ምዕራፍ ፳፰
በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሀሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ይሰራሉ—ውሸትን፣ ከንቱነትን፣ እና የማይረባ ትምህርትንም ያስተምራሉ—በሐሰተኛ አስተማሪዎችም የተነሳ ክህደት ይበዛል—ዲያብሎስ በሰዎች ልብ ቁጣን ያመጣል—የተለያዩ ሐሰተኛ ትምህርቶችን ሁሉ ያስተምራል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ መንፈስ እንደገፋፋኝ ተናግሬአችኋለሁ፤ ስለሆነም፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ እንደሚሆኑ አውቃለሁ።
፪ እናም ሀከመጽሐፉ ላይ የተፃፉት ነገሮች ለሰው ልጆች፣ እና በተለይም የእስራኤል ቤት ቅሪት ለሆኑት ለእኛ ዘር፣ ታላቅ ለዋጋ ይኖራቸዋል።
፫ በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ለጌታም ያልሆነው የተሰሩት ሀቤተክርስቲያኖች፣ አንዱም ለሌላው ይለዋል—እነሆ፣ እኔ የጌታ ነኝ፤ እናም ሌሎቹም እኔ፣ እኔ የጌታ ነኝ ይላሉ፤ እናም ለጌታ ያልተሰሩት ቤተክርስቲያናት ሁሉ እንደዚህ ይላሉ—
፬ እናም አንዳቸው ከሌላኛው ይከራከራሉ፤ ካህናቶቻቸውም አንዱ ከሌላ ይከራከራሉ፣ እናም ከራሳቸው የሆነውን ትምህርት ሀያስተምራሉ፣ የመናገርን ችሎታ የሚሰጠውንም መንፈስ ቅዱስ ይክዳሉ።
፭ እናም የእግዚአብሔርን ሀኃይል፣ የእስራኤሉንም ቅዱስ ለይክዳሉ፤ ለህዝቡም እንዲህ ይላሉ—አድምጡን፣ እናም የእኛን መመሪያ ስሙ፤ እነሆም እግዚአብሔር ዛሬ ሐየለምና፣ ጌታና አዳኝ ስራውን ሰርቷል፣ እናም ኃይሉን ለሰዎች ሰጥቷልና።
፮ እነሆ፣ የእኔን መመሪያ አድምጡ፤ በጌታ እጅ የተሰራ ተአምር አለ ካሉ አትመኑአቸው፤ በዛሬ ጊዜ እርሱ ሀየተአምራት አምላክ አይደለምና፤ እሱ ስራውን ሰርቷል።
፯ አዎን፣ እናም ብዙዎች እንዲህ የሚሉ አሉ፥ ሀብሉ፣ ጠጡ፣ እናም ተደሰቱ፣ ነገ እንሞታለንና፤ ይህም ለእኛ መልካም ይሆናል።
፰ እናም ሌሎች ደግሞ እንዲህ የሚሉ ብዙ አሉ፥ ብሉ፣ ጠጡ፣ እናም ተደሰቱ፤ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔርን ፍሩ—ትንሽ ኃጢያትን ብንሰራ ሀጥፋተኛ አያደርገንም፤ አዎን፣ ትንሽም ለዋሹ፣ በቃሉ የተነሳ በሌላ ላይ ዕድል ተጠቀሙ፣ በጎረቤታችሁም ላይ ሐጉድጓድን ቆፍሩ፤ በዚህ ምንም ጉዳት የለም፤ እናም እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ ነገ እንሞታለንና፤ እናም ምንም እንኳን ጥፋተኛ ብንሆን፣ እግዚአብሔር በትንሹ ይቀጣናል፣ እናም በመጨረሻ በእግዚአብሔር መንግስት እንድናለን።
፱ አዎን፣ እናም እንደዚህ ውሸትና ከንቱና ሀየማይረባ ለትምህርትን የሚያስተምሩ፣ እናም በልባቸውም የታበዩና፣ ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለመሰወር የሚፈልጉ ብዙዎች ይኖራሉ፤ እናም ስራቸውም በጨለማ ውስጥ ይሆናል።
፲ እናም የቅዱሳን ሀደም ከምድር በእነርሱ ላይ ይጮሃል።
፲፩ አዎን፣ ሁላቸውም ሀመንገዳቸውን ስተዋል፤ ለተበላሽተዋልም።
፲፪ ሀበኩራትና፣ በሐሰተኛ አስተማሪዎች፣ እንዲሁም በሀሰት ትምህርት የተነሳ፣ ቤተክርስቲያናቸው ተበላሽቷል፣ እናም ቤተክርስቲያኖቻቸው ከፍ ብለዋል፤ በኩራትም የተነሳ ተወጥረዋል።
፲፫ በመልካሙ ቅዱስ ስፍራ የተነሳ ሀድሆችን ለይበዘብዛሉ፤ በመልካም ልብሳቸውም የተነሳ ድሆችን ይበዘብዛሉ፤ እናም ትሁታንንና በልባቸው ድሆች የሆኑትን ያሳድዳሉ፣ ሐበኩራታቸው የተነሳ ተወጥረዋልና።
፲፬ ሀአንገተ ደንዳና እና ትምክህተኞች ናቸው፤ እናም አዎን፣ ከጥቂት ትሁት የክርስቶስ ተከታዮች በስተቀር በኩራታቸው፣ በክፋታቸው፣ በእርኩሰታቸውና በዝሙት የተነሳ ሁሉም ለባክነዋል፤ ይሁን እንጂ፣ ተመርተዋል፣ በብዙ መንገድ የተሳሳቱበት ምክንያትም በሰዎች አስተያየቶች ስለተማሩ ነው።
፲፭ አቤቱ በልባችሁ ሀኩራት የተወጠሩ ለጥበበኞች፣ የተማሩና፣ ሀብታሞች፣ እናም ሀሰተኛ ትምህርትን የሚያስተምሩ ሁሉና፣ ዝሙትን የሚፈጽሙ ሁሉ፣ እናም ትክክለኛውን የጌታን መንገድ የሚያጣምሙ፣ ወዮ፣ ወዮ፣ ለእነርሱ ሐወዮላቸው ወደ ሲዖልም ይጣላሉና ይላል ሁሉን የሚገዛ ጌታ እግዚአብሔር።
፲፮ ፃድቁንም በከንቱ ነገር ሀዞር የሚይደርጉና ጥሩ የሆነውን የሚሰድቡ፣ እናም ዋጋ የለውም ለሚሉ ወዮላቸው! ጌታ እግዚአብሔር የምድር ነዋሪዎቹን የሚጎበኝበት ቀን በፍጥነት ይመጣልና፤ እናም በዚያን ቀን በጥፋት ለፈጽመው የበሰሉትም ይጠፋሉ።
፲፯ ነገር ግን እነሆ፣ የምድር ነዋሪዎች ለክፋታቸውና ለእርኩሰታቸው ንሰሀ ከገቡ አይጠፉም ይላል የሠራዊት ጌታ።
፲፰ ነገር ግን እነሆ፣ ያቺ ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን የምድር ሁሉ ሀጋለሞታም ወደ አፈር ለትወድቃለች፣ እናም አወዳደቋም ታላቅ ይሆናል።
፲፱ የዲያብሎስ መንግስት ሀመናወጥ አለበት፣ እናም የእርሱ የሆኑትም ለንስሀ መነቃቃት ይገባቸዋልና፣ አለበለዚያ ለዲያብሎስ በዘለዓለማዊ ሐሰንሰለቱ ይይዛቸዋል፣ እናም እነርሱ ለቁጣ ይነሳሳሉም፣ ይጠፋሉም፤
፳ እነሆም፣ በዚያን ቀን በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ሀይቆጣል፣ እናም ጥሩ በሆነውም ላይ ለቁጣ ያነሳሳቸዋል።
፳፩ እናም እርሱ ሌሎችን ሀያረጋጋልና፣ ቀስ ብሎም ወደ ስጋዊ ደህንነት አባብሏቸው እንዲህ ይላሉ፥ በፅዮን ሁሉም መልካም ነው፤ አዎን፣ ፅዮን ትለመልማለች፤ ሁሉም መልካም ነው—ለዲያብሎስም ነፍሳቸውን እንዲህ ያታልላል፣ እናም በጥንቃቄ ወደ ሲኦል ይመራቸዋል።
፳፪ እናም እነሆ፣ ሌሎችን እያሞገሰ ያስታቸዋል፣ እናም ሀሲኦል የለም ብሎ ይነግራቸዋል፤ እናም ይላቸዋል፥ እኔ ዲያብሎስ አይደለሁም፣ እርሱ የለምና—እናም ማላቀቅ በማይቻለው በመጥፎው ለሰንሰለቱ እስከሚያስራቸው ድረስ በጆሮአቸው እንዲህ ያንሾካሹካል።
፳፫ አዎን፣ በሞትና በሲኦል ተይዘዋል፤ እናም ሞትና ሲኦል እንዲሁም ዲያብሎስና በእነርሱም የተያዙት ሁሉ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መቆም አለባቸው፣ እናም እንደስራቸው ሀይፈረድባቸዋል፣ ከዚያም ለእነርሱ በተዘጋጀው ቦታ ወደማያቋርጥ ስቃይ ወደሆነው፣ እንዲሁም ወደ እሳትና ወደ ዲኑ ለባህር መሄድ አለባቸው።
፳፬ ስለዚህ፣ በፅዮን ለሚዝናናው ወዮለት!
፳፭ ሁሉ መልካም ነው! ብሎ ለሚጮህ ወዮለት!
፳፮ አዎን፣ የሰዎችን አስተያየት ሀለሚያዳምጥና፣ የእግዚአብሔርን ኃይልና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለሚክድ ወዮለት!
፳፯ አዎን፣ እኛ ተቀብለናል፣ እናም ሌላ ሀአንፈልግም ለሚልም ወዮለት።
፳፰ እናም በአጠቃላይ ለሚንቀጠቀጡ ሁሉና፣ በእግዚአብሔር እውነት ምክንያት ሀለሚቆጡ ወዮላቸው! እነሆም ለበአለት ላይ የሰራ ይህን በደስታ ይቀበላል፤ እናም በአሸዋ መሰረት ላይ የሰራው ግን በፍርሃት እወድቃለሁ ብሎ ይንቀጠቀጣል።
፳፱ የእግዚአብሔርንም ቃል ተቀብለናል፣ እናም የእግዚአብሔርንም ቃል ከዚህ በተጨማሪ ሀምንም ለአንፈልግም፣ ምክንያቱም በቂ አለንና ለሚሉት ወዮላቸው!
፴ እነሆም፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል—ለሰው ልጆች በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ ሀበስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ እሰጣለሁ፤ ትምህርቴን የሚሰሙ፣ እናም ምክሬን የሚያደምጡ የተባረኩ ናቸው፣ ለጥበብን ይማራሉና፤ ሐለሚቀበልም መተጨማሪ እሰጣለሁና፤ እና ይበቃናል ለሚሉም፣ ያላቸውም እንኳን ቢሆን ይወሰድባቸዋል።
፴፩ ሀእምነቱን በሰው የሚያደርግ፣ ወይም ስጋን ክንዱ የሚያደርግ፣ ወይም አስተያየታቸው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል አማካኝነት ካልተሰጠ በስተቀር የሰውን ትምህርት የሚሰማ የተረገመ ነው።
፴፪ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለአህዛብ ሀወዮላቸው ይላል! ክንዴን ከቀን ወደቀን ብዘረጋትም እንኳን ይክዱኛልና፣ ይሁን እንጂ፣ ንስሀ የሚገቡና ወደ እኔ የሚመጡ ከሆነ እምራቸዋለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ለክንዴ ቀኑን ሁሉ ትዘረጋለችና ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።