ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 16–22፦ “ወደ ክርስቶስ ኑ እናም በእርሱ ፍፁማን ሁኑ።” ሞሮኒ 10


ታህሳስ 16፟–22፦‘ወደ ክርስቶስ ኑ እና በእርሱ ፍፁማን ሁኑ’ ሞሮኒ 10፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

“ታህሳስ 16–22። ሞሮኒ 10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ) (2023 [እ.አ.አ])

ምስል
ኢየሱስ ለኔፋውያን ታየ

That Ye May Know [ታውቁ ዘንድ፣ በጋሪ ኤል. ካፕ

ታህሳስ 16–22፦“ወደ ክርስቶስ ኑ እናም በእርሱ ፍፁማን ሁኑ።”

ሞሮኒ 10

መፅሃፈ ሞርሞን “የጌታ ምህረቶች ርህራሄ በእምነታቸው ምክንያት ለመዳን ሀይል እስኪኖራቸው ድረስ ሀያል እንዲሆኑ በመረጣቸው ላይ ሁሉ” (1 ኔፊ 1:20) እንደሆነ ኔፊ ሊያሳየን በሚሰጠው ተስፋ ይጀምራል። መፅሐፉ ሞሮኒ ባደረገው ተመሳሳይ ግብዣ ይዘጋል፦“ምን ያህል መሃሪ እንደነበረ እንድታስታውሱ” (ሞሮኒ 10:2–3)። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የአዳኙ ይቅርታ ምሳሌ የሆኑ ምን ምሳሌዎችን አይታችኋል ? እግዚአብሔር የሌሂን ቤተሰብ በምድረ በዳ እና በታላላቅ ባህሮች ላይ የመራበትን የምህረት መንገድ፣ ነፍሱ ይቅርታን በተራበች ጊዜ ለሄኖስ ያሳየውን ርኅራኄ፣ ወይም የቤተክርስቲያኗ ደመኛ ጠላት ለሆነው (በኋላ ፍርሃት አልባ ተከላካዮቹ ከነበሩት መካከል አንዱ ሆኗል) ለአልማ ያሳየውን ምሕረት ልታስቡ ትችላላችሁ። ወይም ሀሳባችሁ ከሞት የተነሳው አዳኝ የታመሙ ሰዎቻቸውን በመፈወስ እና ትንንሽ ልጆቻቸውን በመባረክ ለሕዝቡ ወዳሳየው ምህረት ሊዞር ይችላል። መፅሐፈ ሞርሞን እያንዳንዳችን የእግዚአብሔርን ምህረት እንድንቀበል ለመጋበዝ ተጽፎ ስለነበረ ምናልባት ከሁሉም በላይ፣ ይህ ሁሉ “ጌታ ምን ያህል መሃሪ እንደነበረ” ሊያስታውሳችሁ ይችላል—ይኸውም፣ በሞሮኒ የመሰናበቻ ቃላት ውስጥ የተገለጸ “ወደ ክርስቶስ ኑ እናም በእርሱ ፍፁማን ሁኑ” የሚል ግብዣ ነው (ሞሮኒ 10:32)።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ሞሮኒ 10፥3–7

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የሁሉንም ነገሮች እውነትበመንፈስ ቅዱስ ኃይል ላውቅ እችላለሁ።

ሞሮኒ 10፥3–7 ውስጥ የተሰጠው ተስፋ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት ቀይሯል። የእናንተን የቀየረው እንዴት ነው? ሞሮኒ 10:3-7 ስታነቡ ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት የበለጠ በጥንቃቄ ማንበብን አስቡ። ይህ ምን ማለት ነው? እንደሚሉ ዓይነት ጥያቄዎችን ራሳችሁን በመጠየቅ እያንዳንዱን ሐረግ መመርመር ትችላላችሁ። ይህንን ሥራ እንዴት በተሻለ ሁኒታ መሥራት እችላለሁ? በዚህ ላይ ምን ተሞክሮዎች ነበሩኝ?

መንፈሳዊ እውነትን ለማግኘት የምታደርጉትን የግል ፍለጋ ስታሰላስሉ ሌሎች በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እውነትን እንዴት እንዳገኙ መማር ሊረዳ ይችላል። ሽማግሌ ማቲያስ ሔልድ አዲስ የቤተክርስቲያን አባል እያሉ የነበራቸውን ልምድ ገልፀዋል (“Seeking Knowledge by the Spirit,” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 31–33 ይመልከቱ)። ሽማግሌ ዴቪድ ኤፍ. ኤቫንስ ገልፀዋል ብቤተክርስቲያን እንዳደገ ሆኖም ጥያቄዎች እንደነበሩት ልጅ ተሞክሯቸውን ገልፀዋል (“The Truth of All Things,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 68–70)። ከእነዚህ መልዕክቶች መካከል አንዱን ወይም ሁለቱንም ማንበብን እና ከእውነት ፍለጋዎቻቸው ለእናንተ የሚጠቅመውን የምትማሩትን ማንኛውንም ነገር መፃፍን አስቡ።

በተጨማሪም እግዚአብሄር ስለእውነት ያስተማረውን ከቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ ውስጥ የተወሰኑትን ምንባቦች በማንበብ ልትመረምሩም ትችላላችሁ፣ “እውነት” (ወንጌል ላይብረሪ)። ይበልጥ ጥልቅ ግንዛቤዎችን ያሏቸው የሚመስሉት የትኞቹ ጥቅሶች ናቸው? ምናልባት እውነትን በመንፈስ ለሚፈልግ ለሌላ ሰው ማካፈል ትችሉ ዘንድ አንዱን መምረጥ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “The Faith to Ask and then to Act,” ሊያሆና፣ ሕዳር 2021(እ.አ.አ)፣ 74–76፤ “Let the Holy Spirit Guide,” መዝሙር, ቁጥር 143፤ የወንጌል አርዕሥቶች፣ “Seek Truth and Avoid Deception,” ወንጌል ላይብረሪ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለወጥ ወንጌሉን ማወቅን እና መኖርን ይጠይቃል። የምትፅፉት ከሆነ በተማራችሁትን ነገር ላይ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ እድላችሁ ሰፊ ነው። እያስተማራችሁ ከሆነ የምታስተምሯቸው ሠዎች መንፈሳዊ ግንዛቤያቸውን እንዲመዘግቡ ጋብዟቸው።

ሞርሞን 10፥8–25

እግዚአብሄር መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ሰጥቶኛል።

አንድ ሠው“የእግዚአብሔርን ስጦታዎች [የሚክድባቸው]” ብዙ መንገዶች አሉ (ሞሮኒ 10:8)። አንዳንዶች የእነዚህን ሥጦታዎች ህልውናም ጭምር ይክዳሉ። ሌሎች ደግሞ ስጦታዎቻቸውን ችላ በማለት ወይም ባለማዳበራቸው ይክዳሉ። ሞሮኒ 10 8–25 በምታነቡበት ጊዜ መፈሳዊ ሥጦታዎቻችሁን እንድታውቁ እና የእግዚአብሄርን ልጆች ለመባረክ እንድትጠቀሙባቸው የሚረዷችሁን እውነቶች ፈልጉ። እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ፦መንፈሳዊ ሥጦታዎች ምንድን ናቸው? የሚሰጡት ለማን ነው? የሚሠጡት ለምንድን ነው? የምንቀበላቸው እንዴት ነው? በሞሮኒ 10:9–16 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሥጦታዎች የሚጠቀሙ ሰዎችን ምሳሌዎች ማሰብ ትችላላችሁ?

ሞሮኒ 10፥30–33

በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ፍጹም መሆን እችላለሁ።

“ወደ ክርስቶስ ኑ” የሚለው የሞሮኒ ምክር ስለ እርሱ ከመማር እና ከማሰብ የበለጠ ነገርን ያካትታል። ይልቁንም፣ በተቻለ መጠን ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስቶስ ለመምጣት የቀረበ ግብዣ ነው—እንደ እርሱ ለመሆን። ሞሮኒ10:30–33 በምታነቡበት ጊዜ፣ ወደ ክርስቶስ መምጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት እንደተቻለ እና ይህን በማድረግ የሚገኘውን ውጤት ለመገንዘብ የሚረዱ ሐረጎችን አስተውሉ።

የዚህን ዓመት የመፅሐፈ ሞርሞን ጥናታችሁን መለስ ብላችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰማችሁን እና የተማራችሁትን አሰላስሉ። ለምሳሌ፦ መፅሐፈ ሞርሞን ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ የረዳችሁ እንዴት ነው? ይበልጥ ሙሉ በሙሉ በፀጋው ላይ እንድትደገፉ የረዳችሁ እንዴት ነው? የአዳኙን ኃይል “እንዳትክዱ” የረዳችሁ እንዴት ነው? ስለ መልዕክቱ የማያውቁትን የምትወዷቸውን ሠዎች እና ጓደኞች ጨምሮ ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ያላችሁን ምስክርነት ለመስማት ለሚፈልግ ለአንድ ሰው ማካፈልን አስቡ።

በተጨማሪም “ሞሮኒ ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ይጋብዟል” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ይመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት፣ የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መፅሄቶች እትሞች ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ሞሮኒ 10፥3-4

መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ በራሴ ለማወቅ እችላለሁ።

  • መፅሐፈ ሞርሞን እውነት ስለመሆኑ እግዚአብሄርን እንዲጠይቁ ሞሮኒ ያቀረበውን ግብዣ ልጆቻችሁ እንዲቀበሉ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? አንብቡአስታውሱአሰላስሉ እንዲሁም ጠይቁ የሚሉ ቃላት የተፃፉባቸው ቁራጭ ወረቀቶችን ለእነሱ መስጠትን አስቡ። ልጆቻችሁ እነዚህን ቃላት በአልማ 10፧3-4 ውስጥ ሊያገኙ ይችላሉ። የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነቶቻችንን ለማግኘት እና ለማጠናከር ማንበበ፣ ማሰላሰል እና መጠየቅ ያለብን ምንድን ነው? ልጆቻችሁ በእነዚህ ጠቅሶች እና “Search, Ponder, and Pray” (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣ 109) በሚለው መዝሙር መከከል ያለውን ተመሳሳይነት ሊፈልጉም ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል በመጠቀም ስለሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎቹን መቅበር ለማውራት ይችላሉ (በተጨማሪም Chapter 54: The Promise of the Book of Mormon፣” የመጽሐፈ ሞርሞን ታሪኮች፣ 156 ይመልከቱ)። ትንንሽ ልጆች በሰሌዳዎች ላይ በመፃፍ እና በመቅበር ሞሮኒን እንደሆኑ ማስመሰል ሊያስደስታቸው ይችላል። ስለመፅሐፈ ሞርሞን ያላችሁን ምስክርነት አንዳችሁ ለአንዳችሁ አካፍሉ።

ሞርሞን 10:8–19

የሰማይ አባት መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ይሠጠኛል።

  • ልጆቻችሁን ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ለማስተማር ከ9 እስከ 16 ያሉትን ቁጥሮች በተለያዩ ቁራጭ ወረቀቶች ላይ መጻፍና እያንዳንዱን ወረቀት እንደ ስጦታ መጠቅለል ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ስጦታዎቹን በየተራ መፍታት፣ ከቁጥሮቹ ጋር የሚዛመዱትን በሞሮኒ10:9–16 ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች ማንበብ ከዚያም እያንዳንዱን መንፈሳዊ ስጦታ ለይተው ማወቅ ይችላሉ። የሰማይ አባት እነዚህን ስጦታዎች ልጆቹን ለመባረክ እንድንጠቀምባቸው እንዴት እንደሚፈልግ መናገር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የሰማይ አባት የሰጣቸውን ስጦታዎች እንዲያስተውሉ መርዳትም ትችላላችሁ።

ሞሮኒ 10፥32–33

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንድመጣ ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ “ወደ በክርስቶስ መምጣት]” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉ? ምናልባት ሞሮኒ 10:32ን ልታነቡና ሐረጉን ከእናንተ ጋር እንዲደግሙት ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ከዚያም በክፍሉ ውስጥ በአንድ ቦታ የኢየሱስን ምሥል በምስታስቀምጡበት ጊዜ ዓይናቸውን ሊጨፍኑ ይችላሉ። ከዚያም አይናቸውን መክፈት፣ ምሥሉን መፈለግ፣ በዙሪያው መሰብሰብ እና ወደ ክርስቶስ መምጣት ስለምንችልባቸው መንገዶች መነጋገር ይችላሉ። ምናልባት ወደ ክርስቶስ መምጣት ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን ጥያቄ መፃፍ ሊረዳ ይችላል። የሚሆኑ መልሶችን ለማግኘት ሞሮኒ 10:32–33 እንዲያሡ እርዷቸው (በተጨማሪም የእምነት አንቀጾች 1:3–4 ይመልከቱ)። ክርስቶስ እንድናደርግ የሚፈልገውን እና እርሱ ለእኛ ለማድረግ ቃል የገባውን ለመዘርዘር አብራችሁ ሥሩ።

  • ምናልባት ልጆቻችሁ “በሙሉ ኃይ[ሌ]፣አዕምሮ[ዬ] እና ጉልበ[ቴ] እግዚአብሔርን [እወዳለሁ]” የሚል ፅሁፍ ያለበት የልብ ቅርጽ ያለውን ባጅ መስራት እና ማሰማመር ያስደስታቸዋል (ሞሮኒ 10:32ን ይመልከቱ)። ይህንን እየሰሩ እያሉ እግዚአብሄርን እንደምንወደው እንዴት እንደምናሳየው ከእነርሱ ጋር ተነጋገሩ።

ለተጨማሪ ሃሳቦች የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

ምስል
ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ሲቀብር

ሞሮኒ መዝገቦቹን ከመቅበሩ በፊት “ጌታ ምን ያህል መሃሪ እንደነበረ እንድ[ናስታውስ]” ጋብዞናል (ሞሮኒ 10:–3)።