ክፍል ፫
ሐምሌ ፲፰፻፳፰ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቬንያ ውስጥ መፅሐፈ ሌሒ ተብሎ ይጠራ የነበረውን የተተረጎመበት ፻፲፮ የመፅሐፈ ሞርሞን ገጾች የመጀመሪያ ክፍል መጥፋት በተመለከተ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ በቸልተኛነት እነዚህን ገጾች ለጥቂት ጊዜ የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ጸሐፊ በመሆን ያገለግል ለነበረው ማርቲን ሀሪስ ኣሳልፎ ሰጠ። ራዕዩ በኡሪምና ቱሚም አማካይነት የተሰጠ ነው። (ክፍል ፲ን ተመልክቱ።)
፩–፬፣ የጌታ ጎዳና አንድ እና ዘለአለማዊ ዙሪያ ነው፤ ፭–፲፭፣ ጆሴፍ ስሚዝ ንስሀ መግባት ወይም የመተርጎም ስጦታውን ማጣት አለበት፤ ፲፮–፳፣ መፅሐፈ ሞርሞን የሌሒ ዘሮችን ለማዳን ይመጣል።
፩ የእግዚአብሔር ሀስራ፤ ጥበብ፤ እና ዓላማ ሊከሸፍም ሆነ ከንቱ ሊሆን አይችልም።
፪ ሀእግዚአብሔር በተጣመመ መንገድ አይጓዝም፣ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አይዞርም፣ የተናገረውንም አይለውጥም፣ ስለዚህ መንገዱ ቀጥተኛ ነው፣ ለጎዳናውም አንድ እና ዘለአለማዊ ዙሪያ ነው።
፫ አስታውሱ፣ አስታውሱ የሚሰናከለው የሰው ስራ እንጂ የእግዚአብሔር ሀስራ አይደለም፤
፬ ሰው ብዙ ራዕይ ቢቀበል፣ እናም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሀይል ቢኖረውም፣ ነገር ግን በራሱ ጥንካሬ ሀቢታበይ፣ የእግዚአብሔርን ለምክር ከንቱ ቢያደርግ እናም ሐበስጋው እና በራሱ ፈቃድ ቢመራ፣ ውድቀትንና የእግዚአብሔርን መበቀል በራሱ ላይ ማምጣት አለበት።
፭ እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች ተሰጥተውሀል፣ ነገር ግን የተሰጡህ ትእዛዛቶች እንዴት የጠበቁ ነበሩ፤ እናም ካልተላለፍካቸው፣ ለአንተ የተገባልህን የተስፋ ቃላት እንዲሁ አስታውስ።
፮ እናም እነሆ፣ ምን ያህል ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና ህግጋት ሀተላልፈሀል፤ እናም በሰዎችም ለሀሳብ ምን ያህል ሄደሀል።
፯ ስለሆነም እነሆ ሰውን ከእግዚአብሔር አስበልጠህ ሀፍርሀት አልነበረብህም። ምንም እንኳን ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክር ከንቱ ቢያደርጉም እናም ቃሉንም ለቢንቁ—
፰ ነገር ግን ታማኝ መሆን ነበረብህ፤ እናም እጁን ዘርግቶ ሀከጠላትም ክፉ ለፍላፃ ይደግፍህ ነበር፤ እናም ሐበመከራህ ጊዜ ሁሉ ከአንተ ጋር ይገኝ በነበር።
፱ እነሆ አንተ ጆሴፍ ነህ፣ እናም የጌታን ስራ እንድትሰራ ተመርጠሀል፣ ነገር ግን በመተላለፍህ ምክንያት ካልተጠነቀቅህ ትወድቃለህ።
፲ ነገር ግን አስታውስ፤ እግዚአብሔር መሀሪ ነው፤ ከሰጠሁህ ትእዛዛት ተጻራሪ የሆነውን ለሰራህበት ንስሐ ግባ፣ እናም አሁን የተመረጥህ ነህ፣ እናም ለስራው ዳግም ተጠርተሀል፤
፲፩ ይህን ካላደረግህ በቀር፣ ትተዋለህ እናም እንደሌሎችም ሰዎች ትሆናለህ፣ እና ስጦታም አይኖርህም።
፲፪ እናም እግዚአብሔር የሰጥህን ሀየመተርጎም መንፈሣዊ ብርሀንና ሀይል አሳልፈህ በሰጠህ ጊዜ፣ የተቀደሰውን ነገር በኃጢአተኛ ለሰው እጅ ውስጥ እንዲገባ አሳልፈህ ሰጥተሀል፣
፲፫ የእግዚአብሔርንም ምክር ከንቱ ላደረገ ሰው፣ እና በእግዚአብሔር ፊት የተደረገውን በጣም የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን ላፈረሰና፣ በራሱ ፍርድ ላይ ለሚመካና በራሱም ጥበብ ሀለሚታበይ ሰው አሳልፈህ ሰጥተሀል።
፲፬ እናም በዚህ መክንያት ነው ለጊዜው ስጦታህን ያጣኽው—
፲፭ ምክንያቱም ሀየመሪህን ምክር ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዲረገጥ አድርገኃልና።
፲፮ ሆኖም፣ ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል፣ ሀየአዳኝ እውቀት ወደ አለም በአይሁዶች ለምስክርነት እንደመጣ እንዲሁ፣ የአዳኝ ሐእውቀት ወደ ህዝቤ ይመጣል—
፲፯ እንዲሁም ሀለኔፋውያን፣ እናም ለያዕቆባውያን እናም ለዮሴፋውያን እናም ለዞራማውያን በአባቶቻቸው ምስክርነት ይመጣል—
፲፰ እናም ይህ ሀምስክርነት በአባቶቻቸው ክፋት ምክንያት እምነት በማጣት ለወደመነመኑት፣ ጌታ ወንድሞቻቸው ኔፋውያንን፣ በኃጢአታቸው እና በእርኩስነታቸው የተነሳ፣ ሐእንዲጠፉ ወዳደረጋቸው፣ ወደ መላማናውያን እና ልሙኤላውያን እና እስማኤላውያን እውቀት ይመጣል።
፲፱ በዚህ ሀዓላማ ምክንያት ነው ጽሁፎቹን የያዘው ይህ ለሰሌዳ የተጠበቀው—ጌታ ለህዝቦቹ የገባው ሐየተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ፤
፳ እናም ሀላማናውያን ወደ አባቶቻቸው እውቀት ይመጡ ዘንድ፣ እናም የጌታን የተስፋ ቃል ያውቁ ዘንድ፣ እናም ወንጌልንም ለያምኑ ዘንድ፣ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ስራ ሐይመኩ ዘንድ፣ እናም በእምነት በስሙ መይከብሩ ዘንድ፣ እናም በንሰሀቸው ይድኑ ዘንድ ነው ሰሌዳው የተጠበቀው። አሜን።