ምዕራፍ ፳፭
ኔፊ በግልፅነት ይደሰታል—የኢሳይያስ ትንቢቶች በመጨረሻው ዘመናት ግልፅ ይሆናሉ—አይሁድ ከባቢሎን ይመለሳሉ፣ መሲሁንም ይሰቅላሉ፣ እናም ይበተናሉ፣ ይቀሰፋሉም—በመሲሁ ሲያምኑ ደግመው ይመለሳሉ—በመጀመሪያ ሌሂ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ከስድስት መቶ አመት በኋላ ይመጣል—ኔፋውያን የሙሴን ህግ ይጠብቃሉ፣ የእስራኤሉ ቅዱስ በሆነው ክርስቶስም ያምናሉ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።
፩ አሁን እኔ ኔፊ፣ በኢሳይያስ አፍ ስለተነገሩት፣ እኔ ስለፃፍኳቸው ቃላት በመጠኑ እናገራለሁ። እነሆም ኢሳይያስ ለብዙ ህዝቦቼ ለመረዳት ሀአስቸጋሪ የሆኑ ብዙ ነገሮችን ተናግሯል፤ እነርሱም በአይሁድ መካከል ስላለው በትንቢት አነጋገር አያውቁምና።
፪ እኔ ኔፊ ስለአይሁዶች አኳኋን ብዙም አላስተማርኳቸውምና፤ ሀስራዎቻቸው የጨለማ ስራ፣ አድራጎታቸውም የእርኩሰት አድራጎት ነበሩና።
፫ ስለዚህ፣ ለህዝቦቼም ሆነ ከዚህ በኋላ እነዚህን የምፅፋቸውን ለሚቀበሉ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ፍርድ፣ በሁሉም ሀገሮች ላይ እርሱ በተናገረው ቃል መሰረት እንደሚመጡ ያውቁ ዘንድ ይህንን እፅፋለሁ።
፬ ስለዚህ፣ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ ህዝቤ ሆይ፣ አዳምጡኝ፣ ቃላቶቼንም ለመስማት ጆሮአችሁን ስጡ፣ የኢሳይያስ ቃላት ለእናንተ ግልፅ አይደሉም፣ ይሁን እንጂ ሀበትንቢት ለመንፈስ ለተሞሉት ሁሉ ግልፅ ናቸው። ነገር ግን እኔ በውስጤ ባለው መንፈስ መሰረት ይህንን ትንቢት እሰጣችኋለሁ፤ ስለዚህ ከአባቴ ጋር ኢየሩሳሌምን ለቅቄ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ባለኝ ሐግልፅነት እተነብይላችኋለሁ፤ እነሆም ህዝቦቼ ይማሩ ዘንድ ነፍሴ በግልፅነት ትደሰታለች።
፭ አዎን፣ ነፍሴ ሀበኢሳይያስ ቃላት ትደሰታለች፣ እኔ ከኢየሩሳሌም ወጥቻለሁና፣ አይኖቼም ለየአይሁዶችን ነገር አይታለች፣ እናም አይሁድ የነቢዩን ነገሮች እንደተረዱት አውቃለሁ፣ እናም በአይሁዶች ጉዳይ የተማሩ ካልሆኑ በስተቀር ለአይሁዶች የተነገሩትን ነገሮች ከራሳቸው በቀር የሚረዳው ማንም የለም።
፮ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ ኔፊ፣ ልጆቼን የአይሁድ ጉዳዮችን አላስተማርኳቸውም፤ ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ራሴ፣ በኢየሩሳሌም ኖሬአለሁ፣ ስለዚህ በዙሪያዬ ስለነበሩት ክልሎች በተመለከተ አውቃለሁ፤ ለልጆቼም ኢሳይያስ በተናገረው ሁሉ መሰረት በአይሁድ መካከል ሀሊመጣ ስላለውም የእግዚአብሔር ፍርድ ለልጆቼ ገልጬላቸዋለሁ፣ እናም እኔ አልፅፋቸውም።
፯ ነገር ግን እነሆ፣ እኔ ሀበግልፅነቴ መሰረት የራሴን ትንቢት እቀጥላለሁ፤ በዚህም ማንም ሰው እንደማይሳሳት አውቃለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ የኢሳይያስ ትንቢት በሚፈፀምበት ጊዜ፣ ሆነውም ሲያልፉ፣ ሰዎች እርግጠኛነቱን ያውቃሉ።
፰ ስለዚህ፣ ለሰው ልጆች ሀጥቅም አላቸው፣ እናም አይኖራቸውም ብሎ የሚያስብ፣ እኔ እነርሱን በተለይ እናገራቸዋለሁ፣ እናም ለለህዝቤ ብቻ ቃሉን እናገራለሁ፤ ምክንያቱም ሐበመጨረሻ ቀናት ለእነርሱ ታላቅ ዋጋ እንደሚኖራቸው አውቃለሁ፤ በዚያ ቀንም ይረዱአቸዋልና፤ ስለሆነም፣ ለጥቅማቸው ፅፌአቸዋለሁና።
፱ እናም በክፋታቸው የተነሳ ከአይሁዶች መካከል ሀእንደጠፋው አንድ ትውልድ፣ እንደ ክፋታቸው እነርሱም ከትውልድ እስከ ትውልድም ሊጠፉ ችለዋል፤ እናም በጌታ ነቢያት አማካኝነት ለአስቀድሞ ካልተነገረላቸው በስተቀር ማናቸውም አልጠፉም።
፲ ስለሆነም፣ አባቴ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ወዲያው በእነርሱ ላይ የሚመጣባቸውን ጥፋት በተመለከተ ተነግሯቸዋል፤ ይሁን እንጂ፣ እነርሱ ልባቸውን አጠጠሩ፤ እናም በትንቢቴ መሰረት ወደ ባቢሎን በምርኮ ሀከተወሰዱት በስተቀር ሌሎች ለጠፍተዋል።
፲፩ እናም አሁን ይህን የምናገረው በውስጤ ባለው መንፈስ የተነሳ ነው። እናም እነርሱ ቢወሰዱም እንኳን እንደገና ይመለሳሉ፣ የኢየሩሳሌምን ምድርንም ይወርሳሉ፤ ስለሆነም፣ ወደ ርስት ምድራቸው ሀእንደገና ይመለሳሉ።
፲፪ ነገር ግን፣ እነሆ፣ ጦርነትና የጦርነት ወሬዎች በመካከላቸው ይኖራቸዋል፤ እናም የአብ ሀአንድያ ልጅ፣ አዎን፣ የሰማይና የምድር አባት የሆነውም እንኳን፣ በስጋ እራሱን የሚገልፅበት ቀን በሚመጣበት ጊዜ፣ እነሆ፣ በክፋታቸውና በልባቸው ጠጣርነት እንዲሁም በአንገተ ደንዳናነታቸው ምክንያት አይቀበሉትም።
፲፫ እነሆ፣ ሀይሰቅሉታል፤ እናም ከድንጋይ ከተወቀረው ለመቃብር ውስጥ ሐለሶስት ቀን ከቆየ በኋላ፣ ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ከሙታን መይነሳል፤ እናም በስሙ የሚያምኑ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግስት ይድናሉ። ስለሆነም፣ ነፍሴ እርሱን በተመለከተ ለመተንበይ ትደሰታለች፣ ቀኖቹን ሠአይቻለሁና፣ ልቤም ቅዱስ ስሙን ታመሰግናለች።
፲፬ እናም እነሆ እንዲህ ይሆናል ሀመሲሁ ከሞት ከተነሳ እናም፣ በስሙ ለሚያምኑ ለብዙዎች ሕዝቦቹ ራሱን ከገለጸ በኋላ፣ እነሆ፣ ኢየሩሳሌም በድጋሚ ለትጠፋለች፤ ከእግዚአብሔርና ከቤተክርስቲያኑ ሰዎች ጋር ለሚጣሉ ወዮላቸው።
፲፭ ስለሆነም፣ ሀአይሁዶች በሀገር ሁሉ መካከል ለይበተናሉ፤ አዎን፣ እናም ደግሞ ሐባቢሎን ትጠፋለች፤ ስለሆነም፣ አይሁዶች በሌሎች ሀገሮች ይበተናሉ።
፲፮ እናም እነርሱ ከተበተኑና፣ ለብዙ ዘመን ጌታ እግዚአብሔር በሌሎች ሀገሮች ከቀጣቸው በኋላ፣ አዎን፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ፣ እና ለሁሉም የሰው ዘር ያልተገደበውን የኃጢያት ክፍያ ሀለማመን እስኪገደዱም ድረስ—እናም በክርስቶስ የሚያምኑበትና፣ በፍፁም ልብና በንፁህ እጃቸው አብን በስሙ የሚያመልኩበት፣ እናም ሌላ መሲህ ይመጣል ብለውም የማይጠብቁበት ያ ቀን ሲመጣ፣ በኋላም፣ በዚያን ጊዜ እነዚህን ነገሮች ማመን ለእነርሱ አስፈላጊ የሚሆንበት ቀን ይመጣል።
፲፯ እናም ጌታ ለሁለተኛ ጊዜ ህዝቡን ከጥፋትና ከውድቀት ሀለመመለስ እጁን ይዘረጋል። ስለዚህ፣ በሰው ልጆች መካከል አስደናቂውንና ለድንቅ ስራውን መስራት ይቀጥላል።
፲፰ ስለዚህ፣ ሀቃሉን ይገልፅላቸዋል፣ እነዚህም ቃላት በመጨረሻውም ቀን ለይፈርድባቸዋል፣ ምክንያቱም በእነርሱ ስለተነቀፈው ስለ እውነተኛው መሲህ ዓላማ ሐለማሳመን ተሰጥቶአቸዋልና፤ እናም ከእንግዲህ መሲሁ ይመጣል ብለው እንዳይጠብቁ ለማሳመን፣ ህዝቡን የሚያታልለው መሀሰተኛው መሲህ ካልሆነ ሌላ ማንም ሊመጣ አይገባውምና፤ በነቢያት የተነገረበት አንድ መሲህ ብቻ ነው ያለውና፣ እናም ያ መሲህ በአይሁዶች የተነቀፈው ነው።
፲፱ በነቢያቶቹ ቃል መሰረት፣ አባቴ ኢየሩሳሌምን ለቆ ከወጣ ሀከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ለመሲሁ ይመጣል፤ እናም እንደ ነቢያቱ ቃል፣ ደግሞም በእግዚአብሔር ሐመልአክ ቃል መሰረት፣ ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል።
፳ እናም አሁን ወንድሞቼ እንዳትሳሳቱ ዘንድ በግልፅ ነግሬአችኋለሁ። እናም ከግብፅ ምድር እስራኤልን ሀያወጣና፣ ለሙሴ ህዝቡ በመርዘኛ እባብ ከተነደፉ በኋላ በፊታቸው ከፍ ያደረገውን ለእባብ ላይ አይናቸውን ከጣሉ ሐለመፈወስ ይችል ዘንድ ኃይልን የሰጠው፣ እናም ደግሞ መድንጋዩን መትቶ ውኃ እንዲፈልቅለት ኃይልን የሰጠው ጌታ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ፤ አዎን፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ነገሮች እውነት ናቸው፣ እናም ጌታ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እኔ እንደተናገርኩበት ከዚህ ከኢየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ሰው ሊድንበት የሚችል ምንም አይነት ሠስም ከሰማይ በታች የተሰጠ የለም።
፳፩ ስለዚህ፣ በዚህ ምክንያት ነው ጌታ እግዚአብሔር እነዚህን ሀየፃፍኳቸው ነገሮች እንደሚጠበቁና እንደሚቀመጡ፣ እናም ዘሮቹ ምድር እስካለችም ድረስ ለእንደማይጠፉ ለዮሴፍ የተገባለት ቃል ኪዳን እንዲሟላ ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ ለዘሮቼ እንደሚተላለፉ ቃል የገባልኝ።
፳፪ ስለሆነም፣ እነዚህ ነገሮች ምድር እስካለች ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋሉ፤ እናም እነሱም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና ደስታ ይተላለፋሉ፤ እናም እነርሱ ያሏቸውም ሀገሮች በተፃፉት ቃል መሰረት ሀይፈረድባቸዋል።
፳፫ ለመጻፍ፣ ልጆቻችንን እናም ደግሞ ወንድሞቻችንን በክርስቶስ እንዲያምኑና ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ሀለማሳመን በትጋት እንሰራለንና፤ ምክንያቱም ለበጸጋ የምንድነው የምንችለውን ሐካደረግን በኋላ እንደሆነ እናውቃለንና።
፳፬ እናም በክርስቶስ ብናምንም እንኳን የሙሴን ህግ ሀእንጠብቃለን፣ እናም ህጉ እስከሚፈፀም ድረስ በፅኑነት ወደፊት ወደክርስቶስን እንመለከታለን።
፳፭ ይህ ህግ የተሰጠው ለዚህ አላማ ነበርና፤ ስለሆነም ሀህጉ ለእኛ ለሙት ሆኗል፣ እናም እኛ በእምነታችን ምክንያት በክርስቶስ ህያው ሆነናል፤ ቢሆንም ግን ህጉን በትዕዛዝ ምክንያት እንጠብቃለን።
፳፮ እናም ሀልጆቻችን ለኃጢአታቸው ለስርየት የትኛውን ምንጭ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ፣ ሐስለክርስቶስ እንናገራለን፣ በክርስቶስ እንደሰታለን፣ ስለክርስቶስ እንሰብካለን፣ ስለክርስቶስ መትንቢት እንናገራለን፣ እናም በትንቢታችን መሰረት እንፅፋለን።
፳፯ ስለዚህ፣ ህጉን በተመለከተ ልጆቻችን የህጉን መሞት ያውቁት ዘንድ እንናገራለን፤ እናም እነርሱ የህጉን ሞት በማወቅ፣ በክርስቶስ የሚመጣውን ህይወት ይጠብቃሉ እናም ህጉ ለምን ዓላማ እንደተሰጠ ያውቃሉ። እናም ህጉ በክርስቶስ ከተፈፀመ በኋላ፣ ህጉ በሚፈፀምበት ጊዜ በእርሱ ልባቸውን ማጠጠር እንደማያስፈልጋቸው እንዲያውቁም ነው።
፳፰ እናም አሁን እነሆ ህዝቦቼ፣ አዎን እናንተ ሀአንገተ ደንዳና ህዝብ ናችሁ፤ እኔ በግልፅ የተናገርኳችሁ አንዳትደናገሩም ነው። የምናገረው ቃል ለእንደምስክር በእናንተ ላይ ይቆማሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ማንኛውንም ሰው ትክክለኛውን መንገድ ሐለማስተማር በቂ ናቸውና፤ ትክክለኛው መንገድ በክርስቶስ ማመንና እርሱን አለመካድ ነውና፤ ምክንያቱም እርሱን በመካድ እናንተ ደግሞ ነቢያትንና ህጉን ትክዳላችሁና።
፳፱ እናም እነሆ አሁን፣ ትክክለኛው መንገድ በክርስቶስ ማመን ነው እላችኋለሁ፣ እርሱንም አትካዱ፤ እናም ክርስቶስ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ በፊቱ መስገድና፣ በሙሉ ሀኃይላችሁ፣ አእምሮአችሁና ጉልበታችሁ እንዲሁም በፍፁም ነፍሳችሁ እርሱን ማምለክ አለባችሁ፤ እናም ይህን ካደረጋችሁ በምንም ሁኔታ አትጣሉም።
፴ እናም አስፈላጊ እስከሆነ፣ ለሙሴም የተሰጠው ህግ እስከሚፈፀም ድረስ የእግዚአብሔርን ስራና ሀስርዓቱን መጠበቅ አለባችሁ።