡11–13 ስታነቡ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የተቀበለውን መከራ ፈልጉ። ይህን ዓረፍተ ነገር ለማጠናቀቅ ልጆቻችሁ ያገኙትን ቃላት እና ሀረጎች እንዲጠቀሙ ጋብዟቸው፡- “ኢየሱስ መከራ የተቀበለው እንዲረዳኝ ነው። ኢየሱስ በመከራችን እንደሚረዳን ማወቃችን እንዴት ይጠቅመናል? የእርሱን እርዳታ የምንቀበለውስ እንዴት ነው? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታችሁን አካፍሉ።

አልማ 5:147፡19–20

ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ወደ ሰማይ አባት በሚመልሰው ቀጥተኛ መንገድ ላይ ያቆየኛል።

  • አልማ 5፡14ን በምታነብበት ጊዜ ልጆቻችሁ መስታወት እንዲመለከቱ አድርጉ (በተጨማሪም የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ተመልከቱ)። በፊታችን የአዳኙን መልክ መያዝ ማለት ምን ማለት ነው?

  • ልጆቻችሁ ጥሩ ምርጫ መምረጥ እንዲማሩ ለመርዳት የአልማን ወደ ሰማይ አባት የሚመልሰውን መንገድ መግለጫ እንዴት መጠቀም ትችላላችሁ? አልማ 7፡19–20ን ልታነቡላቸው ትችላላችሁ፣ ከዚያም በ“ጠማማ ጎዳና” እና በቀና መንገድ እየተራመዱ እንደሆነ እንዲተውኑ ፍቀዱላቸው። በመንገዱ ላይ እንድንቆይ የሚረዱን ምርጫዎችን እና ከመንገድ የሚያወጡን ሌሎች ምርጫዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው። እንዲሁም የኢየሱስን ምስሎች በአንድነት ማየት እና ወደ ሰማይ አባት የምንመለስበትን መንገድ ሊያሳየን ስላደረጋቸው ነገሮች ማውራት ትችላላችሁ። እንደ “እንደ ኢየሱስ ለመሆን እየሞከርኩ ነው፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79) ያለ መዝሙር የተወሰነ ሃሳብ ይሰጣል።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ቀይ ካባ ለብሶ

ጠበቃችን በጄይ ብርያንድ ዋርድ