የሚስዮን ጥሪዎች
ምዕራፍ 3፦የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አጥኑ እንዲሁም አስተምሩ።


“ምዕራፍ 3፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን አጥኑ እንዲሁም አስተምሩ” ወንጌሌን ስበኩ፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የማካፈል መመሪያ (2023 (እ.አ.አ))

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አጥኑ እንዲሁም አስተምሩ” ወንጌሌን ስበኩ

ምስል
የክርስቶስ ጥምቀት፣ በጆሴፍ ብሪኬይ

ምዕራፍ 3

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አጥኑ እንዲሁም አስተምሩ።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉት ትምህርቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል አስፈላጊ ትምህርት፣ መርሆች እና ትእዛዛትን ይይዛሉ። እነዚህ ትምህርቶች ህያው ነብያት እና ሃዋርያት እንድትማሩ እና እንድታስተምሩ ያዘዟቸው ናቸው። ሌሎች የክርስቶስን ትምህርት በግልፅ እንዲረዱ ለመርዳት እዚህ ቀርበዋል።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያለው የመጀመሪያው ክፍል የጥምቀት ግብዣ ነው። የተቀረው ምዕራፉ የሚከተሉትን አራት ትምህርቶች የያዘ ነው:-

በእያንዳንዱ ትምህርት ቅዱሳት መጻህፍትን አጥኑ እንዲሁም ለትምህርቱ ትልቅ ዋጋ ስጡ። ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ ስለምታጠኑት እውነት መንፈስ ይመሰክራል። ሌሎች የእውነት ምሥክርነት እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ማለት እንዳለባችሁ እንድታውቁ ይረዳል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥85 ተመልከቱ።)

ሰዎች አዳኙ እንዲያደርጉ የጋበዛቸውን ሲያደርጉ እርሱን ይበልጥ እያወቁ ይሄዳሉ። በእያንዳንዱ ትምህርት ግብዣ አቅርቡ እንዲሁም ሰዎች ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ አግዟቸው። ሰዎች ቃል ኪዳኖችን ሲጠብቁ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መኖር ይጀምራሉ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ ይዘጋጃሉ።

ሁሉንም ትምህርቶች ከጥምቀት በፊትና በኋላ አስተምሩ። በሁለቱም ጊዜያት ትምህርቶቹን በማስተማር ረገድ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ቀዳማዊ ይሆናሉ። የቅርንጫፋችሁ ሚስዮናውያን ወይም ሌሎች አባላት ሲችሉ ይሳተፋሉ። በማስተማር ሂደት ውስጥ አባላትን ስለማካተት መረጃን ለማግኘት ምዕራፍ 10 እና 13ን ተመልከቱ።

ለማስተማር መዘጋጀት

ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ፣ በወንጌሌን ስበኩ መተግበሪያ ውስጥ ያለውን የእያንዳንዱን ግለሠብ መረጃ ገምግሙ። በምታስተምሩት ግለሠብ ፍላጎት መሰረት የትምህርት እቅድ አዘጋጁ። በማስተማር ጉብኝታችሁ ወቅት እሱ ወይም እሷ ምን ማወቅ እና ምን ሊሰማቸው እንደሚገባ አስቡ። ለመዘጋጀት እና ለማቀድ ጊዜ ስትወስዱ መንፈሱ ጥረቶቻችሁን ያጎላል።

ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ እናንተ እና የሚስዮን ጓደኛችሁ በጸሎት ልታስቡባቸው የሚገቡ አንዳንድ ጥያቄዎች እዚህ ይገኛሉ።

  • ግለሰቡ በክርስቶስ ላይ እምነት እንዲያዳብርና እንዲያድግ ለመርዳት ምን ግብዣ እናቅርብ? ግብዣዎች ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ እና “[የማዳኑን ስልጣን]” (ሄለማን 5፡11) እንዲለማመዱ የምትረዱበት መንገድ ነው። የግለሰቡን እድገት፣ ሁኔታ እና ፍላጎቶች ግምት ውስጥ አስገቡ። ከዚያም በማስተማር እቅዳችሁ ውስጥ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ግብዣዎችን አካትቱ።

  • ግለሰቡ እንዲገባ የጋበዝነውን ቃል ኪዳን እንዲጠብቅ የሚረዳው የትኛው ትምህርት እና መርህ ነው? ሰዎች ቃላቸውን መጠበቅ ለእነሱ እና ለጌታ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ እንዲገነዘቡ የሚረዳቸው የትኛው ትምህርት እና መርሆ እንደሆነ በጸሎት ለዩ።

  • ግለሰቡ ትምህርቱን እንዲማር እንዴት እንርዳው? ትምህርቱን ለማስተማር ለመዘጋጀት፣ ትምህርት 1–4ን በመጠቀም የምታስተምሩትን አደራጁና አጠቃሉ። ግለሰቡ የምታስተምሩትን ነገር እንዲገነዘብ የሚረዱ ጥያቄዎችን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን፣ ምሳሌዎችን እና ምቹ ሚዲያዎችን ለዩ። የማስተማር ሂደታችሁን እንዴት ማሻሻል እንደምትችሉ መረጃ ለማግኘት ምዕራፍ 10ን ተመልከቱ።

  • እግዚአብሄር ቃል ኪዳኖችን ለሚቀበሉ እና ለሚፈጽሙ ምን በረከቶችን ቃል ገብቷል? ትምህርቱን ስታጠኑ፣ እግዚአብሔር ቃል የገባቸውን በረከቶች ለዩ። ስታስተምሩ በረከቶችን ቃል ግቡ እንዲሁም ስለእነሱ ምስክርነት ስጡ።

  • የትኞቹ አባላት መሳተፍ ይችላሉ? በሳምንታዊው የማስተባበር ስብሰባ፣ ግለሰቡን ለማስተማር እና ለመደገፍ የትኞቹ አባላት ሊረዷችሁ እንደሚችሉ ወስኑ። ከትምህርቱ በፊት ስለተሳትፏቸው ተወያዩ። ምዕራፍ 10ን ተመልከቱ።

  • ከሄድን በኋላ ሰዎች የገቡትን ቃል ኪዳን እንዲጠብቁ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን? ሰዎች ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ ለማገዝ አጭር በሆነ ዕለታዊ ግንኙነት ተከታተሉ። የምታስተምሯቸው ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ ለመርዳት አባላትን የምታካትቱባቸውን መንገዶች ፈልጉ። ይህ ግንኙነት ከመፅሐፈ ሞርሞን ወይም ከሌሎች ቅዱሳት መጻህፍት አንድን ምዕራፍ ማንበብን ሊያካትት ይችላል። አንድ ሰው ከዚህ ቀደም የገባውን ቃል ካልጠበቀ፣ ሌላ ቃል ከማስገባታችሁ በፊት በዚህኛው መርዳት የተሻለ ሊሆን ይችላል። ምዕራፍ 11ን ተመልከቱ።

  • በሚቀጥለው ጊዜ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? ከእያንዳንዱ የማስተማር ሁኔታ በኋላ የምታስተምሯቸውን ሰዎች ልምድ ገምግሙ። በክርስቶስ ላይ ያላቸው እምነት እያደገ ነው? መንፈሱ እየተሰማቸው ነው? ንስሐ እና ቃል ኪዳን እየገቡ እንዲሁም እየጠበቁ ነው? እየጸለዩ፣ መፅሐፈ ሞርሞንን እያጠኑ፣ እና ቤተክርስቲያን እየሄዱ ነው? እነሱን ለመርዳት እቅድ አውጡ።

መንፈስ እንደመራችሁ ከልባችሁ አስተምሩ

ለሁሉም ሽማግሌዎች እና እህቶች በተናገሩበት ጊዜ፣ የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን እንዲህ ብለዋል፡-

“ዓላማችን ዳግም የተመለሰውን የወንጌል መልእክት መንፈስ ሚስዮናውያንንም ሆነ የሚማሩትን እንዲመራ በሚያስችል መንገድ ማስተማር ነው። የምንባቦችን ዋና ግንዛቤ መማር አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን እነዚህን በተገመገመ የትምህርት አቀራረብ ማስተማር አይገባም። ሚስዮናዊው በመንፈስ በመነሳሳት የራሱን ቃላት ለመጠቀም ነፃነት ሊሰማው ይገባል። የተሸመደደ ትምህርት ማቅረብ አይገባውም፣ ነገር ግን ከልቡ በእራሱ ቃል ይናገር። ፟[ግለሰቡን] በሚያነሳሳ እና ፍላጎቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ለመስጠት የተነሳሳውን በመስጠት፣ የትምህርቱን ቅደም ተከተል መቀየር ይችላል። ከራሱ እርግጠኝነት ተነስቶና በራሱ አንደበት በመናገር፣ ስለ ትምህርቱ እውነት መመስከር አለበት።”

ምስል
ሚስዮናውያን አንድን ሰው ሲያገኙት

እንደ ግለሰባዊ ፍላጎቶች አስተምሩ እንዲሁም ጋብዙ

ሰዎችን ለጥምቀት እና ለመረጋገጥ በሙሉ እንዲዘጋጁ ለመርዳት ከሁሉም በላይ ይጠቅማል ብላችሁ በምታስቡበት በማንኛውም መንገድ ትምህርቶችን ለማስተማር ትችላላችሁ። ምን እንደምታስተምሩ፣ መቼ እንደምታስተምሩ፣ ለእዚህም ምን ያህል ጊዜ እንደምትሰጡ የሚወሰነው በምታስተምሩት ግለሠብ ፍላጎት እና በመንፈስ ምሪት ነው። ለምሳሌ፣ ለክርስትና አዲስ የሆኑ ሰዎችን ስታስተምሩ ከሰማይ አባት ጋር የበለጠ ግንኙነት እንዲያዳብሩ እና የእሱን እቅድ እንዲረዱ በመርዳት ልትጀምሩ ትችላላችሁ (በምዕራፍ 10 ላይ ያለውን “ለክርስትና አዲስ የሆኑ ሰዎችን ማስተማር” የሚለውን በምዕራፍ 10 ላይ ተመልከቱ)።

መቼ እና ምን አይነት ግብዣ እንደምትጋብዙ መንፈስ እንዲመራችሁ ፍቀዱ። በትክክለኛው ጊዜ የተደረገው ግብዣ ሰዎች እምነታቸውን የሚገነቡ ነገሮችን እንዲያደርጉ ሊያነሳሳቸው ይችላል። እነዚህ ድርጊቶች ወደ ታላቅ የልብ ለውጥ ይመራሉ (ሞዛያ 5፥2አልማ 5፥12–14 ተመልከቱ)።

ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር ትምህርቶችን አስተምሩ። የማስተማር ጉብኝት ከ30 ደቂቃዎች በላይ መሆን የለበትም፣ አንድን ግለሠብ በ5 ደቂቃዎች ውስጥ እንኳን ማስተማር ትችላላችሁ።

አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ትምህርት ውስጥ ያሉ መርሆዎችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ መገናኘት ሊያስፈልጋችሁ ይችላል። በተደጋጋሚ አጫጭር እና ትንሽ ትምህርቶችን ስታስተምሩ ሰዎች መልእክታችሁን በተሻለ ሁኔታ ይረዳሉ።

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት

ምን እንድታስተምሩ መመሪያ ተሰጣችሁ?

በትምህርቶቹ ውስጥ ያለን አስተምህሮ ማጥናት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?