ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 23–29 (እ.አ.አ)፦“ህዝቡን ለማዳን ወደ ዓለም ይመጣል።” ገና


“ታህሳስ 23–29 (እ.አ.አ)፦‘ህዝቡን ለማዳንና ወደ ዓለም ይመጣል።’ ገና፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023)

“ታህሳስ 23–29 (እ.አ.አ)። ገና፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023)

ምስል
ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ህጻኑ ኢየሱስ በበረት ውስጥ

እነሆ የእግዚአብሄር በግ በዋልተር ሬን

ታህሳስ 23–29 (እ.አ.አ)፦“ህዝቡን ለማዳን ወደ ዓለም ይመጣል።”

ገና

ከኔፊ አንስቶ እስከ ሞሮኒ እያንዳንዱ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ በመጽሐፉ የርዕስ ገፅ ውስጥ ተጠቃሎ ለተቀመጠው የተቀደሰ ዓላማ ቁርጠኛ ነበር፦ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ [ሁሉንም ሰዎች] ማሳመን።” አንድ ነቢይ በቅድመ ምድር መንፈስ እንደነበረ አየው እንዲሁም ሌላው ምድራዊ አገልግሎቱን በራዕይ ተመለከተ። አንዱ የውልደቱን እና የሞቱን ምልክቶች ለመናገር ግንብ ላይ ቆመ እንዲሁም ሌላው በእጆቹ፣ በእግሮቹ እና በጎኑ የነበረውን ቁስሉነ እየነካ ከሞት ከተነሳው አካሉ ፊት ተንበረከከ። ሁሉም ይህን አስፈላጊ እውነት ያውቁ ነበር፦“በሚመጣው በአዳኙ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ካልሆነ በቀር የሰው ልጅ ሊድንበት የሚችልበት መንገድም ሆነ ዘዴ የለም፤ አዎን፣ ዓለምን ለማዳን [በሚመጣው] (ሔለማን 5:9)።

ስለዚህ በዚህ የገና ወቅት፣ በአለም ዙሪያ የሚገኙ አማኞች ልጁን በመላክ ያሳየውን የእግዚአብሄርን ደግነት እና ፍቅር ሲያከብሩ መፅሐፈ ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት እንዳጠናከረላችሁ አሰላስሉ። ስለ ውልደቱ በምታስቡበት ጊዜ ለምን እንደመጣ እና መምጣቱ እንዴት አድርጎ ህይወታችሁን እንደቀየረው አሰላስሉ። ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጣችሁን እውነተኛ የሆነውን ሥጦታ ይኸውም የገናን ደስታ ልታገኙ ትችላላችሁ።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ለመሆን ተወልዷል።

ገና ሲመጣ የአዳኙን የልደት ታሪክ ከአዲስ ኪዳን ውስጥ ማንበብ የተለመደ ነው፤ ነገር ግን በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥም የዚህን የተቀደሰ ክስተት ልብ የሚነኩ ትንቢቶችን ልታገኙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ ስለአዳኙ ውልደት እና አገልግሎት የሚናገሩ ትንቢቶች በ1 ኔፊ 11:13–36ሞዛያ 3:5–10፤ እና ሔለማን 14:1–13 ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህን ምንባቦች ስታነቡና ስለውልደቱ ምልክቶች ምሳሌነት ስታሰላስሉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አይነት ግንዛቤዎች ወደ እናንተ ይመጣሉ? የእነዚህ ነቢያት ምስክርነቶች ስለአኢየሱስ እና ስለአገልግሎቱ ያላችሁን ምስክርነት የሚያጠናክሩት እንዴት ነው?

ገና ሲመጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ትኩረት ለማድረግ የሚረዷችሁ ሌሎች ጥቆማዎች ቀረውላቹሃል፦

  • ከቀዳሚ አመራር የተሰጡ የቀድሞውን የገና አምልኮ መልዕክቶችን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ መመልከት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ? በ“Christmas Videos” ሥብሥብ ውስጥ ተመልከቷቸው። የገናን ደስታ ለማዳረስ እነዚህን መልዕክቶች እና ሙዚቃዎች ማካፈልን አስቡ።

  • እናንተ እና ቤተሰባችሁ ከ“Christmas Music” ወንጌል ላይብረሪ ሥብሥብ. የተመረጡትን በማዳመጥ ልትደሰቱ ትችላላችሁ።

  • እናንተ ወይም ቤተሰባችሁ የክርስቶስ መንፈስ እንዲሰማችሁ ገና ሲቃረብ ልታደርጓቸው የምትችሏቸውን ለምሳሌ አንድን ሰው እንደማገልገል ወይም የገና መዝሙሮችን አንድ ላይ እንደ መዘመር ያሉ አክቲቪቲዎችን ማቀድን አስቡ። ሐሳቦችን ለማግኘት LighttheWorld.org ይመልከቱ።

በተጨማሪም ማተዎስ 1፥18–252ሉቃስ 23 ኔፊ 1፥4–22፤ “Away in a Manger,” መዝሙር፣ ቁ. 206 ይመልከቱ.።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ ነው።

ገናን የምናከብርበት ዋነኛ ምክንያት የሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ነው። በዚያ መስዋዕት ምክንያት ከሞት እና ከሃጢያት ሊያድነን፣ በመከራ ሊያጽናናን እና “በእርሱ ፍፁማን [እንድንሆን]” ሊረዳን ይችላል (ሞሮኒ 10፥32)። አዳኙ ስላለው እናንተን የማዳን ኃይል በዚህ ዓመት ከመጽሐፈ ሞርሞን ምን ተማራችሁ? ጎልተው የሚታዩ ዘገባዎች ወይም ትምህርቶች አሉ? የሚከተሉት ምንባቦች ስለ አዳኙ የማዳን ተልዕኮ ምን እንደሚያስተምሯችሁ አስቡ: 2 ኔፊ 2:6; አልማ 7፥7–1311፥40፤ እና ሔለማን 5፥914፥16–17። ለእርሱ ያላችሁን አመስጋኝነት ለማሳየት ምን ለማድረግ ትነሳሳላችሁ?

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
መፅሐፈ ሞርሞን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ ሌላኛው ምስክርነት” የመጽሐፈ ሞርሞን ንዑስ ርእስ ከመሆን በላይ ነው። ከሚከተሉት ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ መፅሐፈ ሞርሞን ስለክርስቶስ ለመመስከር ስላለው ተልእኮ ምን እንደምትማሩ አስቡ፦1 ኔፊ 6፥419፥18፤ እና 2 ኔፊ 25፥23, 2633፥4፣ 10

በዚህ ዓመት መጽሐፈ ሞርሞንን ማጥናታችሁ እንዴት ወደ ክርስቶስ እንዳቀረባችሁ በማስታወሻ ደብተር ውስጥ መመዝገብን አስቡ። የሚከተሉት ማበረታቻዎች ሊረዱዎት ይችላሉ፦

  • በዚህ ዓመት ስለአዳኙ የተማርኩት ወይም የተሰማኝ ነገር…”

  • በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለአዳኙ መማሬ…” መንገድ ለውጦታል።

  • በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኝ የምወደው ሰው [ወይም ታሪክ] አዳኙ…” አስተምሮኛል።

ምናልባት ስለ መጽሐፈ ሞርሞን ያላችሁንን ሥሜት በማወቁ የሚባረክ ሰው ሊኖር ይችላል። ተሞክሮዎቻችህን እና ምስክርነቶቻችሁን ለሌሎች የምታካፍሉት እንዴት ነው? አንድ ቅጂ እንደ የገና ሥጦታ ለመስጠት ልትነሳሱ ትችላላችሁ። የመፅሐፈ ሞርሞን መተግበሪያ ማካፈልን ቀላል ያደርጋል።

ኤጲስ ቆጶስ ጄራልድ ኮሴ ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ በርካታ እውነቶችን አውጥተው ዘርዝረዋል (“A Living Witness of the Living Christ,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 39–40)። የእርሳቸውን ዝርዝሮች ልታዩዋቸው እና እነዚህ እውነቶች ህይወታችሁን እንዴት እንደለወጡት— ወይም ሊለውጡት እንደሚችሉ ልታሰላስሉ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች “መፅሓፈ ሞርሞን፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ይመልከቱ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ይህ እሁድ የወሩ አምስተኛ ሰንበት ስለሆነ የልጆች ክፍል አስተማሪዎች የመማሪያ አክቲቪቲዎችን በ“Appendix B: Preparing Children for a Lifetime on God’s Covenant Path” እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ የሰማይ አባት ሥጦታ ነው።

  • ልጆቻችሁ የሰማይ አባት ልጁን በመላክ በሰጠን ስጦታ ላይ እንዲያተኩሩ ለመርዳት የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል እንደ ገና ስጦታ መጠቅለል ትችላላችሁ። እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለተቀበላችኋቸው ወይም እንቀበላለን ብላችሁ ተስፋ ስላደረጋችኋቸው ተወዳጅ የገና ስጦታዎች መነጋገር ትችላላችሁ። ከዚያም የክርስቶስን ሥዕል ሊፈቱና እርሱ ለእኛ እንዴት ውድ ስጦታ እንደሆነ መወያየት ይችላሉ። እንደ “He Sent His Son” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 34–35) ዓይነት መዝሙር ይህን ውይይት ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል። በኢየሱስ መወለድ ምክንያት ያገኘናቸውን በረከቶች የሚገልጹ ሐረጎችን በመዝሙሩ ውስጥ እንዲፈልጉ ልጆቻችሁን እርዷቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ እንዲሆን ተወልዷል።

  • ልጆቻችሁ ስለ ኢየሱስ ውልደት የሚያውቁትን ለእናንተ መንገር ያስደስታቸው ይሆናል። የGospel Art Book ታሪኩን እንዲናገሩ የሚረዳቸው በርካታ ሥዕሎች አሉት። (ቁ. 282930፣ 31 ይመልከቱ)። ስለአዳኙ ህይወት እና ስለኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ የሚያሳዩ ሥዕሎችን መመልከትም ትችላላችሁ። የሰማይ አባት ኢየሱስ ክርስቶስን የላከው ለምንድን ነው?

    ምስል
    መልአክ
  • ልጆቻችሁ የኢየሱስን ውልደት እና አገልግሎት የሚያሳዩ የራሳቸውን ሥዕሎችን መሳልም ያስደስታቸው ይሆናል። ምናልባት በ1 ኔፊ 11:13-23ሞዛያ 3:5–10ሔለማን 14:1–13፤ እና 3 ኔፊ 1:4–22 ውስጥ የተገለፁትን ነገሮች ሊስሉ ይችላሉ። ከዚያም ሥዕሎቻቸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሚያስተምሩ ሊነግሯችሁ ይችላሉ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ እና መፅሐፈ ሞርሞን ሁለቱም ስለኢየሱስ ውልደት እንደሚያስተምሩ አፅንዖት ለመስጠት በሉቃስ 2:4–14ማቴዎስ 2:1–2፤ እና 3 ኔፊ 1:15፣ 19–21 የተገለጹትን ክስተቶች መዘርዘር ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ የትኞቹ ክስተቶች በቤተልሔም፣ በአሜሪካዎቹ ወይም በሁለቱም ተከስተው እንደነበረ ለማረጋገጥ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መፈለግ ይችላሉ። የኢየሱስ ክርስቶስ ሁለተኛ ምስክር የሆነው መፅሐፈ ሞርሞንን ስላለን አመስጋኞች የሆንነው ለምንድን ነው?

ልጆች ታሪኮችን ይወዳሉ። ልጆች እውነትን እንዲማሩ እና እንዲያስታውሱ ከሚያደርጉ ምርጥ ከሆኑት መንገዶች መካከል አንዱ ታሪክ ነው። ስለኢየሱስ ውልደት ታሪክ ስታካፍሉ፣ በአዳኝ ላይ ያላችሁን እምነት ለማጠናከር የረዷችሁን ከህይወታችሁ የተገኙ ታሪኮችን ማካፈልንም አስቡ።

መፅሐፈ ሞርሞን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በዚህ አመት መፅሐፈ ሞርሞንን ስትጨርሱ ከዚህ የተቀደሰ መጽሐፍ ያገኛችኋቸውን የምትወዷቸውን ታሪኮች ወይም ምንባቦች አንዳችሁ ላንዳችሁ ለማካፈል ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። በኑ፤ ተከተሉኝ ወይም የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ሥዕሎች መመልከት ልጆቻችሁ በዚህ ዓመት የተማሩትን እንዲያስታውሱ ሊረዳቸው ይችላል። እነዚህ ታሪኮች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሚያስተምሩን እንዲያዩ እርዷቸው።

  • ለልጆቻችሁ የኢየሱስን ሥዕል ልትሰጧቸው ወይንም የራሳቸውን እንዲስሉ ልትፈቅዱላቸው ትችላላችሁ። 2 ኔፊ 25:23፣ 26፣ ስታነቡ የክርስቶስን ሥም በጠራችሁ ቁጥር ሥዕሎቻቸውን ከፍ አድርገው እንዲይዙ ጋብዟቸው። መፅሐፈ ሞርሞን “በክርስቶስ [እንድናምን]” እንዲረዳን እንደተፃፈ መስክሩ (2 ኔፊ25:23)።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
መልአክ ድንግል ማሪያምን ለኔፊ በራዕይ እያሳየው።

የኔፊ የድንግል ማርያም ራዕይ፣ በጁዲት ኤ. ሜህር