የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፫፥፳፩–፳፭።ማርቆስ ፫፥፳፰–፴ ጋር አነጻፅሩ

በመንፈስ ቅዱስ ላይ ከሚሳደቡት በስተቀር፣ ኢየሱስ ንስሀ የሚገቡ ኃጢያተኞችን በሙሉ ይሰርይላቸዋል።

፳፩ አንዳንዶችም ወደ እርሱ መጡ፣ እንዲህ በማለትም ከሰሱት፣ ራስህን የእግዚአብሔር ልጅ በማድረግ ለምን ኃጢያተኞችን ትቀበላለህ።

፳፪ ነገር ግን እርሱም መለሳቸው እናም እንዲህ አለ፣ እውነት እላችኋለሁ፥ ሰዎች ለሚሰሩት ኃጢአት ሁሉ፣ ንስሀ ሲገቡ፣ ይሰረይላቸዋል፤ ለሰው ልጆች ንስሀ ለመስበክ መጥቻለሁና።

፳፫ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ፣ ወደ እኔ ለሚመጡት፣ እና እኔ ሳደርግ ያዩትን ለሚያደርጉ ይሰረይላቸዋል።

፳፬ ነገር ግን የማይሰረይለት አንድ ኃጢያት አለ። በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ግን ለዘላለም አይሰረይለትም፤ ነገር ግን ከአለም ለመቆረጥ በአደጋ ላይ ነው የሚገኘው። እናም የዘላለም ፍርድን ይወርሳሉና።

፳፭ እርሱም እንዲህ ያላቸው እነርሱ ርኵስ መንፈስ አለበት ስለሚሉ ነበርና።