የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬፥፳–፳፮።ማርቆስ ፲፬፥፳፪–፳፭ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን ለእርሱ ስጋ እና ደም መታሰቢያነት መሰረተ።

ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና አላቸው፣ እንካችሁ፣ ብሉ።

፳፩ እነሆ፣ ይህም ሰውነቴን ለማስታወስ ነው፤ ይህን በየጊዜው ስታደርጉም ከእናንተ ጋር የነበርኩበትን ሰአት ታስታውሳላችሁና።

፳፪ ጽዋንም አንሥቶ፣ እና ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።

፳፫ እና እንዲህም አላቸው፣ ይህም ለብዙዎች የሚፈስ፣ እና የምሰጣችሁ የአዲስ ኪዳን ደሜን ለማስታወስ ነው፤ ስለእኔ ለአለም ሁሉ ምስክር ትሰጣላችሁና።

፳፬ ይህን ስነስራአት በየጊዜው ስታደርጉም፣ ከእናንተ ጋር የነበርኩበትን እና ከጸዋው ከእናንተ ጋር የጠጣሁበትን፣ እንዲሁም የአግልግሎቴ የመጨረሻ ጊዜን፣ ይህን ሰአት ታስታውሳላችሁ።

፳፭ እውነት እላችኋለሁ፣ ስለዚህ ምስክር ስጡ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከእናንተ ጋር ደግሞ አልጠጣውምና።

፳፮ እና አሁን እነርሱም አዝነው ነበር፣ በእርሱም ላይ አለቀሱ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬፥፴፮–፴፰።ማርቆስ ፲፬፥፴፪–፴፬ ጋር አነጻፅሩ

በጌቴሴማኒ፣ አስራ ሁለቱም ቢሆኑ የኢየሱስን መሲህነት ሚና ሙሉ በሙሉ አልተረዱትም።

፴፮ ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ቦታ መጡ፣ ይህም አትክልት ስፍራ ነበር፤ እና ደቀመዛሙርቱ መደነቅ ጀመሩ፣ እና በጣምም ተጨነቁ፣ እና ይህ መሲህ እንደሆነ እያሰቡ በልቦቻቸውም ቅሬታ ተሰማቸው።

፴፯ እና ኢየሱስ ልቦቻቸውን በማወቅ ደቀ መዛሙርቱንም፣ ስጸልይ ሳለሁ፣ በዚህ ተቀመጡ አላቸው።

፴፰ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ እና ገሰጻቸው፣ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ትጉም አላቸው።