የጥናት እርዳታዎች
መሲህ


መሲህ

በዕብራውያን እና በአራሚያክ ቋንቋ ይህ ቃል “የተቀባ” ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል፣ ይህም በግሪክ ቋንቋ መሲህ ማለት ነው። ይህም የተቀባ ነቢይ፣ ካህን፣ ንጉስ፣ እና መምጣቱን አይሁዶች በጉጉት ይጠብቁት የነበረ አዳኝ ማለት ነው።

ብዙ አይሁዶች ከሮሜ ሀይል የሚያድናቸውን እና ታላቅ የሀገር ብልፅግናን ብቻ ይጠብቁ ነበር፤ በዚህም መሲህ ሲመጣ፣ መሪዎች እና ብዙ ሌሎች አስወገዱት። ትሁት እና ታማኝ የሆኑት ብቻ የናዝሬት ኢየሱስ እውነተኛው ክርስቶስ እንደሆነ ለማየት ችለው ነበር (ኢሳ. ፶፫ማቴ. ፲፮፥፲፮ዮሐ. ፬፥፳፭–፳፮)።