የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፪


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፪፥፴፯–፴፰።ማቴዎስ ፲፪፥፵፫–፵፬ ጋር አነጻፅሩ፤ ደግሞም ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪፥፱–፲፪ ተመልከቱ

በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር አይሰረይለትም።

፴፯ ከዚያም ከጸሀፊዎች አንዳንድ መጡ እና ለእርሱም እንዲህ አሉ፣ መምህር፣ እያንዳንዱ ኃጢያት ይሰረያሉ ተብሎ ተፅፏል፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር አይሰረይለትም ብለሀል። እናም እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ እነዚህ ነገሮች እንዴት ይሆናሉ?

፴፰ እርሱም እንዲህ አላቸው፣ ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም፤ ነገር ግን ሰው በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሲናገር፣ በዚያን ጊዜም፣ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል፤ ምክንያቱም መልካሙ መንፈስ ለራሱ ይተወዋል።