የኔፊ ሁለተኛ መጽሐፍ
የሌሂ የአሟሟት ታሪክ። የኔፊ ወንድሞች በእርሱ ላይ አመጹ። ጌታ ኔፊን ወደ ምድረበዳ እንዲሄድ አስጠነቀቀው። በምድረበዳ የነበረው ጉዞና የሌሎች ነገሮች መዝገብ።
ምዕራፍ ፩
ሌሂ ስለነፃነቷ ምድር ተነበየ—የእስራኤልን ቅዱስ የሚቃወሙ ከሆነ ዘሮቹ ይበተናሉ እናም ይጠፋሉ—ወንዶች ልጆቹን የፅድቅን የጦር ዕቃ እንዲለብሱ አበረታታቸው። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እና እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ፣ ወንድሞቼን ማስተማሬን ከጨረስኩ በኋላ ሀአባታችን ሌሂም ደግሞ፣ ብዙ ነገሮችን ተናገራቸው፣ እናም ጌታ እነርሱን ከኢየሩሳሌም ምድር በማውጣት ምን ያህል ታላቅ ነገር እንዳደረገላቸው አስታወሳቸው።
፪ እናም በባህር ላይ በነበሩ ጊዜ ስለነበራቸው ሀአመፅና፣ ደግሞ በባህር ውስጥ እንዳይሰጥሙ በማድረግ እግዚአብሔር ስላሳየው ምህረት ነገራቸው።
፫ እናም ደግሞ ስላገኙት የቃል ኪዳን ምድር በተመለከተ፣ ጌታ እኛን ከኢየሩሳሌም እንድንወጣ በማስጠንቀቅ እንዴት መሀሪ እንደነበር ነገራቸው።
፬ እነሆም፣ አለ እርሱ፥ ሀራዕይን አይቻለሁ፣ በእርሱም ለኢየሩሳሌም እንደጠፋችም አውቃለሁ፤ እኛም በኢየሩሳሌም ቀርተን ቢሆን ኖሮ እኛም ደግሞ ሐእንጠፋ ነበር።
፭ ነገር ግን፣ መከራችንን በሙሉ በመቋቋም ከምድር ሁሉ ሀየተመረጠችውን ለየቃል ኪዳን ምድር፣ ጌታ አምላክ ለእኔ ለዘሮቼ ርስት እንድትሆን ቃል የገባልኝን ምድር አግኝተናል አለ። አዎን፣ ጌታ ይህንን ምድር ለእኔና ለልጆቼ እናም ደግሞ ከሌሎች ምድር በጌታ እጅ ተመርተው ለሚወጡት በሙሉ ለዘለዓለም ሐቃል ኪዳን ገብቷል።
፮ ስለዚህ፣ እኔ፣ ሌሂ፣ በውስጤ ባለው የመንፈስ ሥራ መሠረት፣ በጌታ እጅ ተመርተው ካልሆነ በቀር ወደ እዚህች ምድር ሀማንም እንደማይመጣ እተነበያልሁ።
፯ ስለዚህ ይህች ሀምድር እርሱ ለሚያመጣው ተቀድሳለች። እናም በሰጣቸው ትዕዛዛት መሰረት እርሱን የሚያገለግሉት ከሆነ ለእነርሱ ለየነፃነት ምድር ትሆናለች፤ ስለዚህ፣ መቼም ቢሆን በምርኮ አይያዙም፤ ከተያዙ ግን በኃጢያት ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ኃጢያት ከተስፋፋ ምድሪቷ በእነርሱ የተነሳ ሐየተረገመች ትሆናለች፣ ነገር ግን ለፃድቃን ለዘለዓለም የተባረከች ትሆናለች።
፰ እናም እነሆ፣ ይህች ምድር በሌሎች ሀገሮች ሳትታወቅ ትቆይ ዘንድ ይህ ጥበብ ነው፤ እነሆም፣ ብዙ ሀገሮችም ምድሪቷን ይሞሏታል፣ ለውርስ የሚሆን ቦታ እንኳን አይኖርም።
፱ ስለዚህ፣ እኔ፣ ሌሂ፣ ጌታ አምላክ ከኢየሩሳሌም የሚያወጣቸው በሙሉ ትዕዛዛቱን እስከጠበቁ ሀድረስ፣ በዚች ምድር ላይ ለእንደሚበለፅጉ ቃል ኪዳንን ተቀበልኩ፤ እናም ከሌሎች ሀገሮች ይጠበቃሉ፣ ይህችንም ምድር በራሳቸው ይይዟታል። የእርሱን ትዕዛዛት ሐየሚጠብቁ ከሆኑም በዚች ምድር ላይ የተባረኩ ይሆናሉ፣ የሚያስቸግራቸው ወይም የርስት ምድራቸውን የሚወስድባቸውም ማንም አይኖርም፤ እናም ለዘለዓለም በደህንነት ይኖራሉ።
፲ ነገር ግን እነሆ፣ ታላላቅ በረከቶችን ከጌታ እጅ ከተቀበሉ በኋላ ባለማመን የሚመነምኑበት ጊዜ ሲመጣ—የምድርንና የሁሉን ሰዎች አፈጣጠር እያወቁ፣ ከምድር መፈጠር ጀምሮ የጌታን ታላቅና ድንቅ ስራዎች እያወቁ፣ ሁሉን ነገር በእምነት ለማድረግ ኃይል ከተሰጣቸው በኋላ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሁሉንም ትዕዛዛት ኖሯቸው፣ እናም በእርሱ በማያልቅ ደግነት ወደዚህች የተከበረች የቃል ኪዳን ምድር ከመጡ በኋላ—እነሆ፣ እኔ እላለሁ፣ እነርሱ የእስራኤሉን ቅዱስ፣ እውነተኛውን ሀመሲህ፣ ቤዛቸውንና አምላካቸውን የሚክዱበት ቀን ከመጣ፣ እነሆ፣ ትክክለኛ የሆነው የእርሱ ፍርድ በላያቸው ላይ ይመጣባቸዋል።
፲፩ አዎን፣ ሀሌሎች ሀገሮችን በእነርሱ ላይ ያመጣባቸዋል፣ ለእነርሱም ኃይልን ይሰጣቸዋል፣ እናም የርስት ምድራቸውንም ይወሰድባቸዋል፣ እንዲሁም ለእንዲበተኑና እንዲጠፉ ያደርጋል።
፲፪ አዎን፣ አንዱ ትውልድ ወደሌላው ሲተላለፍ ሀደም መፍሰስ ይኖራል፣ እናም በእነርሱ መካከል ታላቅ ቅጣት ይሆናል፤ ስለዚህ፣ ልጆቼ ሆይ፣ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፤ አዎን፣ ቃላቶቼን እንድታዳምጡ እፈልጋለሁ።
፲፫ አቤቱ እናንት እንድትነቁ፤ ከከባድ እንቅልፍ እንድትነቁ፣ አዎን፣ ሀከሲኦል እንቅልፍ እንኳን እንድትነቁ፣ እናም የታሰራችሁበትን የሰው ልጆችን ወደዘለአለማዊ የጉስቁልና የሀዘን ለጥልቅ በምርኮ የሚወስደውን ሐሰንሰለት አውልቁ።
፲፬ ንቁ! ከትቢያም ላይ ተነሱ፣ እናም ማንም ተጓዥ ሊመለስበት ወደ ማይችለው ወደ ቀዝቃዛውና ወደ ዝምተኛው ሀመቃብር በቅርቡ ሊሄዱ ያሉትን የሚንቀጠቀጡትን ለየወላጃችሁን ቃላት አድምጡ፤ እኔም በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ምድር ሁሉ ሐወደሚሄዱበት እሄዳለሁ።
፲፭ ነገር ግን እነሆ፣ ጌታ ነፍሴን ከሲኦል ሀአድኗታል፤ እኔ የእርሱን ክብር አይቻለሁ፣ እናም እኔ በእርሱ በዘለዓለማዊው ለፍቅር ሐክንዶች ተከብቤአለሁ።
፲፮ እናም የጌታን ሀስርዓቶችና ፍርዶች መጠበቅን ታስታውሱ ዘንድ እፈልጋለሁ፤ እነሆ፣ ይህ ከመጀመሪያው ጀምሮ ነፍሴን የሚያስጨንቅ ነው።
፲፯ ልቤ ከጊዜ ወደጊዜ በኃዘን ተጨንቋል፣ ምክንያቱም በልባችሁ ጠጣርነት የተነሳ ትለዩና ለዘለዓለም ሀትጠፉ ዘንድ ጌታ አምላካችሁ በሙሉ ለቁጣው እንዳይመጣ እኔ ፈርቻለሁ፤
፲፰ ወይም፣ ሀለብዙ ትውልድ እርግማን በላያችሁ ላይ ይመጣባችኋል፣ እናም በሰይፉና በርሃብ ትጎበኛላችሁ፣ እንዲሁም ትጠላላችሁ፣ እናም ለእንደዲያብሎስ ፈቃድ በምርኮ ትመራላችሁ ብዬ ፈርቼ ነበርና።
፲፱ አቤቱ፣ ልጆቼ ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ እንዳይመጡባችሁ፣ ነገር ግን እናንተ በጌታ የተመረጣችሁና ሀየተወደዳችሁ ህዝቦች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። ነገር ግን እነሆ፣ የእርሱ ፈቃድ ይሁን፤ የእርሱ ለመንገዶች ለዘለዓለም ፅድቅ ናቸውና።
፳ እናም እርሱ እንዲህ አለ፥ ሀትዕዛዛቴን እስከጠበቃችሁ ለድረስ በምድሪቱ ሐትበለፅጋላችሁ፤ ነገር ግን ትዕዛዛቴን ባልጠበቃችሁ ጊዜ ሁሉ ከእኔ ዘንድ ትለያላቸሁ።
፳፩ እናም አሁን ነፍሴ በእናንተ ደስ እንዲላትና፣ ልቤ ይህንን ዓለም በእናንተ ምክንያት በደስታ እንድትለይ፣ እኔ በሀዘንና በመከራ ወደ መቃብር እንዳልሄድ፣ ልጆቼ ሆይ ከትቢያ ላይ ተነሱና፣ ሀሰዎች ሁኑ፣ እናም በምርኮ እንዳትያዙ ለበአንድ ሀሳብና በአንድ ልብ ሁኑ፣ በሁሉ ነገሮች ተስማሙ፤
፳፪ በከባድ እርግማን እንዳትረገሙ፤ እንደዚሁም ደግሞ ሀየትክክለኛውን አምላክ ቁጣ እስከሚያጠፋችሁ ድረስ፣ አዎን፣ ዘለዓለማዊ የስጋም የነፍስም ጥፋት በላያችሁ ላይ እንዳታመጡ።
፳፫ ንቁ፣ ልጆቼ፣ የፅድቅን ሀየጦር ዕቃ ልበሱ። የታሰራችሁበትን ሰንሰለት አውልቁ፣ ከጨለማም ውጡ፣ ከትቢያም ተነሱ።
፳፬ ራዕዮቹ ታላቅ በነበሩትና ከኢየሩሳሌም ከወጣን ጀምሮ ትዕዛዛቱን በጠበቀው፤ እናም ደግሞ እኛን ወደ ቃል ኪዳን ምድር በማምጣት በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ በሆነው፣ በወንድማችሁ ላይ አታምፁ፤ በእርሱ ባይሆን ኖሮ፣ ሁላችንም በምድረበዳው ሀበረሃብ ባለቅን ነበርና፤ ይሁን እንጂ፣ እናንተ ለልትገድሉት ሞክራችኋል፤ አዎን፣ እናም እርሱ በእናንተ የተነሳ ብዙ መከራን ተቀብሏል።
፳፭ እናም እኔ እርሱ በእናንተ የተነሳ ድጋሚ ይሰቃያል ብዬ በእጅጉ እፈራለሁ፤ እነሆም እናንተ እርሱ በእናንተ ላይ ሀስልጣንና ኃይልን ይፈልጋል ብላችሁ ወቅሳችሁታል፤ ነገር ግን እርሱ ኃይልንና ስልጣንን በእናንተ ላይ እንዳልፈለገ አውቃለሁ፣ ነገር ግን እርሱ የእግዚአብሔርን ክብርና የእናንተን ዘለዓለማዊ ደህንነት ይፈልጋል።
፳፮ እናም እናንተ እርሱ ለእናንተ ግልፅ በመሆኑ አጉረምርማችኋል። እናንተ እርሱ ቁርጥ ቃል ተናግሯል ብላችኋል፤ ተቆጥቶናል ብላችኋል፤ ነገር ግን እነሆ፣ የእርሱ ሀኃይለኝነት በእርሱ ውስጥ በነበረው በእግዚአብሔር ቃል ኃይል ነው፣ እናም እናንተ ቁጣ የምትሉትም ሊያቆመው የማይችለው በእግዚአብሔር ውስጥ ባለው መሰረት የእናንተን ኃጢአቶች በግልፅ የሚገልጸው እውነት ነው።
፳፯ እናም እናንተም ያዘዛችሁን መቀበል እስኪኖርባችሁ ድረስ የእግዚአብሔር ሀኃይል በእርሱ ውስጥ መሆን አለበት። ነገር ግን እነሆ፣ መዝጋት እስኪያቅተው አፉን ለበመክፈት ያናገረው እርሱ ሳይሆን በውስጡ የነበረው የጌታ ሐመንፈስ ነው።
፳፰ እናም አሁን ልጆቼ፣ ላማንና፣ ደግሞም ልሙኤልና ሳም፣ እናም ደግሞ የእስማኤል ልጆች የሆናችሁ ልጆቼ፣ እነሆ፣ የኔፊን ድምፅ የምትሰሙ ከሆነ አትጠፉም። እናም እርሱን የምታደምጡ ከሆነ ሀበረከቴን እተውላችኋለሁ፣ አዎን የመጀመሪያውን በረከቴንም እንኳን ቢሆን።
፳፱ ነገር ግን እርሱን የማታደምጡ ከሆነ ሀየመጀመሪያውን በረከቴን እወስድባችኋለሁ፣ አዎን፣ እንዲሁም የእኔን በረከት፣ እናም በእርሱ ላይ ያርፋል።
፴ እናም አሁን ዞራም፣ ለአንተ እናገራለሁ—እነሆ፣ አንተ ሀየላባን አገልጋይ ነህ፤ ይሁን እንጂ፣ አንተ ከኢየሩሳሌም ምድር ወጥተሀል፣ እናም አንተ ለልጄ ለኔፊ እውነተኛና የዘለዓለም ጓደኛው እንደሆንክ አውቃለሁ።
፴፩ ስለሆነም አንተ ታማኝ በመሆንህ ዘርህ ከእርሱ ዘር ሀጋር የተባረከ ይሆናል፣ በዚህች ምድር ላይ ለብዙ ጊዜ በብልፅግና ይኖራሉ፤ እናም ከክፋት በስተቀር በዚህች ምድር ላይ ለዘለዓለም ብልፅግናቸውን የሚጎዳቸው ወይም የሚረብሻቸው ምንም አይኖርም።
፴፪ ስለሆነም፣ እናንተ የጌታን ትዕዛዛት የምትጠብቁ ከሆነ፣ ጌታ ይህችን ምድር ለዘርህ ደህንነት ከልጄ ዘር ጋር ይቀድሳል።