የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፮


ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፮፥፩–፲።ዕብራውያን ፮፥፩–፲ ጋር አነጻፅሩ

የክርስቶስ ትምህርት መሰረታዊ መርሆች ወደ ፍጹምነት ይመራሉ።

ስለዚህ የክርስቶስ መሰረታዊ መርሆችን ሳንተው ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ ከሞተ ሥራ ንስሐ፣ እና በእግዚአብሔር እምነት መሠረትን ደግመን አንመሥርት።

ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርትም።

እግዚአብሔርም ቢፈቅድ ወደ ፍጻሜም እንሄዳለን።

አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን፣

መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን፣

በኋላም የካዱትን በንስሐ እንደገና እንዲታደሱም የማይቻል አድርጓል፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታል፣ እናም ያዋርዱትማልና።

ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ ለሚኖሩባትም የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፣ በእሳትም የምትጸዳበት ቀን ይመጣል።

እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያመጡ፣ ወደ እሳት ይጣላሉ፤ መጨረሻቸውም መቃጠል ነው።

ስለ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ምንም እንኳ እንዲሁ ብንናገር፥ አብልጦ የሚሻለውና ለመዳን የሚሆነው እንዲሆንላችሁ ተረድተናል።

ስለዚህ እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።