ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 22–28፦ “ዘሩን በልባችሁ ትከሉ።” አልማ 32–35


“ሐምሌ 22–28፦ ‘ዘሩን በልባችሁ ትከሉ።’ አልማ 32-35፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

“ሐምሌ 22–28። አልማ 32-35፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023[እ.አ.አ])

ምስል
በልጅ እጅ ላይ ያለ ዘር

ሐምሌ 22–28፦ “ዘሩን በልባችሁ ትከሉ።”

አልማ 32–35

ለዞራማውያን ጸሎት ሁሉም ሊያዩ በሚችሉበት ቦታ መቆምን እና ትርጉም የለሽ ውስጣዊ ስሜቶቻቸውን የማይገልፁ ቃላትን መደጋገምን ያካትት ነበር። ዞራማውያን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት አልነበራቸውም—መኖሩን እንኳን ክደው ነበር— እንዲሁም ድሆችን ያሳድዱ ነበር ( አልማ 31:9–25 ይመልከቱ)። በተቃራኒው፣ አልማ እና አሙሌቅ ጸሎት ህዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ ከሚሆነው ይልቅ በውስጣችን ከሚሰማን ነገር ጋር የበለጠ ግንኙነት እንዳለው አስተምረዋል። ለተቸገሩ ሰዎች ርኅራኄ ካላሳየን ጸሎታችን “ከንቱ ነው እናም ለእኛ የሚጠቅ[መን] ምንም የለም” (አልማ 34:28)። ከሁሉም በላይ የምንጸልየው “በመጨረሻ መስዋዕትነ[ቱ]” አማካኝነት ቤዛ በሚሠጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ስላለን ነው (አልማ 34:10)። አልማ እንዲህ ያለው እምነት የሚጀምረው በትህትና እና “ለማመን በመፈለግ” ነው ሲል ያብራራል (አልማ 32:27)። በጊዜ ሂደት፣ ያለማቋረጥ በመመገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል “ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያድግ ዛፍ” እስኪሆን ድረስ በልባችን ውስጥ ስር ይሰዳል (አልማ 32:41)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

አልማ 32፥17–43

ቃሉን በልቤ ውስጥ በመትከል እና በመመገብ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን እምነት እለማመዳለሁ።

አልማ 32፥17–43 ስታነቡ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን መለማመድን እንድታውቁ የሚረዷችሁን ቃላት እና ሃረጋት አስተውሉ። እምነት ምን እንደሆነ እና እንዳልሆነ ምን ትማራላችሁ?

አልማ 32 የሚጠናበት ሌላው መንገድ የዘርን የተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች የሚወክሉ ሥዕሎችን በመሳል ነው። ከዚያም እያንዳንዱን ሥዕል የእግዚአብሔርን ቃል በልባችሁ ውስጥ ለመትከል እና ለመንከባከብ በሚረዷችሁ ከአልማ 32:28–43 ውስጥ በተወሰዱ ቃላት ሰይሙ።

በተጨማሪም ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመንም ተራራን ያነቃንቃል፣፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 101-4 ይመልከቱ።

አልማ 32፥26–43

እኔ ራሴ ማወቅ እችላለሁ።

ስለአልማ የክርስቶስ ምስክርነት ገና እርግጠኛ ላልሆኑት ለዞራማውያን አልማ “ሙከራ” የማድረግን ሃሳብ ሰጥቷል ( አልማ 32:26 ይመልከቱ)። ሙከራዎች ፍላጎትን፣ ጉጉትን፣ ተግባርን እና ቢያንስ ትንሽ እምነትን ይፈልጋሉ—ከዚያም ወደ አስደናቂ ግኝቶች ይመራሉ! ስላያችኋቸው ወይም ስለተሳተፋችሁባቸው ሙከራዎች አስቡ። በአልማ 32፥26-36 መሰረት በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ወደመኖር የሚመራን ምን ዓይነት ሙከራ ነው?

የእግዚአብሔርን ቃል “ሞክራችሁ” “ቃሉ መልካም እንደሆነ” ያወቃችሁት እንዴት ነው? አልማ 32፥28

አልማ 33፧2–1134፧17–29

በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ እግዚአብሄርን በፀሎት አመልከዋለሁ።

አልማ እና አሙሌቅ ስለ አምልኮ እና ስለ ጸሎት የሰጡት ምክር ዞራማውያን የነበሩባቸውን የተለዩ የግንዛቤ እጥረቶች ማረምን ያለመ ነበር። እነርሱን መዘርዘርን አስቡ (አልማ 31፥13-23 ይመልከቱ)። ከዚያ ዝርዝር በኋላ በአልማ 33:2–11 እና 34:17–29 ውስጥ ስለ ፀሎት የሰፈሩትን እውነቶች መዘርዘር ትችላላችሁ። ከእነዚህ ጥቅሶች የተማራችኋቸው ነገሮች በምትጸልዩበትና በምታመልኩበት መንገድ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

እንዲሁም ስለ እምነት ከሚናገር መዝሙር ግንዛቤን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ “Sweet Hour of Prayer” (መዝሙር፣ 142)።

አልማ 34፥9–16

ምስል
seminary icon
ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሃጢያት ክፍያው ያስፈልገኛል።

በአልማ 34:9–14 ውስጥ አሙሌቅ የአዳኙን የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት ለመግለፅ መጨረሻ የሌለው እና ዘለአለማዊ የሚሉትን ቃላት ምን ያህል ጊዜ እንደተጠቀመባቸው አስተውሉ ። የአዳኙን የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት መጨረሻ የሌለው እና ዘለአለማዊ መሆኑን ማወቁ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በተጭማሪም በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ የሚገልጹ ቃላትን እና ሀረጎችን ፈልጉ፦ ዕብራውያን 10:102 ኔፊ 9:21ሞዛያ 3:13

የኢየሱስ የማዳን ኃይል መጨረሻ የሌለው እና ዘለአለማዊ መሆኑን እያወቅንም እንኳን፣ አንዳንድ ጊዜ ለእኛ—ወይንም ሃጢያትን ላደረገብን ሰው ስለመሥራቱ ልንጠራጠር እንችላለን። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር በአንድ ወቅት ስለ ሰዎች ሲናገሩ “በአዳኙ ላይ እምነት ያላቸው የሚመስሉ፣ ነገር ግን ቃል የገባቸው በረከቶች ለእነሱም እንደሆነ ስለማያምኑ” ሰዎች ተናግረዋል (“If Ye Had Known Me፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2016 (እ.አ.አ) 104))። የአዳኙን ሙሉ ኃይል ከመቀበል ምን ያግደናል? የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት መጨረሻ የሌለው እና ዘለአለማዊ መሆኑን እንዴት ልታውቁ እንደምትችሉ አሰላስሉ?

የአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ምን ያህል እንደሚያስፈልጋችሁ ለማሰላሰል በየቀኑ የሚያስፈልጋችሁን አንድ ነገር ማሰብ ሊረዳችሁ ይችላል። እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፣ “ያለዚህ ሕይወቴ ምን ይመስል ነበር?” ከዚያም አልማ 34፥9-16 ስታጠኑ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወታችሁ ምን ይመስል እንደነበር አሰላስሉ። በ2 ኔፊ 31፥21ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። አልማ 34:9–10 በአንድ አረፍተ ነገር እንዴት ታጠቃልሉታላችሁ?

በተጨማሪም ሚካአኤል፤ ጆን ዩ. ቴ፣ “Our Personal Savior,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ) 99–101፤ የወንጌል አርዕስቶች፣ “Atonement of Jesus Christ,” ወንጌል ላይብረሪ፤ “Reclaimed” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ።

አልማ 34፥30–41

“የመዳን ጊዜና ቀን አሁን ነው።”

በማራቶን ወይም በሙዚቃ ዝግጅት ላይ መካፈል እንደምትፈልጉ አስቡ። ዝግጅት ለማድረግ ፕሮግራሙ እስከሚካሄድበት ቀን ድረስ ብትጠብቁ ምን ይሆናል? ይህ ምሳሌ በአልማ 34:32–35 ውስጥ ካለው ከአሙሌቅ ማስጠንቀቂያ ጋር የሚገናኘው እንዴት ነው? ንስሐ መግባትን እና መለወጥን ማዘግየት ምን አደጋ አለው?

ቁጠር 31 በጣም ለረጅም ጊዜ እንደዘገዩ እንዲሁም ንስሃ ለመግባት ሰዓቱ በጣም አልፏል ብለው ሊያስቡ ለሚችሉ ሰዎች መልዕክት አለው። ያ መልዕክት ምንድነው ትላላችሁ?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶችን ዕትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

አልማ 32፥1–16

ጌታ ትሁት መሆንን ስመርጥ ሊያስተምረኝ ይችላል።

  • አልማ እና አሙሌቅ ትሁት የነበሩትን ዞራማውያንን በማስተማር ውጤታማ ሆነው ነበር። ትሁት መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ልጆቻችሁ ትሁት የሚለውን ቃል በቅዱሳን ጸሁፎች መመሪያ ውስጥ እንዲያገኙ እርዷቸው። በአልማ 32፥13–16 ውስጥ ስለእነዚህ ቃላት ትርጉም ምን ሌሎች ፍንጮችን ለማግኘት እንችላለን? ልጆቻችሁ “ በማደርግበት ጊዜ ትሁት እየሆንኩኝ ነው” እንደሚሉ ያሉ ዓረፍተ ነገሮችን እንዲያሟሉ ጋብዟቸው።

አልማ 32፥28–43

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን ምስክርነት በምመግበው ጊዜ ያድጋል።

  • ዘሮች፣ ዛፎች እና ፍራፍሬዎች ልጆች እንደ እምነት እና ምስክርነት ያሉ ረቂቅ መርሆዎችን እንዲገነዘቡ ለማገዝ የሚችሉ የተለመዱ ነገሮች ናቸው። አልማ 32:28በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ ዘር ይያዙ። ከዚያም የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ማሳደግ ዘርን እንደ መትከል እና እንደ መመገብ የሆነበትን መንገድ እንድታስቡ እንዲረዷችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ( “Chapter 29: Alma Teaches about Faith and the Word of God,” የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 81 ይመልከቱ)። ምናልባት ዘራችሁን ልትዘሩ እና ዘሩ—ወይም ምስክርነት—እንዲያድግ ለመርዳት ምን እንደሚያስፈልግ ለመነጋገር ትችላላችሁ።

  • የዛፍ ምስል ከዚህ መዘርዝር ጋር ቀርቧል በአልማ 32:28–43 ውስጥ ያለውን የአልማን ቃላት ምስሉን በመጠቀም ለማስረዳት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። ወይንም በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ተክሎችን ፍለጋ የእግር ጉዞ ማድረግ እና በማደግ ላይ ያለን ተክል ከምሥክርነታችን ጋር ከሚያነጻጽሩት ከአልማ 32 ውስጥ ጥቅሶችን ማንበብ ትችላላችሁ። ወይንም ልጆቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታቸው ያድግ ዘንድ ማድረግ ስለሚችሉት አንድ ነገር ባሰቡ ቁጥር በሰሌዳው ላይ ዛፍ ሊስሉ እና ቅጠል ወይም ፍሬ ሊያክሉበት ይችሉ ይሆናል።

  • ልጆቻችሁ ዘርን (በእግዚአብሔርን ቃል ይመሰላል) ወደ ድንጋይ (በኩሩ ልብ ይመሰላል) ውስጥ እንዲሁም ወደ ለስላሳ አፈር (በትሑት ልብ ይመሰላል) ውስጥ ለማስገባት እንዲሞክሩ ማድረግ ትችላላችሁ። አልማ 32፥27–28በጋራ አንብቡ። በልባችን ውስጥ ለእግዚአብሔር ቃል “ቦታ መስጠት” (ቁጥር 27) ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተነጋገሩ።

ሥዕሎችን ሣሉ። አንዳንድ ሰዎች እየተማሩ ስላሉት ነገር ስዕል ሲስሉ በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ ልጆቻችሁ በሚያጠኑበት ጊዜ ወደ ዛፍነት በማደግ ላይ ያለን ዘር መሳል ያስደስታቸው ይሆናል አልማ 32

አልማ 33፧2–1134፧17–27

ስለማንኛውም ነገር በማንኛውም ጊዜ ወደ የሰማይ አባት መጸለይ እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ (በአልማ 33:4–11 ውስጥ) ልንጸልይ የምንችልባቸውን ቦታዎች እንዲሁም (በአልማ 34:17–27) ውስጥ ልንጸልይባቸው የምንችላቸውን ነገሮች የሚገልጹ ሀረጎችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። ምናልባት በእነዚህ ቦታዎች ሲጸልዩ የሚያሳዩ የራሳቸውን ምስሎች ሊስሉ ይችላሉ። የሰማይ አባት ጸሎቶቻችሁን በሚሰማበት ጊዜ ስላላችሁ ልምድ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። እንዲሁም ስለ ፀሎት መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ “A Child’s Prayer” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 12–13)።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
በዛፍ ላይ ያለ ፍሬ

“እናም ስር እንዲያወጣ ዘንድ ቃሉን ለመንከባከብ ትጉ በመሆናችሁና፣ በታማኝነታችሁ እንዲሁም በትዕግስተኛነታችሁ፣ እነሆ፣ የተከበረውን፣ ፍሬ ከጊዜ በኋላ…ትቀጥፋላችሁ” (አልማ 32:42)።