ምዕራፍ ፲
አይሁድ አምላካቸውን እንደሚሰቅሉ ያዕቆብ ገለጸ—በእርሱም ማመን እስኪጀምሩም ድረስ ይበተናሉ—አሜሪካ ንጉስ የማይገዛባት የነፃ ምድር ትሆናለች— ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቁ፣ እናም በፀጋው መዳንን አግኙ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ እኔ ያዕቆብ ስለዚህ ስለተናገርኩት ስለተቀደሰው ሀቅርንጫፍ ደግሜ እናገራችኋለሁ።
፪ እነሆም እኛ የያዝናቸው ሀቃልኪዳኖች ለስጋ የተገቡ ቃልኪዳኖች ናቸው፤ ስለዚህ፣ ብዙዎች ልጆቻችን እምነት በማጣታቸው የተነሳ እንደሚጠፉ ለእኔ ቢገለፀልኝም፣ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር ለብዙዎች ምህረትን ያወርዳል፤ እና ልጆቻችን የመድኃኒታቸውን እውነተኛ እውቀት ወደሚሰጣቸው ለመምጣት ደግመው ይመለሳሉ።
፫ ስለዚህ፣ እንዳልኳችሁ፣ ክርስቶስ—ትናንት ማታ ሀመልአኩ ስሙ ይህ እንደሚሆን ነግሮኛልና—ከአይሁዶች፣ በዓለም ከሌሎች በላይ ኃጢአተኛ በሆኑት፣ መካከል ለይመጣል፤ እነርሱም ሐይሰቅሉታል—እንዲህ መሆኑ ለአምላካችን አስፈላጊ ነበርና፣ እናም በምድር ላይ የራሳቸውን መአምላክ ሠየሚሰቅል ሌላ ህዝብ የለም።
፬ በሌሎች ሕዝቦች መካከል ታላቅ ሀተዓምራት ከተፈፀሙ ንስሀ ይገባሉ፣ እናም አምላካቸው እንደሆነ ያውቃሉ።
፭ ነገር ግን በኃጢያትና ሀበካህናት ተንኮል የተነሳ በኢየሩሳሌም ያሉት እርሱ እስኪገደል ድረስ እንኳ በእርሱ ላይ አንገተ ደንዳና ይሆናሉ።
፮ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተነሳ ጥፋት፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ እና ደም መፍሰስ በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ እናም የማይጠፉት ደግሞ በህዝቦች ሁሉ መካከል ሀይበተናሉ።
፯ ነገር ግን እነሆ፣ ሀጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል—እኔ ክርስቶስ እንደሆንኩ፣ የሚያምኑበት ቀን ለበመጣ ጊዜ፣ ያኔ እኔ በስጋ ወደ ርስታቸው ምድር እመልሳቸው ዘንድ ከአባቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
፰ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ከረጅም ዘመን ብተናቸው፣ ሀከባህር ደሴቶችና፣ ከምድር ከአራቱም ማዕዘናት ለይሰበሰባሉ፤ እና አህዛቦች እነርሱን ወደ ርስት ምድራቸው ሐበመውሰዳቸው የአህዛብ ሀገሮች በዐይኖቼ ፊት ታላቅ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር።
፱ ሀአዎን፣ የአህዛብ ንጉሶች ለእነርሱ እንደ አባት ይሆኑላቸዋል፣ እናም ንግስቶቻቸውም እንደ እናቶች ይሆኑላቸዋል፤ ስለዚህ፣ ጌታ ለአህዛብ የገባው ለቃል ኪዳን ታላቅ ነው፣ እርሱ ተናግሯታልና፣ እናም ማን ይቃወማል?
፲ ነገር ግን እነሆ፣ ይህ ምድር፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የርስታችሁ ምድር ይሆናል፣ እና ሀአህዛብም በምድሩ ላይ የተባረኩ ይሆናሉ።
፲፩ እናም ይህ ምድር ለአህዛብ ሀየነፃነት ምድር ይሆናል፣ እናም በምድሪቷም በአህዛብ ላይ የሚነሱ ለንጉሶች አይኖሩም።
፲፪ እናም እኔ ይህንን ምድር ከሌሎች ሀገሮች አጠናክራቸዋለሁ።
፲፫ እናም ፅዮንን ሀየሚዋጋ ለይጠፋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
፲፬ በእኔ ላይ ሌላ ንጉስ የሚያስነሳ ይጠፋልና፣ ምክንያቱም እኔ ጌታ የሰማይ ሀንጉስ፣ ንጉሳቸው እሆንላቸዋለሁ፣ እናም ድምፄን ለሚሰሙ ሁሉ ለዘለዓለም ለብርሃን እሆንላቸዋለሁ።
፲፭ ስለዚህ፣ በዚህ የተነሳ፣ ለሰው ልጆች የገባኋቸው ሀቃልኪዳኖች ይፈፀሙ ዘንድ፣ እነርሱ በስጋ እያሉ አደርግላቸው ዘንድ፣ ለየጭለማ ሐየሚስጥር ስራዎችንና፣ ግድያዎችን፣ እናም እርኩሰቶችን አጠፋ ዘንድ ያስፈልገኛል።
፲፮ ስለዚህ፣ አይሁድም ሆነ አህዛብ፣ ባርያም ሆነ ነፃ፣ ወንድም ሆነ ሴት፣ ሀፅዮንን የሚዋጋ ይጠፋል፤ የምድር ሁሉ ጋለሞታዎች ለእነዚህ ናቸውና፤ የእኔ ሐያልሆኑት መይቃወሙኛልና ይላል አምላካችን።
፲፯ ለሰው ልጆች በስጋቸው ላደርግላቸው የገባሁትን ቃል ኪዳን ሀእፈፅማለሁና—
፲፰ ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ አምላካችን እንዲህ ይላል፣ ዘሮቻችሁን ሀበአህዛብ እጅ አሰቃያለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ እነርሱ እንደአባት ይሆኑላቸው ዘንድ የአህዛብን ልብ አራራለሁ፤ ስለዚህ፣ አህዛብ ለይባረካሉ እናም ከእስራኤል ቤትም ውስጥ ሐይቆጠራሉ።
፲፱ ስለዚህ፣ ለዘሮችህና ከዘሮችህ መሀል ለሚቆጠሩት ይህችን ምድር የርስት ምድራቸው ለዘለዓለም ትሆን ዘንድ ሀእቀባታለሁ፤ እግዚአብሔርም ለእኔ ከሌሎች ምድሮች ሁሉ በላይ የተመረጠች ምድር ናት አለኝ፤ ስለዚህ፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እኔን እንዲያመልኩ እፈልጋለሁይላል እግዚአብሔር።
፳ እና አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ መሀሪው እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ታላቅ እውቀትን ስለሰጠን፣ እናስታውሰው፣ እናም ኃጢአታችንን እንተው፣ ተስፋም አንቁረጥ፣ እኛ አልተጣልንምና፤ ይሁን እንጂ፣ ከርስታችን ምድር ሀእንድንወጣ ተደርገናል፤ ነገር ግን ለወደተሻለ ምድር ተመርተናል፣ ጌታ ባህሩን ሐመንገዳችን አድርጎልናል፣ እና መበባህር ደሴት ላይ ነን።
፳፩ ነገር ግን ሀበባህር ደሴቶች ላይ ላሉት የጌታ ቃል ኪዳን ታላቅ ነው፣ ስለዚህ ደሴቶች ስለሚል፣ ከዚህ የበለጡ ሌሎችም አሉ ማለት ነው፤ እናም እነርሱ ወንድሞቻችን የሚኖሩባቸው ናቸው።
፳፪ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር እንደፈቃዱና እንደምኞቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከእስራኤል ቤት ህዝቡን ሀአውጥቷል። እናም አሁን እነሆ፣ ጌታ የተገነጠሉትን ሁሉ ያስታውሳል፣ ስለዚህ እኛንም ደግሞ ያስታውሳል።
፳፫ ስለዚህ፣ ልባችሁን አስደስቱ፣ እናም በራሳችሁ ሀለመስራት፣ ዘለዓለማዊውን ሞት ወይም የዘለዓለማዊውን ህይወት መንገድ እራሳችሁ ለለመምረጥ ሐነጻነት እንዳላችሁ አስታውሱ።
፳፬ ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንጂ ከዲያብሎስና ከስጋ ፈቃድጋር አታስታርቁ፤ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቃችሁ በኋላ ሀየምትድኑት በእግዚአብሔር ለፀጋ ውስጥና በእርሱ በኩል ብቻ እንደሆነ አስታውሱ።
፳፭ ስለዚህ፣ ወደዘለዓለም የእግዚአብሔር መንግስት እንድትገቡና፣ በመለኮታዊ ፀጋም እንድታመሰግኑት ዘንድ፣ እግዚአብሔር በትንሣኤ ኃይል ከሞት፣ እናም ደግሞ ከዘለዓለማዊው ሞት ሀበኃጢያት ክፍያ ያንሳችሁ። አሜን።