የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪


ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪፥፩።ያዕቆብ ፪፥፩ ጋር አነጻፅሩ

አባላት አንድን ሰው ከሌላ በላይ ከፍ አድርገው አይመልከቱ።

ወንድሞቼ ሆይ፥ ለሰው ፊት እያደላችሁ፣ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሊኖራችሁ አትችሉም።

ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪፥፲፬–፳፩።ያዕቆብ ፪፥፲፬–፳፪ ጋር አነጻፅሩ

እምነት ያለስራ የሞተ ነው እናም አያድንም።

፲፬ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ይህ ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?

፲፭ አዎን፣ አንድ ሰው፣ እምነት ያለሥራ እንዳለኝ አሳይሀለሁ ይል ይሆናል፣ ግን እኔም እምነትህን ያለስራዎችህ አሳየኝ፣ እና እምነቴን በሥራዎቼ አሳይሃለሁ እላለሁ።

፲፮ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም፣ በደኅና ሂዱ፣ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው፤ ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባይሰጣቸው፤ ለዚህ አይነት እምነትህ ምን ይጠቅማል?

፲፯ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።

፲፰ ስለዚህ፣ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን እና ሊያድንህ እንደማይችል ልታውቅ ትወዳለህን?

፲፱ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፤ ራስህን እንደነርሱ አድርገሀል፣ ጻድቅ ባለመሆን።

አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

፳፩ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፣ በሥራም እምነት ፍጹም እንደሆነ ትመለከታለህን?