ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 9-15፦ “ክርስቶስ ከፍ ያድርግህ።” ሞሮኒ 7–9


“ታህሳስ 9-15፦ ‘ክርስቶስ ከፍ ያድርግህ።’ ሞሮኒ 7–9,” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ታህሳስ 9–15 (እ.አ.አ)። ሞሮኒ7–9”፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ሞሮኒ በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ ሲጽፍ

ሚነርቫ ቴከርት (1888–1976 እ.አ.አ)፣ ሞሮኒ የመጨረሻው ንጉሥ፣ 1949–1951 (እ.አ.አ)፣ oil on masonite፣ 34 3/4 × 48 ኢንች። ብሪግም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የአርት ሙዚየም 1969 (እ.አ.አ)።

ታህሳስ 9-15፦ “ክርስቶስ ከፍ ያድርግህ።”

ሞሮኒ 7–9

ሞሮኒ ዛሬ መፅሐፈ ሞርሞን በመባል የሚታወቀውን መዝገብ የራሱን የመደምደሚያ ሃሳቦች በማካተት ከመደምደሙ በፊት የአባቱን የሞርሞንን ሶስት መልእክቶች አካፍሏል፦“ሰላማዊ ክርስቶስ ተከታይ ለሆ[ኑ] ” (ሞሮኒ 7:3) የተፃፈ እና ለሞሮኒ ፅፏቸው የነበሩ ሁለት ደብዳቤዎች። ምናልባት ሞሮኒ እነዚህን መልዕክቶች በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያካተተው በእርሱ እና በእኛ ዘመን መካከል ያለውን ተመሳሳይነት አስቀድሞ ተመልክቶ ይሆን ይሆናል። እነዚህ ቃላት በተፃፉበት ጊዜ ኔፋውያን ከአዳኙ እየራቁ ነበር። ብዙዎቹ “እርስ በርሳቸውም የነበራቸውን ፍቅር አጥተ[ው]” እና “መልካም ከሆነው በስተቀር” በሁሉም ነገር ተደ[ስተው] [ነበር] (ሞሮኒ 9:5፣ 19)። ሞርሞን ግን ተስፋ ማለት በአለም ውስጥ ያሉትን ችግሮች ችላ ማለት ወይም ጥበብን የጎደለን መሆን ማለት እንዳልሆነ እያስተማረን አሁንም ተስፋ የሚያደርግበት ምክንያት ነበረው። ተስፋ ማለት ሃይላቸው ከእነዚህ ችግሮች በሚበልጠው እና ዘላለማዊ በሆነው በሰማያዊ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ነው። “መልካም የሆኑትን ሁሉ መያዝ” ማለት ነው (ሞሮኒ 7:19)። የኢየሱስ ክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ እና “ለክብሩ እናም ለዘለዓለማዊ ህይወት ያለውተስፋ ለዘለዓለም በአዕምሮ [ማኖር]” ማለት ነው (ሞሮኒ 9:25)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞሮኒ 7፥12–20

የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ትክክለኛውን ክስህተት እንዳውቅ ይረዳኛል።

“ከእግዚአብሄር የመጣ ይሁን ከራሴ ስሜት የመነጨ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” ወይንም “በዛሬው ጊዜ ይህን ያህል ብዙ ማታለል እያለ ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ነገር እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። በሞሮኒ 7 ውስጥ የሰፈረው የሞርሞን ቃላት እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ብዙ መርሆዎች ይሰጡናል። በተለይ በቁጥር 12–20 ውስጥ ፈልጓቸው። እነዚህን እውነቶች፣ የምታገኟቸውን መልእክቶች እና በዚህ ሳምንት የነበሯችሁን ተሞክሮዎች ለመገምገም ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ “Light, Light of Christ,” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Patterns of Light: Discerning Light” (ቪዲዮ) የወንጌል ላይብረሪ ላይ ይመልከቱ።

ሞሮኒ 10፥32–48

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት “መልካም የሆኑትን ሁሉ መያዝ” እችላለሁ።

ሞርሞን በተለይ ዛሬ በጣም አስፈላጊ የሚመስል “መልካም የሆኑትን ሁሉ መያዝ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሚል ጥያቄ ጠይቋል። (ሞሮኒ 7፥20)። ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማመን፣ ስለተስፋ እና ስለልግሥና አስተምሯል። ቁጥር 20–48 በምታነቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ባህሪ ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚመጣውን መልካም ነገር ለመፈለግ እና “ለመያዝ” የሚረዳበትን መንገድ ፈልጉ። እነዚህ ባህርያት ለአንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር አስፈላጊ የሆኑት ልምንድን ው?

በተጨማሪም “Mormon’s Teachings about Faith, Hope, and Charity [ሞርሞን ስለእምነት፣ ተስፋ እና ልግሥና ያስተማራቸው ትምህርቶች]”(ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

ሞሮኒ 7፥44–48

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
“ልግስና የኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ነው።”

ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት እና ተስፋ ወደ ልግስና እንደሚመራን ሃሳብ ሰጥቷል። ሆኖም ልግስና ምንድን ነው? ልግሥና … ብላችሁ ልትፅፉና ከዚያም ሞሮኒ 7:44–48፣ ዓረፍተ ነገሩን ሊያሟሉ የሚችሉ ቃላትን እና ሃረጎችን እየፈለጋችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ስትጨርሱ ልግሥና የሚለውን ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሚለው መተካትን አስቡ። ይህ ስለጌታ ምን ያስተምራችኋል? ኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅሩን ያሳየው እንዴት ነው? ከቅዱሳት መጻህፍት እና ከራሳችሁ ህይወት የተገኙ ምሳሌዎችን አስቡ።

ፕሬዚዳንት ዳሊን ኤች ኦክስ ሲሉ ሃሳብ ሰጥተዋል “ልግሥና በፍፁም የማይወድቅበት ምክንያት እና ልግሥና ከበጎ ተግባር ሳይቀር የሚበልጥበት ምክንያት …‘የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር’ [ሞሮኒ 7፥47] የሆነው ልግሥና ድርጊት ሳይሆን ሁኔታ ስለሆነ ነው … ልግሥና አንድ ሰው ሊላበሰው የሚችለው ነገር ነው “The Challenge to Become፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 2000 (እ.አ.አ)፣ 34። ይህንን ንግግር በአዕምሯችሁ ይዛችሁ የሽማግሌ ማሲሞ ዴ ፌኦን “Pure Love: The True Sign of Every True Disciple of Jesus Christ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ) 81–83) ልታነቡ ትችላላችሁ። ልግሥና በደቀ መዝሙርነታችሁ ላይ ተፅዕኖ ያደረገው እንዴት ነው? “ልግሥናን መያዝ” የምትችሉት እንዴት ነው? (ቁጥር 46)።

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 13:1–13ኤተር 12:33–34፤ “Love One Another,” መዝሙር፣ ቁ. 308፤ “Charity: An Example of the Believers” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ የወንጌል አርዕስቶች፣ “ልግሥና፣” ወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

በተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ተጠቀሙ። ምናልባት ባለ ሶስት እግር በርጩማን ማሰብ በእምነት፣ በተስፋ እና በልግሥና መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለመገንዘብ ሊረዳችሁ ይችላል (ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “The Infinite Power of Hope,” ሊያሆና፤ ሕዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 21–24 ይመልከቱ)።

ሞሮኒ 9፥3–5

ቁጣ ወደ ሃዘን እና ሥቃይ ያመራል።

ሞሮኒ 7፥44–48 ውስጥ ከሰፈረው የሞርሞን የፍቅር መልዕክት በተጨማሪ ለሞሮኒ የላከው የሞርሞን ሁለተኛው መልዕክትዛሬ ብዙዎችን ስለሚቸገሩበት ነገር ያካትታል—ስለቁጣ። በአልማ 9፥3-5 መሠረት የኔፋውያን ቁጣ ውጤቶች ምን ምን ነበሩ? ከቁጥር 3–5, 18–20, 23 ምን ማስጠንቀቂያዎችን መውሰድ እንችላለን?

በተጨማሪም ጎርደን ቢ.ሂንክሊ፣ “Slow to Anger፣” ሊያሆና ህዳር 2007 (እ.አ.አ)፣ 62-66 ይመልከቱ።

ሞሮኒ 5፥25–26

ሁኔታዬ ምንም ይሁን ምን በክርስቶስ ተስፋን ማግኘት እችላለሁ።

ሞርሞን አይቶ የነበረውን ክፋት ከገለጸ በኋላ ልጁ እንዳያዝን ነገረው። ስለሞርሞን የተስፋ መልዕክት ምን ያስደንቃችኋል? “ክርስቶስ ከፍ ያድር[ጋችሁ]” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? የትኞቹ የክርስቶስ ባህርያት እና መርሆዎች “በአዕምሯችሁ ይኖራሉ” እንዲሁም ተስፋ ይሰጧችኋል (ሞሮኒ 9፥26)።

ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ደስታ እና መንፈሳዊ ደህንነት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 81–84።

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መፅሄቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞሮኒ 7፥33።

በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ካለኝ እንዳደርግ የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ።

  • አንድ ሰው በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ አንድን ጠቃሚ ነገር ሲፈጽም የሚያሳዩ ጥቂት ሥዕሎችን አንድ ላይ መመልከትን አስቡ (ለምሳሌ፣ የወንጌል የአርት መፅሐፍ፣ ቁ. 197078፣ 81 ይመልከቱ)። በእነዚህ ምሳሌዎች ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ልዩነት ያመጣው እንዴት ነበር? ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሲኖረን ምን ማድረግ እንደምንችል እየፈለጋችሁ ሞሮኒ 7፥33 ልታነቡ ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ እናንተን በኃይል የባረከበትን ተሞክሮ አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉም ትችላላችሁ።

ሞሮኒ 7፧41

በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ተስፋን ሊሠጠኝ ይችላል።

  • ሞሮኒ 7፧41ን ለልጆቻችሁ በታነቡበት ጊዜ፣ ሞርሞን ተስፋ እንድርግ ብሎ የተናገራቸውን ነገሮች በሰሙ ቁጥር እጃቸውን ሊያነሱ ይችላሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ስለሚሰማችሁ ተስፋ ንገሯቸው።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በአንድ ነገር ምክንያት እየተቸገረ ያለን ሰው ማሰብም ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ተስፋ እንዲኖረው/ራት ሊያስታውሰው/ሳት የሚችልን ሥዕል ለዚያ ግለስብ ሊስሉ ይችሉ ይሆናል።

ሞሮኒ 7:40–419:25–26

በከባድ ፈተናዎች ውስጥ ሆኜም እንኳን በኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ ሊኖረኝ ይችላል።

  • በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን ተስፋ ለልጆቻችሁ ለማስተማር፣ አንድን ንፁህ /ግልፅ የሆነ መያዣ በውሃ ሞልታችሁ አንድ የሚንሳፈፍ እና አንድ የሚሰምጥ ሁለት ነገሮችን ወደ ውስጥ ክተቱ። ሞሮኒ 7:40–41 እና 9:25–26፣ አብራችሁ ስታነቡ ልጆቻችሁ ተስፋ ሊያደርግልን ስለሚችለው ነገር ሊፈልጉ ይችላሉ። ከዚያም የሚንሳፈፈውን ነገር በክርስቶስ ተስፋ ከሚያደርገው ግለስብ ጋር ሊያነፃፅሩ ይችላሉ። ከባድ ፈተናዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ “ከፍ [የሚያደርጉን]” እንዴት ነው? ልጆቻችሁ አዳኙን እና የእርሱን አበረታች ትምህርቶች “በአእምሮአቸው ለዘላለም” ማቆየት የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ እርዷቸው።

ሞሮኒ 7፥45-48።

“ልግስና የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ነው።”

  • እንደ “Love One Another” (የልጆች የመዝሙር መፅሀፍ፣ 136) ያለ ስለፍቅር የሚናገር መዝሙር መዘመር ስለልግስና ምንነት ወይይት ሊያስጀምር ይችላል። ሞሮኒ 7፥47ን ልታነቡ ወይም ባጭሩ ልታጠቃልሉ ትችላላችሁ እንዲሁም ልጆቻችሁ ለአንድ ሰው ፍቅርን ሲያሳዩ የሚያመለክቱ የራሳቸውን ምስሎች እንዲስሉ ጋብዟቸው። ሥዕላቸውን ኢየሱስ እንደወደደው ሌሎችን እንዲወዱ በሚያስታውሳቸው ቦታ ላይ እንዲያስቀምጡ ሃሳብ አቅርቡ።

  • ልጆቻችሁ በሕይወታቸው ውስጥ የክርስቶስን ፍቅር ንጹህ እንዲፈልጉ እና እንዲያዳብሩ ማነሳሳት የምትችሉት እንዴት ነው? ምናልባት ኢየሱስ ልግስና ያሳየባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ (ለምሳሌ ሉቃስ 23:34ዮሃንስ 8:1–11ኤተር 12:33–34)። ምሳሌውን መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

Portrait of Christ the Savior[የአዳኙ የክርስቶስ ሥዕል፣ በሄንሪች ሆፍማን