የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪፥፱–፲፪።ሉቃስ ፲፪፥፱–፲ ጋር አነጻፅሩ፤ ደግሞም ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፪፥፴፯–፴፰ እና ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፮–፳፯ ተመልከቱ

ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን መስደብ እንደማይሰረይ ገለጸ።

ነገር ግን እኔን በሰው ፊት የሚክደኝ፣ በእግዚአብሔር መላእክቶች ፊት ይካዳል።

አሁን ደቀ መዛሙርቱ ይህን ያለው ስለእርሱ በሰዎች ፊት ክፉን ተናግረው ስለነበር እንደሆነ አወቁ፤ በሰዎች በፊት ስለእርሱ ለመመስከር ፈርተው ነበርና።

፲፩ እና እንዲህ በማለትም እርስ በራሳቸው እየተወያዩ አሉ፣ ልባችንን ያውቃል፣ እና ለኩነኔአችን ይናገራል፣ እና አይሰረይልንም። ነገር ግን እርሱ መለሳቸው፣ እና እንዲህም አላቸው፣

፲፪ በሰው ልጅም ላይ ቃል የሚናገር፣ እና ንስሀ የሚገባ፣ ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ ግን አይሰረይለትም።

ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪፥፵፩–፶፯።ሉቃስ ፲፪፥፴፯–፵፰ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ አገልጋዮቹ ለእርሱ መምጣት ሁልጊዜም መዘጋጀት እንዳለባቸው ገለጸ።

፵፩ እነሆ በለሊቱ በመጀመሪያ ክፍል ይመጣልና፣ እና በሁተኛው ክፍልም ደግሞ ይመጣል፣ እና እንደገናም በሶስተኛው ክፍልም ይመጣል።

፵፪ እና እውነት እላችኋለሁ፣ ስለእርሱ እንደተጻፈውም አስቀድሞም መጥቷል፤ እንደገናም ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፣ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤

፵፫ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ይታጠቃል፣ እና ምግብ ለመመገብም ይቀመጣሉ፣ እና መጥቶም ያገለግላቸዋል።

፵፬ አሁንም፣ የጌታ መምጣት እንደሌባ በማታ እንደሚመጣ እነዚህን ነገሮች እንድታውቁ ዘንድ፣ እውነት እላችኋለሁ።

፵፭ እና ይህም እቃዎቹን ካልጠበቀ በማያውቅበት ሰአት ሌባ እንደመጣበት እና እቃዎቹን እንደወሰደበት እና ከጓደኞቹ ጋር እንደተከፋፈለበት ባለቤት ሰው አይነት ነው።

፵፮ እና እርስ በራሳቸውም ተባባሉ፣ ጥሩው ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ በነቃ፣ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም፣ እና እቃዎቹን ባላጣ ነበር።

፵፯ እና እንዲህ አላቸው፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

፵፰ ጴጥሮስም ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ ለእኛ ወይስ ደግሞ ለሁሉ ትናገራለህን? አለው።

፵፱ ጌታም አለ፣ የተናገርኩት እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ለልጆቹ ለሚሰጧቸው ጌታ በቤተ ሰዎቹ ላይ ለሚሾሙት ነው።

እነርሱም ታማኝና መጋቢ አገልጋይ ማን ነው? አሉ።

፶፩ ጌታም አላቸው፣ ይህም የምግቡን ክፍል በጊዜው ለመስጠት የሚጠብቀው አገልጋይ ነው።

፶፪ ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው።

፶፫ እውነት እላችኋለሁ፣ ባለው ሁሉ ላይ መሪ ያደርገዋል።

፶፬ ያ ክፉ ባሪያ ግን ሲጠብቅ የማይገኘው ነው። እና ያ ባሪያ ሳይጠብቅ ከተገኘ፣ በልቡም ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ ያስባል፤ እና ሎሌዎችን ባሪያዎችና ገረዶችንም መምታት፣ መብበምላትም፣ መጠጣትም፣ መስከርም ይጀምራል።

፶፭ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፣ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል እድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።

፶፮ የጌታውንም ፈቃድ አውቆ፣ ለጌታው መምጣት ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል።

፶፯ የጌታውን ፈቃድ ያላወቀ፣ መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ግን ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ጌታ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ ሰዎች አብዝተው ይሹበታል።