የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፯


ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፯፥፭–፳፯።ሮሜ ፯፥፭–፳፭ ጋር አነጻፅሩ

የሰዎችን ነፍሶች ቋሚ በሆነ ሁኔታ ለመልካም ለመቀየር ሀይል ያለው ክርስቶስ ብቻ ነው።

በህግ መሰረት ያልሆነው፣ በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና።

አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት፣ በህጉ ሞተን፣ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።

እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? ይህ ከእኛ ይራቅ። አይደለም፣ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።

ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ። ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።

እኔም ዱሮ ሕግ ባለመተላለፍ ሕያው ነበርሁ፣ የክርስቶስ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ፣ እኔም ሞትሁ።

ለሕይወትም የተሰጠችውን፣ የመጣችውን የክርስቶስ ትእዛዝ ሳላምንም፣ እርስዋን ለሞት ያኮነነችኝ ሆና አገኘኋት።

፲፩ ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ ትእዛዝን በማስወገድ አታሎኛልና፤ በእርስዋም ተገድያለሁ።

፲፪ ይህም ቢሆን፣ ሕጉ ቅዱስ፣ ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅ በጎም ሆነው አገኘዋቸው።

፲፫ እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን? ይህ ከእኛ ይራቅ። ነገር ግን ኃጢአት፣ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፣ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር።

፲፬ ትእዛዝ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን በህግ በታች ስሆን፣ ከኃጢአት የተሸጥሁ የሥጋ ነበርኩኝ።

፲፭ አሁን ግን መንፈሳዊ ነኝ፤ እንዳደርግ የታዘዝኩትን አደርጋለሁና፤ እና እንዳልፈቅድ የታዘዝኩትን አልፈቅድምና።

፲፮ ትክክል እንደሆነ የማላውቀውን አላደርግም፤ ኀጥያት የሆነውን እጠላለሁና።

፲፯ ከእዚያም የማልፈቅደውን አላደርግም፣ ለህግም ጥሩ እንደሆነ እስማማለሁ፤ አልተኮነንኩምም።

፲፰ እንደዚህ ከሆነ ምንም ኀጥያት አልሰራም፤ ነገር ግን በእኔ የሚያድር ኃጢያትን ለመቋቋም እፈልጋለሁ እንጂ።

፲፱ በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንደማይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፣ መልካሙን ግን ማድረግን፣ ከክርስቶስ ውስጥ በስተቀር፣ አላገኘሁም።

በህግ ውስጥ እያለሁ መልካም የማደርገው፣ በጎ ሆኖ አላገኘሁትምና፤ ስለዚህ አላደርገውም።

፳፩ ነገር ግን በህግ ውስጥ የማላደርገውን ክፋት፣ በጎ ሆኖ አግኝቻለሁ፤ ያንንም አደርጋለሁ።

፳፪ አሁን ያን በክርስቶስ እርዳታ ካደረግኩኝ፣ በህግ ውስጥ አላደርገውም፣ ከህግ በታችም አይደለሁም፤ እናም ምንም ጥፋትን ለመስራት አልፈልግም፣ ነገር ግን በእኔ የሚያድር ኃጢአትን ለመቋቋም እፈልጋለሁ እንጂ።

፳፫ እንግዲያስ በህግ በታች መልካሙን ሳደርግ በእኔ ክፉ እንደሚያድርብኝ አግኝቻለሁ፤ በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና።

፳፬ አሁንም ሌላ ሕግ አያለሁ፣ እንዲሁም የክርስቶስ ትእዛዝ፣ እና በአዕምሮዬም ታትሟል።

፳፭ ነገር ግን ብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር ይዋጋሉ፣ በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ ወደሚማርከኝ ያመጣኛል።

፳፮ እና በውስጤ ያለውን ኀጥያት ካልተቋቋምኩኝ፣ ከስጋ ጋር ግን የኀጥያት ህግን አገለግላለሁ፤ እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?

፳፯ በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና እሰጣለሁ፣ እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ በእግዚአብሔር ሕግ እገዛለሁ።