ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 1–7፦ “በእጆቼ መሳሪያ አደርጋችኋለሁ።” አልማ 17–22


“ሐምሌ 1–7፦ ‘በእጆቼ መሳሪያ አደርጋችኋለሁ።’ አልማ 17–22፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023)

“ሐምሌ 1–7። አልማ 17–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ምስል
አሞን ከንጉሥ ላሞኒ ጋር ሲነጋገር

አሞን እና ንጉስ ላሞኒ፣ በስኮት ኤም. ስኖው

ሐምሌ 1–7፦ “በእጆቼ መሳሪያ አደርጋችኋለሁ።”

አልማ 17–22

ሰዎች ወንጌልን ላለማካፈል ሊሰጧቸው የሚችሏቸውን ሁሉንም ምክንያቶች አስቡ፦“በቂ እውቀት የለኝም” ወይንም “ፍላጎት እንዳላቸው እርግጠኛ አይደለሁም” ወይንም “አይቀበሉኝም ብዬ እሰጋለሁ።” ምናልባት አንዳንድ ጊዜ ራሳችሁን ተመሳሳይ ነገሮችን እያሰባችሁ ልታገኙ ትችላላችሁ። ኔፋውያን ወንጌልን ለላማናውያን ላለማካፈል ተጨማሪ ምክንያት ነበራቸው፦“ ዱር፣ ልበ ጠጣሮችና፣ አስፈሪ፤ ኔፋውያንን በመግደል የሚደሰቱ [ነበሩ]” (አልማ 17፥14፤ በተጨማሪም አልማ 26፥23–25 ይመልከቱ)። ነገር ግን የሞዛያ ልጆች ወንጌልን ለማካፈል የግድ የሚላቸው ከዚህም ጠንከር ያለ ምክንያት ነበራቸው፦“ደህንነት ለሁሉም ፍጡር መታወጀ እንደሚገባው ፍላጎት ነበራቸው የማንም የሰው ነፍስ መጥፋቱን ሊቀበሉት አልቻሉምና” (ሞዛያ 28፥3)። አሞንን እና ጓደኞቹን ያነሳሳቸው ይህ ፍቅር እናንተንም ወንጌልን ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለጓደኞቻችሁ እና ለምታወቋቸው ሰዎች—ሊቀበሉ የሚችሉ ለማይመስሉ እንኳን እንድታካፍሉ ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 17፥1–4

ቀላል ዘላቂ የሆኑ ለክርስቶስ የመሰጠት ተግባራት ሃይሉን እንድቀበል ይረዱኛል።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት እና ቁርጠኝነት ጠንካራ ማድረግ ስለምትችሉበት መንገድ ከአልማ 17፥1–4 ምን ትማራላችሁ? የሞዛያ ልጆች ምን አደረጉ ጌታስ እንዴት ባረካቸው?

አልማ 17፥22 ውስጥ ስለሞዛያ ልጆች ተርሞክሮዎች ሰታነቡ መንፈሳዊ ዝግጅታቸው ለላማናውያን በሰጡት አገልግሎት ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ አስተውሉ (ለምሳሌ አልማ 18፥10–18፣ 34–3620፥2–522፥12–16 ይመልከቱ)። የእነርሱን ምሳሌ ለመከተል ምን ለማድረግ የመነሳሳት ሥሜት ይሰማችኋል?

አልማ 17፥6–1219፥16–36

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
በእግዚአብሄር እጆች ውስጥ መሳሪያ መሆን እችላለሁ።

በቅዱሳት መጻህፍት የምናነባቸው የመለወጥ ዘገባዎች ቅፅበታዊ ናቸው ነገር ግን በዋነኝት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስላላቸው እምነት ለመናገር እና ለማጋራት ድፍረት ስለነበራቸው ግለሰቦች እናገኛለን። በዚህ ሳምንት ስለአቢሽ እና ስለሞዛያ ልጆች ስታነቡ ይህን አስቡ።

በእግዚአብሄር እጆች ውስጥ መሳሪያ መሆን ምን ማለት ይመስላችኋል? በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ የምትጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ማሰብ ሊረዳችሁ ይችላል። በአልማ 17፥6–12 ውስጥ የሞዛያ ልጆች በእግዚአብሄር እጆች ውስጥ መሳሪያ ለመሆን ይችሉ ዘንድ ምን እንዳደረጉ ፈልጉ። ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ለመርዳት ይበልጥ ውጤታማ መሳሪያዎች መሆን የምትችሉት እንዴት ነው?

አልማ 19፥16–36 ውስጥ ስለአቢሽ ምን ያስደንቃችኋል? ሌሎች በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲገነቡ ስለመርዳተ ከእርሷ ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፣ ሰዎች “በእግዚአብሄር ሃይል እንዲያምኑ” ምን ማድረግ እንደሚረዳ ይሰማችኋል? (አልማ 19፥17).

የአቢሽን ተሞክሮዎች ሽማግሌ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ፣ በ“የሚስዮናዊነት ሥራ፤ በልባችሁ ያለውን ማካፈል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 15–18 ውስጥ ካስተማሯቸው መርሆዎች ጋር ልታነጻጽሩም ትችላላችሁ። አቢሽ ሽማግሌ ኡክዶርፍ ላስቀመጧቸው “አምስት ቀላል ጥቆማዎች” ምሳሌ የሆነችው እንዴት ነው? ስለኢየሱስ ክርስቶስ ልትናገሯቸው የምትችሏቸውን አንዳንድ ነገሮች ለመጻፍ ሞክሩ። ለምሳሌ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ …” ወይም “ አዳኙ… ይረዳኛል”

በተጨማሪም የወንጌል አርዕስቶች፣ “Ministering as the Savior Does፣” ወንጌል ቤተመፃሕፍት፤ “Brightly Beams Our Father’s Mercy,” መዝሙር፣ ቁ. 335; “Come and See,” “Come and Help,” “Come and Belong” (ቪዲዮዎች)፣ ወንጌል ቤተመፃሕፍት ይመልከቱ።

በተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን አጋሩ። ሰዎች እየተማሩት ካለው ነገር ጋር የተያያዘን አንድ ነገር ማየት እና መንካት ሲችሉ ያንን ነገር ረዘም ላለ ጊዜ የማስታወስ እድላቸው ስፊ ነው። ለምሳሌ ስለ አልማ 17፥11 የምታስተምሩ ከሆነ በእግዚአብሄር እጅ መሳሪያ ስለመሆን ውይይትን ለማነሳሳት እንዲረዳ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ወይም የመጻፊያ መሳሪያዎችን ማሳየትን አስቡ።

አልማ 17–19

ለሌሎች ፍቅር በናሳይበት ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ ልንረዳቸው እንችላለን።

አልማ 17–19 ውስጥ አሞን ለላማናውያን የነበረው ፍቅር የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል ጥረቶቹን እንዴት እንዳነሳሳ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ፈልጉ። ከእርሱ ምሳሌ ወንጌልን ስለማካፈል ምን ሌላ እውነቶች ትማራላችሁ?

በተጨማሪም “Ammon Serves and Teaches King Lamoni” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረ።

ምስል
አሞን የንጉሱን በጎች እያዳነ

ሚነርቫ ቴከርት (1888–1976)እ.አ.አ፣ አሞን የንጉሱን በጎች አዳነ፣ 1949–1951)እ.አ.አ፣ oil on masonite፣ 35 15/16 × 48 ኢንች። ብሪግም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የአርት ሙዚየም 1969 (እ.አ.አ)።

አልማ 19፥36

ጌታ ንስሐ እንድገባ ይረዳኛል።

የላሞኒን እና የህዝቦቹን መለወጥ ከዘረዘረ በኋላ ሞርሞን ዘገባውን ስለአኢየሱስ ክርስቶስ ምልከታ አሳጥሮ ጻፈ። አልማ 19:36 ስለጌታ ባህርይ ምን ያስተምራችኋል? በአልማ 19፥16-36 ላይ ያለው ዘግባ ስለ አዳኙ ምን ያስተምራችኋል? የጌታ እጅ ወደእናንተ እንደተዘረጋ የተሰማችሁ መቼ ነው?

አልማ 20፥2322፥15–18

እግዚአብሄርን ማወቅ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት የሚከፈልለት ነገር ነው።

የላሞኒ አባት ህይወቱን ለማዳን ለመተው ፈልጎ የነበረውን ( አልማ 20፥23 ይመልከቱ) በኋላ ላይ የወንጌልን ደስታ ለማግኘት እና እግዚአብሄርን ለማወቅ ( አልማ 22፥15፣ 18 ይመልከቱ) ሲል ለመተው ፈቃደኛ ከሆነው ነገር ጋር አነጻጽሩ። እግዚአብሄርን ይበልጥ በደምብ ለማወቅ ትችሉ ዘንድ ምን መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሆናችሁ አሰላስሉ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ሳምንት የሊያሆና ዕትም እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄትን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 17፥2–3

ቅዱሳት መጻህፍትን ሳነብ፣ ስጸልይ እና ስጾም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ምስክርነት ያድጋል።

  • የሞዛያ ልጆች ምሳሌ ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን ምስክርነት ለመሳደግ የሚረዳቸው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ በአልማ 17፥2–3 ውስጥ የሞዛያ ልጆች መንፈሳዊ ጥንካሬያቸውን ለማዳበር ያደረጉትን እንዲያገኙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ሥዕሎችን ሊስሉ ወይም እነዚህን ነገሮች የሚወክሉ ነገሮችን ሊፈልጉ ይችላሉ። ስለአዳኙ ያላቸውን ምስክርነት ለማጠናከር ምን እንደሚያደርጉ እንዲያቅዱ እርዷቸው።

አልማ 17–19

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል እችላለሁ።

  • የሞዛያ ልጆች እንደነበሩት በእግዚአብሄር እጅ መሳሪያ ስለመሆን ለመማር እናንተ እና ልጆቻችሁ አንድን መሳሪያ ልትመለከቱ እና ለምን አገልግሎት እንደሚውል ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ከዚያም አልማ 17፥11 ልታነቡ እንዲሁም ሰዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲማሩ በመርዳት ረገድ የሰማይ አባት መሳሪያዎች መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ አሞን ለንጉስ ላሞኒ ያስተማራቸውን እውነቶች የሚወክሉ ስዕሎች አሉት። ልጆቻችሁ እነዚህን እውነቶች በአልማ 18፥24-40 ውስጥ እንዲያገኙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ሚስዮናውያን እንደሆኑ ማስመሰል እና ስለእነዚህ እውነቶች የሚያውቁትን ሊያካፍሉ ይችላሉ።

  • ከልጆቻችሁ ጋር ስለአቢሽ (አልማ 19፥16–20፣ 28–29 ይመልከቱ) ካነበባችሁ በኋላ፣ በአንድ ቦታ በመሮጥ፣ በሮችን በማንኳኳትና በአልማ 19፥1–17 ውስጥ የሆነውን በመናገር አቢሽ እንደሆኑ ማስመሰል ይችላሉ። እንዴት እንደአቢሽ መሆን እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ስለወንጌሉ የምናውቀውን ማካፈል እንችላለን? ልጆቻችሁ ለአንድ ሰው ወንጌልን ሲያካፍሉ የሚያሳይን የራሳቸውን ምስል መሳል ወይም ወንጌል ስለማካፈል የሚያወሳ መዝሙር ለምሳሌ “Called to Serve” (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣ 174–75) መዘመር ይችላሉ።

አልማ 17፥21–2520፥8–2722፥1–3

ለእነርሱ ያለኝን ፍቅር በማሳየት ሌሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ መርዳት እችላለሁ።

  • በመጀመሪያ ንጉስ ላሞኒ እና አባቱ ወንጌልን በተመለከተ ግትር ልብ ነበራቸው። በኋላ ግን ተቃውሟቸው ቀነሰ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ይህ እንዴት ሆነ? ከልጆቻችሁ ጋር የአሞንን ተሞክሮዎች ስትከልሱ ለዚህ ጥያቄ መልሶችን እንዲያገኙ እርዷቸው። “Chapter 23: Ammon: A Great Servant” እና “Chapter 24: Ammon Meets King Lamoni’s Father” (የመፅሃፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 64–68፣ 69–70) መተወንም ይችላሉ። ወይም ምናልባት ልጆቻችሁ የታሪኩን የተለያዩ ክፍሎች ሥዕል ለመሳል እንዲሁም ሥዕሎቹን ተጠቅመው ታሪኮቹን ለመተረክ ይፈልጉ ይሆናል። ላሞኒ እና አባቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ ለመርዳት አሞን ምን አደረገ? ( አልማ 17፥21–2520፥8–2722፥1–3 ይመልከቱ)።

  • ምናልባት አናንተና ልጆቻችሁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ ያስፈልገዋል የምትሉትን ሰው ልታስቡ ትችላላችሁ። አሞን ለላሞኒ እና ለአባቱ እንዳደረገው ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑበትን መንገድ እንዲያስቡ እንዲሁም ለዚያ ሰው ፍቅር እንዲያሳዩ እርዷቸው።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
የአቢሽ ምስል

የአቢሽ ምስል፣ በዳይሊን ማርሽ