የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩፥፴፫።ማቴዎስ ፳፩፥፴፪–፴፫ ጋር አነጻፅሩ

ሰው በኢየሱስ ከማመኑ በፊት ንስሀ መግባት አለበት።

፴፫ ዮሐንስ እኔን በሚመለከት ያለውን የማያምን ንስሀ ካልገባ በስተቀር አያምነኝም።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩፥፵፯–፶፮።ማቴዎስ ፳፩፥፵፭–፵፮ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ዋና የማዕዘኑም ድንጋይ እንደሆነ ገለጸ። ወንጌሉ ለአይሁድ ይቀርባል፣ ከዚያም ለአህዛብ። ክፉዎች ኢየሱስ ሲመለስ ይደመሰሳሉ።

፵፯ እና ካህናት እና ፈሪሳዊያን የእርሱን ምሳሌዎች ሲሰሙ፣ ስለእነርሱ እንደተናገረ ገባቸው።

፵፰ እና እንዲህ ተባባሉ፣ ይህን ታላቅ መንግስት እርሱ ብቻውን አበላሻለሁ ብሎ ያስባል? እና በእርሱም ተናደው ነበር።

፵፱ ነገር ግን ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ ፈሩአቸው፣ ምክንያቱም ህዝቡ እንደ ነቢይ እንደሚያዩት ስላወቁ።

አሁንም ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ፣ እና ኢየሱስ አላቸው፣ ለእነርሱ በተናገርኩት የምሳሌ ቃሎቼ ተደንቃችኋል?

፶፩ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ አለት ነኝ፣ እና ክፉዎቹ ተቃወሙኝ።

፶፪ የማዕዘን ራስ ነኝ። እነዚህ አይሁዶች ይወድቁብኛል፣ እና ይሰበራሉ።

፶፫ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእነርሱ ትወሰዳለች፣ ፍሬዋንም ለሚያመጣ ሕዝብ ትሰጣለች፤ (ይህም ማለት አህዛቦች)።

፶፬ ስለዚህ፣ ድንጋዩ የሚወድቅበት ይፈጨዋል።

፶፭ እና የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ፣ እነርሱ የማይረቡ ክፉ ሰዎችን ያጠፋቸዋል፣ እና የወይኑንም አትክልት ስፍራውን፣ እንዲሁም በመጨረሻው ቀናት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል።

፶፮ ከእዚያም ጌታ ከሰማይ ምድር ወደሆነው ወደ ወይን አትክልቱ እና በእርሷ ውስጥ ወደሚኖሩት ሲወርድ፣ አህዛቦችም ደግመው እንደሚጠፉ የነገራቸው ምሳሌ ገባቸው።