የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫፥፬–፲፩።ሉቃስ ፫፥፬–፮ ጋር አነጻፅሩ

ክርስቶስ እንደተተነበየው ደህንነትን ለእስራኤል እና ለአህዛብ ለማምጣት ይመጣል። በዘመን ፍጻሜ፣ በአለም ላይ ለመፍረድ እንደገና ይመጣል።

በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ ውስጥ እንደተጻፈው፤ እና ቃላቶቹም እነዚህ ናቸው፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረበዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ አለ።

እነሆ፣ እና አስተውሉ፣ በነቢያት መፅሀፍ ውስጥ እንደተጻፈውም የአለምን ኀጥያቶች ለማስወገድና ወደ አህዛብ ህዝቦችም ደህናነትን ለማምጣት፣ የጠፉትንም፣ የእስራኤል በግ መንጋዎች የሆኑትን፣ ለመሰብሰብ ይመጣል።

አዎን፣ እንድሁም የተበተኑትን እና የሚሰቃዩትን፤ ደግሞም መንገድን ለማዘጋጀት፣ እና ለአህዛባት ወንጌልን ለመስበክ የሚቻልም ለማድረግ፤

በጭለማ ጥላ ተቀምጠው ላሉትም፣ እስከ ምድር ዳርም ድረስ፣ ብርሀን ለመሆን፤ የሙታንን ትንሳኤ ለማምጣት፣ እና በአብ ቀኝ እጅ በኩል ለመኖር ወደላይም ለማረግ፣

እስከ ዘመን ፍጻሜ፣ እና ህግ እና ምስክር እስከሚታተም፣ እና የመንግስት ቁልፍም ወደ አብ እስከሚመለሱ ድረስ፤

ለሁሉም ፍርድ ለመስጠት፤ በሁሉም ላይ ለፍርድ ለመውረድ፣ እና እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች ስለሰሩት እግዚአብሔርን የማያመልኩ ስራቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ፤ እና ይህም ሁሉ በሚመጣበት ቀን።

ይህም የሀይል ቀን ነውና፣ አዎን፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሞላል፣ እና እያንዳንዱ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሆናል፣ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሆናልና፤

፲፩ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።

ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫፥፲፱–፳።ሉቃስ ፫፥፲–፲፫ ጋር አነጻፅሩ

ደሆች ከግምጃ ቤት ትርፍራፊ እንክብካቤ ያገኛሉ። ቀራጮችም በህግ ከተመደበላቸው በላይ ምንም አይወስዱም።

፲፱ ቴዎፍሎስ፣ ይህም በአንተ በደንብ ይታወቃል፣ በአይሁዳ ልምድ መሰረት፣ እና ገንዘብን ወደ ግምጃ ቤት በሚቀበሉበት በህጋቸው ባህል መሰረት፣ ከተቀበሉት ግምጃ ቤት ትርፍ ውስጥ ለድሆች ተመድቧል፣ ለእያንዳንዱ ሰው ክፍሉም፤

እና ከዚህም መንገድ ቀራጮችም አደረጉ፣ ስለዚህ ዮሐንስ ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው።