የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ተሰሎንቄ ፪


ጆ.ስ.ት.፣ ፪ ተሰሎንቄ ፪፥፪–፫፣ ፯–፱።፪ ተሰሎንቄ ፪፥፪–፱ ጋር አነጻፅሩ

ሰይጣን መውደቅን ወይም ክህደትን ጌታ ከመመለሱ በፊት ያመጣል።

ይህን ከእኛ በመንፈስም ይሁን በቃል እስካልተቀበላችሁ ድረስ፣ የክርስቶስ ቀን ደርሶአል ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ፣ በደብዳቤዎችም እንዳትደነግጡም።

ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ይመጣል፣ እና የዓመፅ ሰው እርሱም እንደ ጥፋት ልጅ ይገለጣልና።

የዓመፅ ሚሥጥር አሁን ይሠራልና፣ አሁንም ይህን የሚሰራው እርሱ ነው፣ እና ከመንገድ የሚወገድበት እስከሚሟላ ጊዜ ድረስ እንዲሰራም ክርስቶስ ፈቅዶለታል።

በዚያም ጊዜ ጌታ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፣ በመመለሻው ብርሀን የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል፤

አዎን፣ ጌታ፣ እንዲሁም ኢየሱስ፣ በሰይጣን ሙሉ ሀይል፣ እና ምልክቶች፣ እናም በሀሰተኛ ድንቆችም አሠራር በኩል ክህደት እስከሚመጣ ድረስ መምጫው አይደርስም።