የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ተጨማሪ መረጃ መግቢያየሚቀጥሉት ከንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ቅጅ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.) የተመረጡ ክፍሎች ናቸው። ጌታ የመጀመሪያዎቹ ቃላቶች ከተጻፉ በኋላ የተቀየሩትን ወይም የጠፉትን የመፅሐፍ ቅዱስ እውነቶች ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግሞ እንዲመልሳቸው አነሳስቶት ነበር። እነዚህ ደግመው የተመለሱ እውነቶች ትምህርቶችን አብራርተዋል እና የቅዱስ መጻህፍት መረዳትን አሻሽለዋል። ጆ.ስ.ት.፣ ኦሪት ዘፍጥረት ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፩–፰ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ ጽሁፍ በጆሴፍ ስሚዝ በዳግም ተመልሶ ነበር እናም ከታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ እንደ ተመረጠ የመፅሐፈ ሙሴ ታትሟል። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፱ከጎርፍ በኋላ፣ ኖህ ምድርን እንደገና እንዳይረግም ጌታን ጠየቀ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፬መልከ ጼዴቅ አብርሐምን ባረከ። የመልከ ጼዴቅ ታላቅ አገልግሎት እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት በረከቶች ተዘርዝረዋል። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፭አብርሐም ስለትንሳኤ ተማረ እናም የኢየሱስን ስጋዊ አገልግሎት ተመለከተ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፯ህዝቡ፣ ከጥምቀት በተጨማሪ፣ የወንጌል ስርዓቶችን አላከበሩም። እግዚአብሔር የግርዘት ቃል ኪዳን እና የልጆች ተጠያቂነት እድሜ ለአብርሐም ገለጸ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፱ሎጥ የሰዶምን ክፋት ተቋቋመ፣ እናም መላዕክት ጠበቁት። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፳፩አብርሐም የዘለአለም እግዚአብሔርን አመለከ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፵፰ኤፍሬም እና ምናሴ የእስራኤል ጎሳዎች ሆኑ። በጥንት ይኖር የነበረው ዮሴፍ ቤተሰቦቹን በጊዜው እንዳዳናቸው፣ የእርሱ ትውልዶችም በኋለኛው ቀናት እስራኤልን በመንፈስ ያድናሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፶ጆሴፍ በግብፅ ውስጥ ሙሴ እስራኤልን ከግብጻዊ ባርነት ነጻ እንደሚያደርግ፤ የጆሴፍ ትውልዶች ቅርንጫፍ በጌታ ቃል ኪዳኖች ወደሚታወሱበት ወደ ሩቅ አገር እንደሚመሩ፤ እግዚአብሔር የይሁዳንና የዮሴፍን መዝገቦች እንዲያዋህድ ዮሴፍ የሚባል ነቢይ በኋለኛው ቀናት እንደሚጠራ፤ እና አሮን እንደ ሙሴ ተናጋሪ እንደሚያገለግል ተነበየ። ጆ.ስ.ት.፣ ኦሪት ዘፀአት ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፬ጌታ ለፈርዖን ልብ መፅናት ሀላፊ አይደለም። ደግሞም ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፯፥፫፣ ፲፫፤ ፱፥፲፪፤ ፲፥፩፣ ፳፣ ፳፯፤ ፲፩፥፲፤ ፲፬፥፬፣ ፰፣ ፲፯ን ተመልከቱ፤ እያንዳንዱ ማጣቀሻዎች፣ በትክክል ሲተረጎሙ፣ ፈርዖን የራሱን ልብ እንዳጸና ያሳያሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፲፰ዮቶር ሊቀ ካህን ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፳፪ገዳዮች አይኖሩም። ጆ.ስ.ት.፣ ኦሪት ዘፀአት ፴፪ጌታ ንስሀ የሚገቡትን እስራኤላውያንን ያተርፋል። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፫ማንም ኀጥያተኛ ሰው የእግዚአብሔርን ፊት ማየት እና መኖር አይችልም። ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፬እግዚአብሔር እንደገና ህግን በሙሴ በተዘጋጀ ድንጋይ ላይ ጻፈ እናም የመልከ ጼዴቅ ክህነትና ስርዓቶችን ከእስራኤል ህዝብ ወሰደ። በዚህ ምትክም የስጋዊ ትእዛዛት ህግን ሰጣቸው። ጆ.ስ.ት.፣ ኦሪት ዘዳግም ጆ.ስ.ት.፣ ዘዳግም ፲በመጀመሪያው ጽላቶች ላይ እግዚአብሔር የቅዱስ ክህነት ዘለአለማዊ ቃል ኪዳንን ገለጸ። ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ሳሙኤል ፲፮በሳኦል ላይ የመጣው የክፉ መንፈስ ከጌታ አልነበረም። ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ሳሙኤል ፲፪የዳዊት አሰቃቂ ኀጥያት በእግዚአብሔር አልተረሣም። ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ዜና ቀዳማዊ ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ዜና ቀዳማዊ ፳፩መልአኩ ኢየሩሳሌምን እንዳይደመስስ እግዚአብሔር አቆመው። ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ዜና ካልዕ ጆ.ስ.ት.፣ መፅሐፈ ዜና ካልዕ ፲፰ጌታ በነብያት አፎች ውስጥ የሀሰት መንፈስ አያስገባም። ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙረ ዳዊት ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፩በመጨረሻው ቀናት ጻድቃን ወደ ጌታ ተራራ ይሸሻሉ። ጌታ ሲመጣም፣ ክፉውን ያጠፋል እናም ጻድቁን ያቤዛል። ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፬መዝሙረኛው በመጨረሻዎቹ ቀናት እውነቶች እንደሚጠፉ ተመለከተ እናም የፅዮን በዳግም መመስረትን በጉጉት ጠበቀ። ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፳፬የክብር ንጉስ በሚመጣበት ጊዜ ህዝቡን ይቤዣቸዋል። ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፻፱ለጠላቶቻችን መጸለይ ይገባናል። ጆ.ስ.ት.፣ ትንቢተ ኢሳይያስ ጆ.ስ.ት.፣ ኢሳይያስ ፳፱በኢየሩሳሌም ከበፊት በጥንት ነቢያት የተሰበከው መልእክት በበኋለኛው ቀናት “ከምድር ውስጥ” በሚመጣው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ይሰበካል። ጆ.ስ.ት.፣ ኢሳይያስ ፵፪ጌታ እውነትን ለማየት ወይም ለመስማት ያልመረጡትን ለማስተማር አገልጋዩን ይልካል፤ የሚያዳምጡና የሚታዘዙም ፍጹም ይሆናሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ትንቢተ ኤርምያስ ጆ.ስ.ት.፣ ኤርምያስ ፳፮ጌታ ንስሀ አይገባም፤ ሰዎች ንስሀ ይገባሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ትንቢተ ዓሞጽ ጆ.ስ.ት.፣ ዓሞጽ ፯ጌታ ንስሀ አይገባም፤ ሰዎች ንስሀ ይገባሉ። ጆ.ስ.ት.፣ የማቴዎስ ወንጌል ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫ነቢያት ቤተ ልሔም መሲህ የሚወለድበት ቦታ እንደሆነ አቅድመው ተናገሩ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬ኢየሱስ የተመራው በመንፈስ እንጂ በሰይጣን አይደለም። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፭ትእዛዛትን የሚጠብቁ እና እንደዚህ እንዲያደርጉ የሚያስተምሩ ሌሎች ይድናሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፮ጌታ ወደ ፈተና አይመራንም። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯ፃድቅ ባለመሆን አትፍረዱ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፱ኢየሱስ የፈሪሳውያንን ጥምቀት አስወገደ፤ ይህም ምንም ዋጋ የለውም ምክንያቱም እነርሱ እርሱን አይቀበሉትምና። እርሱ የሙሴ ህግን የሰጠ እንደሆነ አወጀ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፩መጥምቁ ዮሐንስ ለአዳኝ መንገድን ለማዘጋጀት የሚመጣው ኢልያ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፪በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር አይሰረይለትም። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፫ከአለም መጨረሻ (ከክፉዎች መደምሰስ) በፊት፣ ከሰማይ የተላኩ መልእክተኞች ጻድቅን ከክፉዎች መካከል ይሰበስባሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፮ኢየሱስ “የአንድን መስቀል ማንሳት” የሚለው ትርጉም ምን እንደሆነ ገለጸ፥ ኀጥያተኝነትን እና የአለም ስግብግብነትን መካድ እና የእርሱንም ትእዛዛት መጠበቅ ናቸው። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፯ኢየሱስ አንዱ ለማዘጋጀት እና አንዱ ዳግም ለመመለስ፣ ስለሚያደርጉት ሁለት ኤልያሶች አስተማረ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፰ህጻናት ንስሀ መግባት አያስፈልጋቸውም። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፱ህጻናት ይድናሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩ሰው በኢየሱስ ከማመኑ በፊት ንስሀ መግባት አለበት። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፫በሰማይ ያለው ፈጣሪያችን ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፮ኢየሱስ መጀመሪያ የቅዱስ ቁርባንን እንጀራ ቆረሰ እናም ባረከው። ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስ ስጋ እና ደም መታሰቢያ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፯የይሁዳ ሞት ተገልጿል። ጆ.ስ.ት.፣ የማርቆስ ወንጌል ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፪የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው ምክንያቱም ሰንበትን ሰርቷታልና። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፫በመንፈስ ቅዱስ ላይ ከሚሳደቡት በስተቀር፣ ኢየሱስ ንስሀ የሚገቡ ኃጢያተኞችን በሙሉ ይሰርይላቸዋል። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፯ኢየሱስ ነቢያትን የሚያስወግዱ እና የሙሴን ህግ የማያከብሩን ወቀሰ። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፰ስለኢየሱስ ለመሞት ፈቃደኛ የሆነ ደህንነትን ይቀበላል። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱መጥምቁ ዮሐንስ በመለወጫ ተራራ ላይ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፪እግዚአብሔር የሙታን አምላክ አይደለም፣ ምክንያቱም ሙታንን ከመቃብራቸው ያስነሳልና። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን ለእርሱ ስጋ እና ደም መታሰቢያነት መሰረተ። ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፮ሁለት መላእክቶች ሴቶችን በአዳኝ መቃብር አጠገብ ሰላም አሏቸው። ጆ.ስ.ት.፣ የሉቃስ ወንጌል ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፩የመጥምቁ ዮሐንስ አባት ዘካሪያስ የክህነት ሀላፊነቱን አከናወነ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፪በቤተመቅደስ ውስጥ መምህራን ኢየሱስን አዳመጡ እና ጥያቄዎችንም ጠየቁት። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫ክርስቶስ እንደተተነበየው ደህንነትን ለእስራኤል እና ለአህዛብ ለማምጣት ይመጣል። በዘመን ፍጻሜ፣ በአለም ላይ ለመፍረድ እንደገና ይመጣል። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፮ኢየሱስ ከጠላት ጋር ከመከራከር በመሰደድ መጽናት ይሻላል ብሎ አስተማረ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፱የአለም ሀብትን ማግኘት የራስን ነፍስ ከማጣት የሚጠቅም አይደለም። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፩የቅዱስ መጻሕፍት ሙሉነት የእውቀት ቁልፍ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን መስደብ እንደማይሰረይ ገለጸ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፬ሙሴን እና ነቢያትን የሚያውቁ በኢየሱስ ያምናሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፮ህግ እና ነቢያት ስለኢየሱስ ይመሰክራሉ። ፈሪሳውያን መንግስትን ለመደምሰስ ይፈልጋሉ። ኢየሱስ የሀብታሙን ሰው እና የአልዓዛርን ምሳሌ አስተዋወቀ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯የእግዚአብሔር መንግስት አስቀድማ መጥታለች። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፰በባለጠግነት ማመን ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባትን ይከለክላል። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፩ኢየሱስ ስለመምጫው አንዳንድ ምልክቶች ተናገረ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፫ኢየሱስ እየሰቀሉት ላሉ የሮሜ ወታደሮች ይቅርታ ጠየቀ። ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፬ሴቷ በኢየሱስ መቃብር አጠገብ ሁለት መላእክት አየች። ጆ.ስ.ት.፣ የዮሐንስ ወንጌል ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፩የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ተሰብኳል። መጥመቁ ዮሐንስ የክርስቶስን መንገድ የሚያዘጋጀው ኤልያስ ነው፣ እና ኢየሱስ ክርስቶስም ሁሉንም ነገሮች ደግሞ የሚመልሰው ሌላው ኤልያስ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፬ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመግደል ፈለጉ። እርሱም ጥቂት ጥምቀቶችን አከናወነ፣ ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ተጨማሪዎችን አከናወኑ። ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፮የአብ ፍላጎት ሁሉም ኢየሱስን እንዲቀበሉ ነው። የኢየሱስ ፍላጎትን የሚያደርጉ በጻድቃን ትንሳኤ ይነሳሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፲፫ኢየሱስ የአይሁድ ህግን ለመፈጸም የሐዋሪያትን እግሮች አጠበ። ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፲፬የጭለማ ልዑል፣ ወይም ሰይጣን፣ የዚህ አለም ነው። ጆ.ስ.ት.፣ የሐዋርያት ስራ ጆ.ስ.ት.፣ የሐዋርያት ስራ ፱ጳውሎስ በሚቀየርበት ጊዜ አብረውት የነበሩት ብርሀንን አዩ፣ ነገር ግን ድምፅን አልሰሙም ወይም ጌታን አላዩም። ጆ.ስ.ት.፣ የሐዋርያት ስራ ፳፪ዋናው ሻለቃ ጳውሎስን ከታሰረበት ፈታው። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ሮሜ ሰዎች ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፫ሰው መልካም ነገርን ለማምጣት ክፉ ማድረግ እንደማይችል ጳውሎስ አስተማረ። ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬ሰው ለመዳን የሚችለው፣ የሙሴ ህግን ከመከተል ጋር ባለው ስራ ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ብቻ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፯የሰዎችን ነፍሶች ቋሚ በሆነ ሁኔታ ለመልካም ለመቀየር ሀይል ያለው ክርስቶስ ብቻ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፰የስጋ መንገድን የሚከተሉት እግዚአብሔርን አያስደስቱም። ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፲፫ህዝባዊ ባለስልጣኖችን የሚያከብሩ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ክብር ከፍተኛ እና በጣው ፍጹም የሆነ ያደርጉታል። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፩ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯ጳውሎስ ጋብቻ የሚፈለግ እንደሆነ አስተማረ። በሚስዮን የተጠሩት፣ ግን፣ በአገልግሎታቸው ጊዜ ያላገቡ ቢሆኑ እግዚአብሔርን በተሻለ ለማገልገል ይችላሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፲፭በትንሳኤ ሶስት የክብር ደረጃዎች አሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፪ ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ቆሮንቶስ ፭ጳውሎስ ቅዱሳንን በስጋ አይነት ኑሮ እንዳይኖሩ መከራቸው። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ገላትያ ሰዎች ጆ.ስ.ት.፣ ገላትያ ፫የሙሴ የመጀመሪያው ቃል ኪዳን፣ ወይም የህግ፣ መካከለኛ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ጆ.ስ.ት.፣ ኤፌሶን ፬ከጽድቅ ያልሆነ ቁጣ ኀጥያት ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ቄላስይስ ሰዎች ጆ.ስ.ት.፣ ቁላስይስ ፪የሰዎች ትእዛዛት ራስን በመቆጣጠር አይነት ነገር ላይ ጥቅም ይኖረዋል፣ ግን እነርሱ እግዚአብሔርን አያከብሩም ወይም ሰውን አያድኑም። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ፩ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ተሰሎንቄ ፬ጌታ በሚመጣበት ጊዜ በህይወት የሚኖሩ ጻድቅ ሰዎች ከጻድቅ ሙታን የተለየ ምንም ልዩ እድል አይኖራቸውም። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ፪ ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ተሰሎንቄ ፪ሰይጣን መውደቅን ወይም ክህደትን ጌታ ከመመለሱ በፊት ያመጣል። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ጢሞቴዎስ ፩ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ጢሞቴዎስ ፪ክርስቶስ አንድያ ልጅና መካከለኛ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ጢሞቴዎስ ፫ቤተክርቲያኗ የተመሰረተችው ኢየሱስ ስጋዊ ሆነ፣ ወንጌልን አስተማረ፣ እና ወደ አባቱ ተመለሰ በሚለው ዋና መሰረታዊ መርሆ ላይ ነው። በሚቀጥሉት ጥቅሰቶች ውስጥ ትኩረት በመስጠት የተቀየሩት ኢየሱስ ክርስቶስ “የእውነት አምድ እና ምድር” እንደሆነ አፅንኦት ለመስጠት ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ጢሞቴዎስ ፮የዘለአለማዊ ህይወት (የወንጌል) ብርሀን በውስጣቸው የሚኖርላቸው ኢየሱስን ማየት ይችላሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ወደ ዕብራውያን ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፩መላእክት አገልጋይ መንፈሶች ናቸው። ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፬ልባቸውን የሚያደነድኑ አይድኑም፤ ንስሀ የሚገቡ ወደ ጌታ እረፍት ይገባሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፮የክርስቶስ ትምህርት መሰረታዊ መርሆች ወደ ፍጹምነት ይመራሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፯መልከ ጼዴቅ በእግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱሱ ካህን ነበር። ይህን ክህነት የሚቀበሉ ኁሉ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ይችላሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፲፩እምነት ተስፋ የተደረገባቸውን ነገሮችን ማረጋገጫ ነው። ጆ.ስ.ት.፣ የያዕቆብ መልእክት ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፩ፈተናዎች ሳይሆን ስቃዮች ለመቀደስ ይረዱናል። ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪አባላት አንድን ሰው ከሌላ በላይ ከፍ አድርገው አይመልከቱ። ጆ.ስ.ት.፣ የጴጥሮስ መልእክት ፩ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ጴጥሮስ ፫በወህኒ ቤት ውስጥ ያሉት አንዳንድ መንፈሶች በኖኀ ቀናት ውስጥ ጻድቃን አልነበሩም። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ጴጥሮስ ፬ወንጌሉ ለሙታን ተሰብኳል። ጆ.ስ.ት.፣ የጴጥሮስ መልእክት ፪ ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ጴጥሮስ ፫በመጨረሻው ቀናት፣ ብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ይከዳሉ። ሲመጣም፣ ብዙ የፍጥር መዓቶች ይደርሳሉ። በጻድቅነት ከጸናን፣ አዲስ ምድር እንቀበላለን። ጆ.ስ.ት.፣ የዮሐንስ መልእክት ፩ ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ዮሐንስ ፪ንስሀ ከገባን ክርስቶስ ከአብ ጋር አማላጃችን ነው። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ዮሐንስ ፫ከእግዚአብሔር የተወለደ በኀጥያት አይቀጥልም። ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ዮሐንስ ፬በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ሊያዩት የሚችሉት። ጆ.ስ.ት.፣ የዮሐንስ ራዕይ ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፩ሐዋርያው ዮሐንስ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ትንቢቶች ተቀበለ። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመልአክ ተጎበኘ። ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪ክፉዎች ወደገሀነም ይጣላሉ። ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፭አስራ ሁለት የእግዚአብሔር አገልጋዮች በምድር ሁሉ ተልከዋል። ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፲፪ዮሐንስ የሴቷን፣ የልጅ፣ የብረት በትርን፣ የዘንዶውን፣ እና የሚካኤልን ምሳሌዎች ገለጻቸው። በሰማይ የተጀመረው ጦርነት በምድር ቀጥሏል። በጆ.ስ.ት. ውስጥ የአንቀጾች ተከታታይነት እንዴት እንደተቀየረ ተመልከቱ። ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፲፱እግዚአብሔር የክርስቶስን ቃል በመጠቀም ህዝቦችን ይመታል።