የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፩


ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፩፥፩–፭።መዝሙር ፲፩፥፩–፭ ጋር አነጻፅሩ

በመጨረሻው ቀናት ጻድቃን ወደ ጌታ ተራራ ይሸሻሉ። ጌታ ሲመጣም፣ ክፉውን ያጠፋል እናም ጻድቁን ያቤዛል።

አንተ በምትመጣበት በዚያ ቀን፣ አቤቱ ጌታ፤ እናም እምነቴን በአንተ ላይ እጥላለሁ። ለህዝብህም ትላለህ፣ ጆሮዬ ድምጽህን ሰምቷልና፤ ለእያንዳንዱም ነፍስ ትላለህ፣ ወደ ተራራዬ ሽሹ፤ እናም ጻድቃን ከወፍ ወጥመድ እንደተለቀቀች ወፍ ይሸሻሉ።

ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ፣ መሰረታቸውን ይደመስሱ ዘንድ።

ነገር ግን የክፉ መስረት ይደመሰሳልና፣ እናም ምን ለማድረግ ይችላሉ?

ጌታ ወደተቀደሰው መቅደሱ ሲመጣ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ በሰማይ ተቀምጦ፣ ዓይኖቹ ክፉዎችን ይመረምራሉ።

እነሆ አይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ፣ እናም ጻድቃንን ያድናል፣ እናም እነርሱም ይመረመራሉ። ጌታ ጻድቅን ይወዳል፣ ዓመፃን የወደዳት ኅጥእን ግን ነፍሱን ጠልቶአል።