ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፯፥፲–፲፬። ከማቴዎስ ፲፯፥፲፩–፲፫ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ አንዱ ለማዘጋጀት እና አንዱ ዳግም ለመመለስ፣ ስለሚያደርጉት ሁለት ኤልያሶች አስተማረ።
፲ ኢየሱስም መለሰ እና እንዲህ አላቸው፣ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፣ እና በነብያት እንደተጻፈው ሁሉንም ነገሮች ደግሞ ይመልሳል።
፲፩ እንደገናም እላችኋለሁ፣ እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፣ እና እርሱም መንገዴን በፊቴ ያዘጋጃል ተብሎ ስለእርሱ የተጻፈበት ኤልያስ ከዚህ በፊት መጥቷል፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም።
፲፪ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበላል።
፲፫ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ኤልያስ ማን ነው? እነሆ፣ መንገዴን በፊቴ እንዲያዘጋጅ የላኩት፣ ይህም ኤልያስ ነው።
፲፬ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፣ እና ደግሞም በነቢያት እንደተጻፈው መጥቶ ሁሉንም ነገሮች ዳግሞ ስለሚመልሰው እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።