ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 24-30 (እ.አ.አ): “ወደ ጌታ እረፍት ይገቡ ዘንድ” አልማ 13–16


“ሰኔ 24-30 (እ.አ.አ) : “ወደ ጌታ እረፍት ይገቡ ዘንድ” አልማ 13-16፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023)

“ሰኔ 24-30 አልማ 13-16፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ምስል
አልማ እና አሙሌቅ ከእስር ቤት ውስጥ ሲወጡ

አልማ እና አሙሌቅ ከእስር ቤት ሲፈቱ የሚያሳይ ምስል፣ በአንድሪው ቦስሊ

ሰኔ 24-30 (እ.አ.አ): “ወደ ጌታ እረፍት ይገቡ ዘንድ”

አልማ 13–16

በብዙ መንገድ፣ በአሞኒሃ ህይወት ለአሙሌቅ እና ለዚኤዝሮም መልካም ነበር። አሙሌቅ “ትንሽ ዝና [ያለው] ሰው” አልነበረም። “ብዙ ነገድና ወዳጆች”፣ “ብዙ ሀብት[ም]” (አልማ 10፡4) ነበረው። ዚኤዝሮም “ብዙ እንቅስቃሴዎች” የሚያደስቱት ባለሙያ ጠበቃ ነበር (አልማ 10፡31)። ከዚያም አልማ ለንስሃ እና “ወደ ጌታ እረፍት” (አልማ 13፡16) እንዲገባ ግብዣ ይዞ መጣ። ለአሙሌቅ፣ ለዚኤዝሮም እና ሌሎችም ይህንን ግብዣ መቀበል መስዋዕትነትን የሚጠይቅ አልፎ ተርፎም ሊቋቋሙት የማይችሉትን መከራ አስከትሏል።

ነገር ግን ታሪኩ በዚህ አያበቃም። በአልማ 13–16፣ በመጨረሻ “ለመዳን የሆነውን የክርስቶስ ኃይል” በሚያምኑ ሰዎች ላይ ምን እንደሚፈጥር እንማራለን (አልማ 15፡6)። አንዳንድ ጊዜ መዳን አለ፣ አንዳንድ ጊዜ ፈውስ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገሮች በህይወት ውስጥ ቀላል አይሆኑም። ነገር ግን ሁልጊዜ፣ “ጌታ [ህዝቡን] በክብር ወደ ራሱ [ይቀበላቸዋል]” (አልማ 14፡11)። ሁል ጊዜ “በክርስቶስ ላይ [ባለን] እምነት መሰረት…ጌታ ሃይልን ” (አልማ 14፡28) ይሰጣል። እናም ያ እምነት ሁል ጊዜ “ዘላለማዊ ህይወት ለመቀበል በተስፋ” (አልማ 13፡29) ይሞላናል። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ፣ በእነዚህ ተስፋዎች መጽናናት ትችላላችሁ፣ እናም አልማ ወደ “ጌታ እረፍት” ስለመግባት ሲናገር ምን ማለቱ እንደሆነ በደንብ ልትረዱ ትችላላችሁ (አልማ 13፡16)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 13፡1–19

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የክህነት ስነስርዓቶች ለመዳን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመለክቱኛል።

ወደ “ጌታ እረፍት” እንድንገባ (አልማ 13፡16) ወይም ለዘላለማዊ ህይወት በአልማ 13 ውስጥ የአልማ ቃላት ስለ እግዚአብሔር የክህነት ስልጣን እና አላማው ኃይለኛ እውነቶችን ይገልጻሉ። ምናልባት በአልማ 13፡1–19 ለእያንዳንዱ ጥቅስ ቢያንስ አንድ እውነት መፃፍ ትችሉ ይሆናል። ለመጀመር ያህል አንዳንድ ሀሳቦች ቀርበውላችሃል፡

ቁጥር 1ክህነት “የእግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት” ተብሎም ተጠርቷል (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፡1–4 ይመልከቱ)።

ቁጥር 2እግዚአብሔር ሰዎች ልጁን ለቤዛነት እንዲመለከቱ ለመርዳት ካህናትን ይሾማል።

ሌላ ምን ታገኛላችሁ? እነዚህን እውነቶች ስታሰላስሉ ስለ ክህነት ምን ይሰማችኋል?

የክህነት ስርዓቶች “ልጁን ለቤዛነት እንድትጠባበቁት” እንዲረዳችሁ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ? (ቁጥር 2፤ በተጨማሪም ቁጥር 16ን ይመልከቱ)። እንደ ጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ፣ ቅዱስ ቁርባን፣ ለጥሪ መለየት፣ የመጽናናት ወይም የፈውስ በረከት፣ የፓትርያሪክ በረከት እና የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ያሉ የተቀበላችሁትን ስነስርዓቶች ዝርዝር ልታወጡ ትችላላችሁ። እንደዚህ ባሉ ስነስርዓቶች ላይ ያላችሁን ተሞክሮ አስቡ። የተያያዙ ምልክቶችን እና የተሰማችሁን መንፈስ ግምት ውስጥ አስገቡ። እነዚህ ስርዓቶች እናንተን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛነት እንዴት ነው የሚጠቁመው?

አንዳንድ ሰዎች ስነስርዓቶች—እና እነሱን ለማከናወን የክህነት ስልጣን—አስፈላጊ አይደለም ብለው በስህተት ያምናሉ። ለዚህ ሀሳብ ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ? ሃሳባችሁን ሊያሳውቁ የሚችሉ ሁለት የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች እነሆ፡ አንዱን በመምረጥ ወደ እናንተ የሚመጡትን መልሶች ጻፉ፡ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “መንፈሳዊ ውድ ሀብቶች [Spiritual Treasures]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019፣ 76–79፤ ዴል ጂ. ሬንሉንድ፣ “ ክህነት እና የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ሃይል [The Priesthood and the Savior’s Atoning Power]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 64–67

በተጨማሪምትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፡19–22፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ቃል ኪዳን”፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ይመልከቱ።

ምስል
ወጣቶች በቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ አጠገብ

የክህነት ስነስርዓቶች ኢየሱስ ክርስቶስን ለቤዛነት እንድንመለከት ይረዱናል።

አልማ 13

ጌታ ወደ እረፍቱ እንድገባ ይጋብዘኛል።

“ወደ ጌታ ዕረፍት [እንድንገባ]” (አልማ 13፡16) የተደረገው ግብዣ ብዙ ጊዜ በአልማ 13 ተደግሟል። ምናልባት “እረፍት” የሚለው ቃል የሚገኝበትን እያንዳንዱን ጥቅስ በመፈለግ “የጌታ እረፍት” ምን ማለት እንደሆነ ምን እንደሚያስተምር ማሰብ ትችሉ ይሆናል። ከሥጋዊ እረፍት የሚለየው እንዴት ነው? እንዴትስ እናገኘዋለን?

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዓለምን አሸንፉና እረፍትን አግኙ [Overcome the World and Find Rest]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 95–98 “ወደ ኢየሱስ ኑመዝሙሮች፣ ቁ. 117 ይመልከቱ።

አልማ 14

በመከራ ጊዜ በጌታ መታመን አለብን።

ብዙዎች እንደሚያስቡት በጽድቅ ለመኖር በሚጥሩ ሰዎች ላይ ለምን አስከፊ ነገሮች እንደሚደርሱ ታስቡ ይሆናል። ለዚህ አስቸጋሪ ጥያቄ በሙሉ መልሶችን በአልማ 14 ላታገኙ ይችላሉ፣ ነገር ግን አልማ እና አሙሌቅ ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ከሰጡበት መንገድ ብዙ የምትማሩት ነገር አለ። አንዳንድ ጊዜ ጌታ ጻድቅ ሰዎች እንዲሰቃዩ ስለሚፈቅድበት ምክንያት ንግግራቸው እና ተግባራቸው ምን ያስተምራል? አስቸጋሪ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን አልማ እና አሙሌቅ ምን ምክር ሊሰጡን ይችላሉ?

በተጨማሪም ሮሜ 8፡35–39 1 ጴጥሮስ 4፡12–14 ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፡5–9፤ ዴል ጂ. ሬንሉንድ፣ “Infuriating Unfairness”፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 41–45 ይመልከቱ።

“ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ።” የማስተማር አጋጣሚዎች በፍጥነት ያልፋሉ፣ ስለዚህ ሲመጡ ተጠቀሙባቸው። በአለም ላይ ያለ አሳዛኝ ክስተት፣ ለምሳሌ፣ ጌታ ለምን አንዳንድ ጊዜ ንፁሃን እንዲሰቃዩ እንደሚፈቅድ ከአልማ 14 መመሪያዎችን ማካፈያ እድል ሊሆን ይችላል።

አልማ 15፡16፣ 18

ደቀመዝሙርነት መስዋዕትነትን ይጠይቃል።

አሙሌቅ ወንጌልን ለመቀበል የተዋቸውን ነገሮች መዘርዘር ሊያስደስት ይችላል (አልማ 10፡4–515፡16ን ይመልከቱ) እናም ካገኘው ነገር ዝርዝር ጋር አወዳድሩ (አልማ 15:1816:13–1534:8 ይመልከቱ)። ይበልጥ ታማኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ምን ለመሠዋት ፈቃደኛ ናችሁ?

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶችን እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

አልማ 13፡1–2, 16

የክህነት ኃይል ወደ ክርስቶስ እንድቀርብ ይረዳኛል።

  • ልጆቻችሁ የክህነት ሃይል ወደ ክርስቶስ እንዴት እንደሚጠቁመን እንዲያዩ መርጃ አንዱ መንገድ የክህነት ሃይል ጥቅም ላይ የሚውልባቸውን መንገዶች ምስሎችን በማሳየት ነው (የወንጌል ጥበብ መጽሐፍቁጥር 103–110 ይመልከቱ)። ልጆቻችሁ ኢየሱስ ኃይሉን የተጠቀመባቸውን መንገዶች እንድታስቡ ሊረዱ ይችላሉ (ለምሳሌ፣ ማቴዎስ 26፡26–28ማርቆስ 5፡22–24፣ 35–43፤ የወንጌል ጥበብ መጽሐፍ፣ ቁጥር 38–41ን ይመልከቱ)። ከዚያም አልማ 13፡2ን አንድ ላይ ማንበብ እና የክህነት ሃይል እንዴት “[የእግዚአብሔርን] ልጅ እንድንጠባበቅ” እና እርሱን እንድንመስል እንደሚረዳን ማውራት ትችላላችሁ።

    ምስል
    ጥምቀት
    ምስል
    ኢየሱስ ሃዋርያትን ሲሾም
  • እግዚአብሔር ለምን የክህነት ሥርዓቶችን ሰጠን? በአልማ 13፡16 ላይ ልጆቻችሁ መልስ እንዲያገኙ እርዷቸው። ስርዐት ምን እንደሆነ ለማወቅ እርዳታ ከፈለጋችሁ፣ በጠቅላላ መመሪያ መጽሃፍ18.1 እና 18.2 ውስጥ ዝርዝሮች አሉ። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ እነዚህን ስነስርዓቶች ስለተቀበላችሁበት አጋጣሚ ማውራት ትችላላችሁ። “የኃጢአታችንን ስርየትን [ከኢየሱስ ክርስቶስ] እንድንጠባበቅ” የሚረዱን እንዴት ነው? እንደ “እኔ ስጠመቅ” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 103) ያለ መዝሙር ልጆቻችሁ ለክህነት ሥርዓቶች አመስጋኝ የሚሆኑበትን ሌሎች ምክንያቶች እንዲያስቡ ይረዳቸዋል።

አልማ 13፡10–12

ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያነጻኝ ይችላል።

  • እነዚህን ጥቅሶች አንድ ላይ ካነበባችሁ በኋላ የሚያስተምሩትን ልጆቻችሁ በዓይነ ህሊናቸው እንዲያዩ ለመርዳት የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ። ምናልባት የሆነ ነገር አንድ ላይ ማጠብ ትችላላችሁ። በቆሸሽን ጊዜ ምን ይሰማናል? እንደገና ንፁህ ስንሆንስ? እነዚህ ስሜቶች ኃጢአት ስንሠራ እና ከዚያም ንስሐ ስንገባ እናም በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ንፁህ ስንሆን ከሚሰማን ጋር እንዴት ይመሳሰላሉ?

አልማ 14፡18–29

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ሲኖረኝ የሰማይ አባት ያበረታኛል።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ እናንተ ወይም ልጆቻችሁ በአልማ 14፡18–29 ውስጥ ያለውን ታሪክ እንድትናገሩ ሊረዳችሁ ይችላል (“ምዕራፍ 22፡ የአልማ ምስዮን ለአሞኒሃ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 58–63 ተመልከቱ)። አልማ እና አሙሌቅ “በክርስቶስ [ባላቸው እምነት]” (አልማ 14፡26) ብርታት እንደተሰጣቸው አጽንኦት ስጡ። በተጨማሪም እግዚአብሄር “[እንደ እምነታችሁ]” ብርታትን ስለሰጣችሁ ጊዜ መናገር ትችላላችሁ። እንደ አልማ እና አሙሌቅ እንዴት ታማኝ መሆን እንችላለን?

አልማ 15፡3–12

ኢየሱስ ክርስቶስ ልብን መለወጥ ይችላል።

  • የዚኤዝሮም ልብ በኢየሱስ ክርስቶስ መለወጥ የሚያበረታ ነው። ከልጆቻችሁ ጋር ባለፈው ሳምንት ስለ ዚኤዝሮም የተማሩትን ለመከለስ አስቡ። ከዚያም እሱ እንዴት እንደተለወጠ ለማወቅ አልማ 15፡3–12ን አብራችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። ስለ ጌታ ኃይል ከዚኤዝሮም ተሞክሮ ምን እንማራለን? (“ዚኤዝሮም ተፈወሰ እናም ተጠመቀ” [ቪዲዮ]፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት ይመልከቱ)።

ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ምስል
አልማ እና አሙሌቅ በእስር ቤት

አልማ እና አሙሌቅ በእስር ቤት፣ በጋሪ ኤል.ካፕ