የጥናት እርዳታዎች
መግቢያ


ከጆሴፍ ስሚዝ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምርጫዎች

የሚቀጥሉት ከንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ቅጅ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.) የተመረጡ ክፍሎች ናቸው። ጌታ የመጀመሪያዎቹ ቃላቶች ከተጻፉ በኋላ የተቀየሩትን ወይም የጠፉትን የመፅሐፍ ቅዱስ እውነቶች ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግሞ እንዲመልሳቸው አነሳስቶት ነበር። እነዚህ ደግመው የተመለሱ እውነቶች ትምህርቶችን አብራርተዋል እና የቅዱስ መጻህፍት መረዳትን አሻሽለዋል።

ጌታ የመጀመሪያ ጸሀፊዎች የጻፉትን አንዳንድ እውነቶችን ለጆሴፍ ስለገለጠለት፣ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም በአለም ውስጥ ካሉት ማናቸውም ሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የተለየ ነው። በዚህም አስተያየት፣ ትርጉም የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ሰፋ ባለና ከልምድ በተለየ መንገድ ነው የሚጠቀምበት፣ ምክንያቱም የጆሴፍ ትርጉም ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ የተተረጎመ ሳይሆን በራዕይ የመጣ ነበር።

የጆሴፍ ስሚዝ የንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከተለያዩ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍሎች ጋር የተገናኘ ወይም በእነዚህ ውስጥ የተጠቀሰ ነው (ክፍሎች ፴፯፵፭፸፫፸፮፸፯፹፮፺፩፣ ና ፻፴፪ ተመልከቱ)። ደግሞም፣ መፅሐፈ ሙሴ እና ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተወሰዱ ምንባቦች ናቸው።

ለጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ተጨማሪ መረጃ፣ የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.)”ን ተመልከቱ።

የሚቀጥሉት ምሳሌዎች ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተመረጡ ናሙናዎችን ያሳያሉ።

ምስል
ምሳሌ

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱። ከማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱ ጋር አነጻፅሩ፤ በሉቃስ ፬፥፪፣ ፭–፲፩ም እንደዚህ አይነት ቅያሬዎች ነበሩ

ኢየሱስ የተመራው በመንፈስ እንጂ በሰይጣን አይደለም።

ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ይሆን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረበዳ ወሰደው።

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅድስት ከተማ ተወሰደ፣ እና መንፈስ እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቆመው።

ከእዚያም በኋላ ዲያብሎስ ወደእርሱ መጣ እና እንዲህ አለው፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፣ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።

ደግሞም፣ ኢየሱስ በመንፈስ ውስጥ ነበር፣ እና ይህም ወደ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳየው።

እና ዲያብሎስም ወደ እርሱ እንደገና መጣ፣ እና አለው፣ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ።

ይህ በደመቀ አይነት የተጻፈው ጥቅስ ከንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ጆሴፍ ስሚዝ የተረጎመው ምንባብ ነው። ትርጉሙ ወደ መፅሐፍ ቅዱስ ጽሁፍ ቃላቶችን በዳግም ስለመለሰ፣ የአንቀጽ ቁጥሮች እናንተ ከምትጠቀሙበት ቅጂ የተለየ ይሆናል።

ይህ ማጣቀሻ በመፅሐፍ ቅዱሳችሁ ውስጥ የትኛውን ጥቅሰት ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ጋር ለማነጻጸር እንደሚገባችሁ ይጠቁማል።

በቅንፍ ውስጥ ያለው የጆሴፍ ስሚዝን ትርጉምን ከመፅሐፍ ቅዱሳችሁ ጋር ማነጻጸር የሚገባችሁ ጥቅስ ነው።

ይህ ጽሁፍ ጆሴ ስሚዝ እንደተረጎመው ነው። (ጠመም ባለ የፊደል አጣጣል የተጻፉት በንጉስ ጄምስ ጽሁፍ ጋር የሚለያዩበትን ቃላቶች ለማሳየት ነው።)